ህዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደውንና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ውይይት አስመልክቶ በስፍራው በመገኘት ያጠናቀረው ፕሮግራም ያለአግባብ ተለውጦ እና ተቆራርጦ ለሕዝብ እንዲቀርብ መደረጉን አስታወቀ። ሰንደቅ ጋዜጣ ይህንኑ አስመልክቶ ዛሬ እንደዘገበው፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መንገሻ በዋናነት በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት እና በሙስና ችግሮች ላይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ ተዘረፈ
ህዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአሁኑ ዝርፊያ ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት አጥቷል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአይቲኤስሲ ላብራቶሪ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ ተዘረፈ፡፡ ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ለሁለተኛ ጊዜ ሰሞኑን የተዘረፈው የ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንስቲትዩቱ ላብራቶሪ እጅግ በጣም ውድ የሆኑ፣ የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች ያካተቱና በብዙ ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ንብረቶቹን አጥቷል። ዝርፊያው የተፈፀመው ...
Read More »በዓለማችን የሠራተኞች መብት ከሚጣስባቸው ዋነኛ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ ተገለፀ
ህዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ዓለም-አቀፉ የስራ ድርጅት ወይም ILO ኢትዮጵያ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ባግባቡ ከማይከበርባቸው የዓለማችን አገሮች ከዋነኞቹ ረድፍ የምትመደብ መሆኗን አስታወቀ። ድርጅቱ ይህንኑ አስመልክቶ ሰሞኑን ያወጣው ሪፖርት እንደሚጠቁመው አርጀንቲና፣ ካምቦዲያ፣ ኢትዮጵያ፣ ፉጂ እና ፔሩ የሰራተኞችን መብት የሚጣስባቸው የዓለማችን አገሮች ናቸው በማለት ይኮንናቸዋል። ድርጅቱ ለዚህ እንደምሳሌ የጠቀሰው በገዥው ፓርቲ ጣልቃ ገብነት ዳግም የተቋቋመውን ተለጣፊውን የኢትዮጵያ ...
Read More »አንድ ኢትዮጵያዊ በእቃ መጫኛ ኮንቴነር ውስጥ ተደብቆ ጀርመን ገባ
ህዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ፍራንክፉርተር ሩድስካው የተባለው የጀርመን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፈው ቅዳሜ የ23 አመቱ ወጣት የተለያዩ ኮንቴነሮችን በጫነው አውሮፕላን ውስጥ ተደብቆ፣ ለ9 ሰአታት ከበረረ በሁዋላ በሰላም ጀርመን ግብቷል። ወጣቱ በቦሌ አየር ማረፊያ የሎጂስቲክስ ሰራተኛ የነበረ ሲሆን በአውሮፕላኑ ውስጥ ያለውን ቅዝቃዜ ተቋቋሙ በደህና መግባቱ አስገራሚ መሆኑን ጋዜጣው ገልጿል። ወጣቱ ለጀርመን መንግስት የስደተኝነት ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ...
Read More »ህወሀት በከፍተኛ ወጪ በትግራይ ያካሄደው ስብሰባ ውጤታማ አልሆነም ተባለ
ህዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ከ 160 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ በትግራይ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ሰሞኑን ያደረገው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ህዝባዊ ስብሰባ የታሰበውን ውጤት ሊያስገኝ አልቻለም ተባለ። በስፍራው የሚገኘው የ ኢሳት ወኪል እንዳደረሰን መረጃ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት በሁዋላ አብዛኛው ህዝብ አሁን በቀሩት ባለስልጣናት በራስ መተማመን እያጣ መምጣቱን ያመለክታል። ከህብረተሰቡ እየተሰሙ ...
Read More »የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽነር ከእስር ተለቀቁ
ህዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከወራት በፊት በጋምቤላ በተገደሉትን 19 ተማሪዎች እና በሳውዲ ስታር ሰራተኞች ላይ በተፈጸመ ጥቃት እጃቸው አለበት ተብሎ ለወራት በእስር ላይ የነበሩት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ግለሰብ ከእስር ተለቀዋል። ኮሚሺነሩ ከእስር የተለቀቁበት ምክንያት ግልጽ አይደለም የሚለው የጋምቤላ ዘጋቢያችን በአሁኑ ጊዜ በመዘጋጃ ቤት ውስጥ ስራ ተሰጥቷቸው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ጋምቤላ አሁንም ሙሉ በሙሉ ተረጋግቷል ብሎ ...
Read More »በጀርመን የሚገኘው የአብያተ-ክርስቲያናት ጉባኤ የጀርመን መንግስት ዋልድባን እንዲታደግ ጥሪ አቀረበ
ህዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአባያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የጀርመን የልማት ሚኒስትር ለሆኑት ለሚ/ር ዲሪክ ኔቢል በጻፉት ደብዳቤ ዋልድባ በአለም ላይ እጅግ ውድቅ የሆኑ ቅርሶችን የያዘና ለዘመናት ተጠብቆ የቆየ በመሆኑ፣ የጀርመን መንግስት ይህን ገዳም እንዲታደግ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቋል። ለሚኒሰትሩ የቀረበው ጥያቄ በጀርመን ጋዜጦች ላይ ታትሞ ወጥቷል። የኢትዮጵያ መንግስት በዋልድባ ዙሪያ ላይ የሚያካሂደው የሸንኮራ ልማት፣ ለገዳሙ ህለውና ስጋት ነው ...
Read More »የኢትዮጲያ ሙስሊሞች በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የእስር ቤት ጉብኝት ወይም ጥየቃ ትላንት ተካሄደ
ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጲያ ሙስሊሞች በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የእስር ቤት ጉብኝት ወይም ጥየቃ ትላንት ተካሄደ ከአዲስ አበባ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ከ ፲፻ ሺህ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች በእስር ላይ የሚገኙትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ለመጠየቅ እንዲሁም ትግላቸው ሰላማዊ መሆኑን ደግሞ ለማመሳከርና ለታሰሩት ድጋፍ ለማሳየት ወደ ቃሊቲ አምርተዋል። በእለቱ ከአራቱም የአዲስ አበባ አቅጣጫዎችን ከአጎራባች መንደሮች ወደቃሊቲ ...
Read More »ለኢትዮጲያ መንግስት የሚያገለግሉ የፌደራል ፓሊስ አባላት ከዱ
ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢትዮጲያ መንግስት የሚያገለግሉ የፌደራል ፓሊስ አባላት እየከዱ መሆናቸውን እንዲሁም በሁመራና በመተማ ወታደራዊ ግጭቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን አንድ የፌደራል ፓሊስ ሃላኢ ገለፁ። ይህም በምስልና በድምፅ ይፋ ሆኗል። በሌላምበኩል በሰሜን ኢትዮጲያ ጠረፋማ አከባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አንዱ የሆነው ትሕዴን ሰራዊቱን በክፍለ ጦር ደረጃ ማዋቀሩን ለቀመንበሩ ለኢሳት ገልፀዋል። በምስራቅ ኢትዮጲያ በኦጋዴን አከባቢ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ሰብስበው ገለፃ ...
Read More »የሕውሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደገና ስብሰባ መቀሌ ላይ መቀመጡ የታወቀ ሲሆን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ስብሰባው መጠናቀቁን አስታውቀዋል
ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደገና ስብሰባ መቀሌ ላይ መቀመጡ የታወቀ ሲሆን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ስብሰባው መጠናቀቁን አስታውቀዋል። ከቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት ወዲህ ሳምንታት እየቆጠረ የቀጠለው የኢሕአዲግ አባል ፓርቲዎች በተለይም የሕወሃትና ኦሕዴድ ሥብሰባ መቋጫ አለማግኘቱንም የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ(ሕወሃት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሕዳር ፭ እስከ ፯ ባካሄደው ስብሰባ ...
Read More »