ጥቅምት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታሪካዊውን ምርጫ 97ትን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት የሞቱ ሰማእታት 7ኛ አመት በተለያየ መንገድ እየታወሰ ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ልዩ ግምት የሚሰጠው ምርጫ 97 የኢትዮጵያውያንን የዲሞክራሲ እና የነጻነት ህልም ያጨለመ እንደነበር በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች እና አለማቀፍ ድርጅቶች ሲገልጹ ቆይተዋል። በምርጫው ማግስት በተፈጠረው ግጭት ከ200 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ1 ሺ ያላነሱት ደግሞ መቁሰላቸውን እንዲሁም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ላለፉት አስር ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው የአገር ቤቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ
ጥቅምት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቅዱስ ሲኖዶሱ በርካታ ጉዳዮችን አንስቶ በጥልቀት በመዳሰስ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፤ በአገር ቤትና እንዲሁም በውጭ አገር በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል በመጪው ኅዳር ወር በዳላስ ቴክሳስ ለሚካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶሱ ልኡክ መደራደሪያ ናቸው የተባሉ አምስት ነጥቦች ለይቶ ማስቀመጡን ደጀ ሰላም ድረ ገጽ ዘግቧል። እነኚህም አምስቱ ነጥቦች “የሰላምና አንድነት ጉባኤው” ...
Read More »በሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለህዳሴ ግድብ ማሰሪያ የተሰበሰበ ብር ተዘረፈ
ጥቅምት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለህዳሴ ግድብ ማሰሪያ ከሰራተኛው የተሰበሰበ ከ 35,ሺ ብር በላይ ተዘረፈ:: ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው መስሪያ ቤቱ የተዘረፈውን ገንዘብ ከመንግስት ካዘና ወጪ በማድረግ ለመሙላት ሞክሯል፡፡ እስካሁን ድረስ ከመስሪያቤቱ በተለያዩ ጊዜያት ከ245, ሺ ብር በላይ የተሰረቀ ሲሆን ጉዳዩ እንዲጣራ ያዘዙ የስራ ሃላፊ በሰበብ አስባቡ ከሃላፊነታቸው እየተነሱ ...
Read More »ለአማራው መብት የሚታገል ሲቪክ ተቆም ተመሰረተ
ባለፉት 21 አመታት በአማራው ብሄረሰብ ላይ በገዥው ፓርቲ የደረሰበትን መፈናቀል፣ መገፋት መገለልና የዘር ማጽዳት እርምጃ ለመታደግና ለመታገል ያለመ ሲቪክ ድርጅት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ተመሰረተ:: ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የተሰኘው ይህ ሲቪክ ተቆም ከትላንት በስቲያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላለፉት 21 አመታት የአማራው ብሄረሰብ አባል ተዋራጅና ተሸማቃቂ ተደርጎል፣የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅሞቹ ተነጥቀዋል ከምስራቅ፣ከደቡብ ምእራብ፣ከደቡብና ከመሀል ኢትዮጵያ መኖር አትችልም ተብሎ ሀብት ንብረቱ ተነጥቆ ተባሮል ...
Read More »የንግዱ ማህበረሰብ አሁንም በታክስ ክፍያ እየተማረረ ነው
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች መንግስት ከገቢያቸው ጋር ያልተጣጣመ ታክስ እንዲከፍሉ በማስገደዱ ድርጅታቸውን ለመዝጋት እየተገደዱ መሆኑን ለኢሳት ገልጠዋል። በደቡብ ጎንደር ወረታ ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ነጋዴ እንዳለው በግብር የተነሳ ህዝቡ እየተሰደደ ነው ብሎአል ። ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ በጨርቃጨርቅ ስራ ላይ የተሰማራ ነጋዴ በበኩሉ በግብር የተነሳ ቤተሰቡን እስከመበተን መድረሱን ተናግሯል ወረታ በእህል ንግድ ላይ ...
Read More »የሙስሊም ችግር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አዲስ የትግል ስልት መቀየሱን አስታወቀ
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ተወካዮች የ ኢህአዴግ መንግስት ከ ህገመንግስት እውቅና ውጭ በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ለማስቆም እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የአህባሽን አስተምሮ በግድ የሚጭንበት ፣ እንዲሁም በቅርቡ በወረዳዎች ባካሄደው ምርጫ ካድሬዎቹን በሙስሊሙ ላይ የሾመበትን ሁኔታ ለ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመግታት አዲስ ስልት መቀየሱን አስታውቋል። እስካሁን በተደረገው መብትን ...
Read More »በኢህአዴግ ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን ሊመሰርቱ አልቻሉም
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኢህአዴግ ባለስልጣን ለኢሳት እንደተናገሩት ኢህአዴግ የድርጅቱን አባላት የአመለካከት መዛባት ለማጥራት በሚል ከክልል ጀምሮ ግምገማ የጀመረ ሲሆን፣ ግምገማውን ወደ ወረዳ ለማድረስ ማቀዱም ታውቋል። በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ አመለካከት እየተጣራ ፣ አዲሱን የጠቅላይ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት አይቀበሉም የተባሉትን ለማግለል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። በድርጅቶች መካከል በተነሳው አለመግባባትም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ...
Read More »በአዲስ አበባ በተካሄደ የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ አንድም ኢትዮጵያዊ አለመሳተፉ ተዘገበ
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው ፤በአዲስኢትዮጵያውያን ያልተሳተፉበትን የኢንቨስትመንትኮንፈረንስ ያዘጋጁት አበባ የተካሄደውንና ፤ተቀማጭነቱ በስፔን የሆነው ሲንጉላ ሪስ አድቫይዘርስ የተባለ ኩባንያ – “ዋይ.ኤች.ኤም ኮንሰልቲንግ” ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው። ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት በሒልተን ሆቴል በተካሄደው የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ አንድም የኢትዮጵያ ኩባንያ አልተሳተፈም። በጣም አስገራሚው ነገር ፤ስብሰባው የተዘጋጀው ኢትዮጵያን ጨምሮ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቻቸው ገንዘብ የሚፈልጉ የአፍሪካ ኩባንያዎችን ከአውሮፓና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከመጡ ...
Read More »የእስራዔል መንግስት 237 “ፈላሻ ሙራዎችን” ከኢትዮጵያ መውሰዱን አስታወቀ
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “የእርግብ ክንፍ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚሁ ዘመቻ ከተጓጓዙት ፈላሻ ሙራዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ሕፃናት ሲሆኑ፣ እስከ ሕዳር 2006 ዓ.ም ድረስ ተጨማሪ 2000 ቤተ እስራኤላውያንን ከጎንደር ለመውሰድ እቅድ እንደያዘ የ የእስራኤል መንግስት ይፋ አድርጓል።፣ ለነኚሁ ተጓዦቹ ማረፊያ ይሆን ዘንድም፣ አስፈላጊው ነገር የተሟላለት 16 የመጠለያ ጣቢያ ነጂቭ በረሃ ላይ መዘጋጀቱ ታውቋል። በእስራኤል ከሚኖሩት ...
Read More »በማረቃ ወረዳ የየኔሰው ገብሬ ጓደኛ የሆነው ወጣት ራሱን በአደባባይ ሰቀለ
ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል የሜዳሊያ ተሸላሚ የነበረው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም ራሱን በአደባባይ ለመስቀል የተገደደው በአካባቢው ያለውን የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ እጦት በመቃወም መሆኑን ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ለኢሳት ገልጠዋል። በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ፣ በዳውሮ ዞን ፣በማረቃ ወረዳ ፣ በዋካ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም፣ በ1980 ዓም ነበር የተወለደው ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን 3 ...
Read More »