ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የውጭ አገር ዜጎች “ኢሳት የህወሀቱ መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ በሀዲድ አምራችነት የሚሳተፍበት የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድ ግንባታ በከፍተኛ ሙስና ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም” በሚል ርእስ በኢሳት የወጣውን ዜና ከተመለከቱ በሁዋላ በዜናው ላይ ማሻሻያ ያሉዋቸውን ነጥቦች በማከልና ኩባንያው በመላው አለም ስለሚፈጽመው ሙስና የሚያትት በጣሊያንኛ ቋንቋ የተጻፈ መልእክት ልከዋል። ከአውሮፓ ህብረት በተገኘው 41 ሚሊዮን ዩሮ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ ለግብጽ አንድ ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር መሬት ልትሰጥ ነው
ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እየተገነባ ባለው የህዳሴው ግድብ ሳቢያ ግብጽ ችግር ልትፈጥርብን ትችላለች የሚል ስጋት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊ ሚዲያዎች ሲስተጋቡ ቢሰሙም፤ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን በተቃራኒው በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለው የልማት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱን ነው ይፋ ያደረጉት። የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሺም ካንዲ በቅርቡ በአልጀሪያ ባደረጉት የሁለት ቀናት ጉብኝት ላይ ፤አገራቸው ፤ በአልጀሪያና በኢትዮጵያ ሁለት የኢንዱስትሪ ዞኖችን ...
Read More »የሚኒሰትር ጁኔዲን ሳዶ ባለቤት ፍርድ ቤት ቀረቡ
ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችና ኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ ክስ ከመሰረተባቸው ሰዎች መካከል አንዷ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትሩ ባለቤት የሆኑት 28ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሀቢባ ሙሀመድ መሆናቸው ...
Read More »አቃቢ ህግ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ክስ መሰረተ
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛር ከጧቱ 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችናኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ ተምልክቷል። ብርሀኑ ወንድማገኘሁ ፣ ዘረሰናይ ምስግናው እና ቴዎድሮስ ባህሩ አቃቢ ህጎች ሆነው የቀረቡ ...
Read More »ባለፉት 30 አመታት ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደ ውጭ አገራት ባንኮች የተሻገረው ገንዘብ 450 ቢሊዮን ብር ደረሰ
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካ የሚገኘው የማሳቹሴትስ ዩኒቨርስቲ በያዝነው ወር ባወጣው አዲስ ጥናት ከኢትዮጵያ እየተዘረፈ ወደ ውጭ አገራት ባንኮች የተሻገረው ገንዘብ ባለፉት 30 አመታት ውስጥ 25 ቢሊዮን ዶላር ወይም 450 ቢሊዮን ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል። ይህ አሀዝ አገሪቱ ካላት አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 84 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍን ነው። ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ሲተያይ የ8ኛ ደረጃነት ብትይም ...
Read More »ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሞ ገጠመው
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድሮ የሚያካሂደውን የአዲስአበባ እና የአካባቢ ምርጫ አስመልክቶ ያዘጋጀውን ጊዜያዊ የምርጫ ማስፈጸሚያ ጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመምከር ባለፈው ሐሙስ ዕለት በአዳማ የጠራው ስብሰባ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ያልተጠበቀ ተቃውሞን በመቀስቀሱ ሁኔታው የቦርዱን አመራሮች አደናግጦ እንደነበር አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ ቦርዱ በጠራው በዚሁ ስብሰባ ላይ ከ70 በላይ ፓርቲዎች ተወካዮቻቸውን የላኩ ሲሆን ስብሰባው በተጠራበት ...
Read More »ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ፤ህግ ሊዘጋጅ ነው
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህ የተጠቆመው፤ የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። እንደ ስብሰባው ምንጮች ገለፃ ምልአተ ጉባኤው በጥቅምት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ውሎው በፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ዝግጅት ዙሪያ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በውሳኔው መሠረት ቀደም ሲል የሕገ ቤተ ክርስቲያንን ማሻሻያ እንዲሠራ የተሠየመው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ምሁራን ኮሚቴ፤ የፓትርያርክ ምርጫ ...
Read More »መንግስት 2 የእስልምና ተቋማትን ጨምሮ 8 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ዘጋ
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የየበጎ አድራጎት ማህበራት ምዘገባ ኤጀንሲ የእስልምና ጥናት ምርምር ማእከልንና የአወልያ ትምህርት ቤትን የምዝገባ ፈቃዳቸውን በመሰረዝ እንዲዘጉ ውሳኔ አስተላልፎአል። የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ “የእስልምና ጥናት ምርምር እና አወልያ ትምህርት ቤት ፣ የበጎ አድራጎት ስራ እንዲሰሩ ፈቃድ የተሰጣቸው ቢሆንም ፣ ከዚህ ሀላፊነታቸው ውጭ በመሄድ በሀይማኖት ጉዳይ ላይ ስራ ሲሰሩ በመገኘታቸው ተዘግተዋል” በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ...
Read More »መንግስት በግብር ክፍያ ላይ የማሻሻያ እርምጃ ለመውሰድ አለመፈለጉ ነጋዴውን እያማረረ ነው
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘጋቢያችን እንደገለጠው በመላ አገሪቱ የሚገኙ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር ያልተመታጠነ ግብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ከመማረር አልፈው የንግድ ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ፣ የቻሉትም ስደትን እየመረጡ ነው ። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነጋዴ እንደተናገሩት ሁለት ክፍል ቤታቸውን በወር 800 ብር በማከራየት ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ቢሆንም ከ2 ሺህ ብር በላይ የሆነ የአመት ግብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸው፣ የሚይዙትን ...
Read More »ቃሊቲ አካባቢ በተፈጠረው የቡድን ጸብ ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ያለፉትን 3 ቀናት በፍርሀት ቤቱ ውስጥ ለማሳለፍ ተገደደ
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ልዩ ቦታው ሳሎ ጊዮርጊስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ በተፈጠረው የቡድን ጸብ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደልባቸው ወጥተው ስራ ለመስራት ተቸግረዋል። ባለፉት 2 ቀናት ጸቡ በመባባሱ አንድ ወጣት በቤቱ ውስጥ በሽጉጥ ተመትቶ መሞቱን ለማወቅ ተችሎአል። እናቶች ከመጨነቃቸው የተነሳ ወጣት ልጆቻቸውን መደበቃቸውም ታውቋል። ፖሊስ የቤት ለቤት ፍተሻ መጀመሩ ቢነገርም እስካሁን ድረስ ችግሩን ባለመፍታቱ ...
Read More »