.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ሀማድ ቢን ጃቦር አልታህኒ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል ። አቶ መለስ ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የ ካታር መንግስት የኤርትራን መንግስትና የመንግስትን ተቃዋሚዎች እንዲሁም አልሸባብን ይረዳል በሚል የዲፕሎማሲው ግንኙነት እንዲቋረጥ አድርገው ነበር። በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ውዝግብ ...

Read More »

በውጭ አገር የሚገኘው ሲኖዶስ አዲስ ፓትሪያርክ ለመሾም የሚደረገው እንቅስቃሴ ተቀባይነት አይኖረውም አለ

ጥቅምት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሲኖዶሱ ” በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  የሚመራው ህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ 34ኛው መደበኛ ጉባኤ መግለጫ” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ የቤተክርስቲያንን ሰላምና አንድነት፣ በተለይም ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ መንበራቸው ስለሚመለሱበት ሁኔታ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው መነጋገራቸውን ጠቅሷል። በመግለጫው” በአዲስ አበባ ያሉት አባቶች ቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ ...

Read More »

የለገጣፎ ለገዳዲ ነዋሪዎች ትናንት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የጦፈ ክርክር አደረጉ

ጥቅምት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኘው የገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ነዋሪዎች ትናንት ባካሄዱት ስብሰባ በአካባቢያቸው ስለሚፈጸመው ሙስና ከአካባቢውና ከክልል ባለስልጣናቱ ጋር ክርክር አካሂደዋል። ከ1000 በላይ ተሰብሰባዎች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ህብረተሰቡ በአካባቢው ስለሚካሄደው የመሬት ዝርፊያ ብሶቱን እያወጣ አሰምቷል። በስብሰባው ላይ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ” 90 በመቶ የሚሆነው የአካባቢው ህዝብ ካርታ ሳይሰጠው፣ ከ 18 ሺ የሚደረስ ካርታ ...

Read More »

የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የንግድ ሚኒስቴር በአግባቡ አያስተናግደንም አሉ

ጥቅምት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች አዲስ አበባ ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የንግድ ሚኒስቴር በአግባቡ እየተስተናገዱ እንዳልሆነ ቅሬታቸውን ገለጹ፡፡ ጥቅምት 30 ቀን ድረስ መከፈል ያለበትን የዘንድሮ የግብር ግዴታ ለመወጣት ካዛንቺስ ወደ ሚገኘው የንግድ ሚኒስቴር ማምራታቸውን የጠቀሱት አንድ አስተያየት ሰጪ እዚያ ባዩት መስተንግዶ በጣም መደንገጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በየዓመቱ የግብር መክፈያ መጠናቀቂያ ወቅት ሲቃረብ ሰዎች በብዛት መምጣታቸው የተለመደ ...

Read More »

ባለውለታዎችን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት በሚል የታሰበው የሸልማት ፕሮግራም ከወዲሁ እየተተቸ ነው

ጥቅምት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ከተማ የተመሰረተበትን 125ኛ ዓመት ክብረ በዓል በማስመልከት ባለውለታዎችን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት በሚል የታሰበው የሸልማት ፕሮግራም ከወዲሁ እየተተቸ ነው፡፡ የአስተዳደሩ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ በውድድር እና ያለውድድር ባለውለታ የሆኑ ሰዎችን ለመሸለም ያቀደ ሲሆን ሸልማቱን ለመስጠት የተቀመጡት መስፈርቶች በአመዛኙ ፓለቲካዊ መሆናቸው ትችትን አስከትሎበታል፡፡ በእቅዱ መሰረት ባለፉት ዓመታት በልማት፣በሥራ ፈጠራ፣ በዴሞክራሲ፣በመልካም አስተዳደር፣በፍትህ፣ በጸጥታ ...

Read More »

የኦፌዴንና የኦብኮ ፓርቲ አመራሮች ጥፋተኞች ተባሉ

ጥቅምት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ ( ኦፌዴን)ና የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ፓርቲ አመራሮች ጥፋተኞች ተባሉ በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና የኦሮሞ ህዝበ ኮንግረስ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኦልባና ሊሌሳ ከሌሎች 9 የኦሮሞ ተወላጆች ጋር በመሆን በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል። ፍርድ ቤቱ ለአቶ በቀለና አቶ ኦልባና ...

Read More »

በደብረብርሐን ዩኒቨርስቲ የታሰሩ ተማሪዎች አልተፈቱም

ጥቅምት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት ከውጤት ጋር በተያያዘ በደብረብርሀን ዩኒቨርስቲ ተቀስቅሶ በነበረው የተማሪዎች ተቃውሞ የታሰሩ ከ50 ያላነሱ ተማሪዎች አለመፈታታቸው ታውቋል። ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ተማሪዎችና አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጡት ተማሪዎቹ ፣ የታሰሩ ጓደኞቻችን እስካልተፈቱ ድረስ ትምህርት አንጀምርም በማለታቸው ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ትምህርት አልተጀመረም። በትናንትናው እለት የዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት የተማሪዎችን ተወካዮች በመሰብሰብ የውጤት አሰጣጡ መመሪያ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውአቸውን አሰሙ

ጥቅምት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 11 ወራት ድምጻችን ይሰማ በማለት የመብት ጥያቄዎችን ያነሱ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውሞአቸውን አሰምተው ውለዋል። ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ተቃውሞአቸውን የገለጡት ነጭ ጨርቅ በማውለብለብና በዝምታ ሲሆን፣ የነጩ ጨርቅ ትርጉሙ በእስር ላይ የሚገኙት መሪዎቻቸው አሸባሪዎች ሳይሆኑ የሰላም ምልክቶች መሆናቸውን ለመግልጽ  መሆኑ ታውቋል። ተቃውሞዓቸውን በዝምታ ያደረጉትም መሪዎቻቸው ህገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩ ይህሊና እስረኞች መሆናቸውን ለመግልጽ ነው ...

Read More »

በትንሹ ሰባሁለት ኢትዩጵያዊያን ስደተኞ ሞቱ ተባለ

ጥቅምት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትንሹ  72  ኢትዩጵያዊያን  ስደተኞች  ከሶማሊያ  ቦሳሶ  ወደብ  ወደ የመን  ለመግባት ሲሞክሩ  ባህር ውስጥ  ሰጥመዋል  ሲሉ  የየመን  ባለስልጣኖች አስታወቁ ። የተወሰኑ  የ ኢትዮጵያውያኑን  አስከሬን  በፎቶ  አስደግፎ  የተሰራጨው  ይሕ ዘገባ  እንዳመለከተው  በሁለት ጀልባ ተጭነው  በገልፍ-ኦፍ  ኤደን ባህር ወደየመን  በማምራት  ላይ እያሉ  ነው  በተነሳ  ሀይለኛ  ንፋስና  ማዕበል አስጥሞአቸው  የከፊሉ  አስከሬን  በየመን  ሰላጤ  አካባቢ  የተገኘው  ። ከ ኢትዮጵያ  በየጊዜው  የሀገሪቱን  የፖለቲካና  የ ኢኮኖሚ  ቀውስ  በመሸሽ ወደ  የመን  በባህር  የሚመጡ  በሺዎች  የሚቆጠሩ  ኢትዮጵያውያን  ለተመሳሳይ አደጋ  እንደተዳረጉና  እንደሚዳረጉ   ይኸው  ዘገባ  አመልክቶዋል። የየመን  የሀገር  ውስጥ  ሚኒስትር  አብዱል-ቃድር  ከታን  ዋቢ  ያደረገው ዘገባው የመን  በየጊዜው  የሚፈልሱትን  ኢትዮጵያዊ  ስደተኞች  ለመግታት  በቅርቡ  ጥብቅ  እርምጃ  እንደምትወስድ  አስታውቀዋል  ብሎዋል ። የተባበሩት  መንግስታት  ምንጮች  እንደሚየመለክተው  በ የአመቱ  75 000 ኢትዮጵያውያን  ስደተኞች  ገልፍ-ኦፍ  ኤደንን  ይሻገራሉ  ወይም  ለመሻገር ይሞክራሉ ።

Read More »

በደብረብርሀን ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰ ግጭት ተማሪዎች መጎዳታቸው ተሰማ

ጥቅምት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት ጥቅምቅ 21 ቀን 2005 ዓም በደብረብርሀን ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ያወጣውን አዲስ የውጤት አሰጣጥ ደንብ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አድረገዋል። ተማሪዎች ጥያቄያቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት፣ የወረዳው ፖሊስ አባላት ወደ ዩኒቨርስቲው ገብተው አስለቃሽ ጭስ በመበተን ተማሪዎችን ደብድበዋል። ተማሪዎቹ እንዳሉት መብታቸውን ተጠቅመው  ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት ግን ጥያቄያቸውን በቅንነት ከመመለስ ይልቅ ዛቻና ማስፈራሪያ መጠቀማቸውን ተማሪዎች ...

Read More »