ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ በጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሄቴል በዚህ አመት በሚደረገው የአካባቢ እንዲሁም የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ ምርጫ የግዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የውይይት መድረክ መጥራቱን ጠቅሰዋል። ድርጅቶቹ በመግለጫቸው ” ምርጫ ለማካሄድ ነባራዊ ሁኔታው የማይፈቅድ ስለሆነ በፖለቲካ ምህዳሩና በህዝብ ወሳኝነት ሁሪያ መወያየት አለብን ብለን ፒቲሺን ተፈራርመን ለቦርዱ ያስገባን 33 ፓርቲዎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ባለፉት 6 አመታት ሩብ ሚሊዮን ኢትዮጵያን ወደ አረብ አገራት ተሰደዋል
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የሚዲያ ዊዝ ኮንሳይስ ዋና አዘጋጅ ግርሀም ፔብልስ ባወጣው ጽሁፍ እንዳመለከተው ባለፉት 6 ዓመታት 250 ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ አረብ አገራት ተሰደዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞችን ኮሚሽን በመጥቀስ ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ በዚህ አመት 85 ሺ አትዮጵያውያን በመንገድ ላይ የሚያጋጥማቸውን አስቸጋሪ ሁኔታ ተቋቁመው የመን ገብተዋል። በየመን ከሚደርሱት ስደተኞች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች የኦነግና የኦብነግ አባላት ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ ጥያቄ አቀረቡ
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-16 የ አውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በፃፉት ግልጽ ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንዲፈታ ጥያቄ አቀረቡ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ አረብ አለም አብዮት በ ኢትዮጵያ ሊከሰት የሚችልበት ዕድል ሰፊ ስለመሆኑ በድረ ገጾች በመጻፉ ሳቢያ የስብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት የ 18 ዓመት እስራት እንደተወሰነበት የጠቀሱት የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላቱ፤ ይህም አልበቃ ...
Read More »ዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ስርአት መለወጥ አለበት አለ
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ስርአት ካልተለወጠ፤ የኢትዮጵያ እድገት ግቡን መምታቱ አጠራጣሪ ነው ሲል የዓለም ባንክ አስጠነቀቀ። የዓለም ባንክ ባለፈው ሳምንት በሂልተን ሆቴል በለቀቀው፤ “ሁለተኛ ደረጃ ት/ት በኢትዮጵያ፤ እድገትና ለውትን ለማገዝ” (Secondary Education in Ethiopia: Supporting Growth and Transformation ) የተሰኘ ጥናት እንደገለጸው፤ ኢትዮጵያ የጠቅላላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ስርአቷና ካላሻሻለች፤ በ2025 መካከለኛ የምጣኔ ሀብት (ወይም ኢኮኖሚ) ወዳላቸው ...
Read More »በአዲግራት የሙስሊሞች መቃብር እየፈረሰ ነው
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክ/ሀገር በአዲግራት ከተማ የሙስሊሞች መቃብር ፈርሶ አጽሞች በብዛት ባንድ ጉድጓድ እንደገና እንዲቀበሩ እየተደረገ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስረዳ። እርምጃውን የወሰደው የከተማው አስተዳደር በቅርቡ ከተመረጡት የመጅሊስ ተወካዮች ጋር በመሆን እንደሆነ ከስፍራው ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል። ኢሳት ከስፍራው ያናገራቸው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ እንደተናገሩት ከሆነ፤ ከመቃብር ስፍራው ወደ 3000 የሚጠጉ አጽሞች የሚነሱ ሲሆን፤ በስፍራው በሺሆች የሚቆጠሩ ፖሊሶች ...
Read More »ውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአቶ ሀይለማሪያምን ንግግር አስተባበለ
ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለአልጀዚራ የሰጡትን ቃለ ምልልስ በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማብራሪያ ሰጡ። የኢትዮጲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድረ-ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ የአቶ ሀይለማሪያም ቃለምልልስ በተዛባ መንገድ በስፋት እየተሰራጨ መሆኑን ገልጾ፤ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ያለውን ግንኙነት በተመለከተ የተደረገ የፖሊሲ ለውጥ አለመኖሩንም አብራርቷል። የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔውን ከሰጠበት እ/ኤ/አ ህዳር 2004 ጀምሮ የኢትዮጲያ መንግስት የያዘው አቋም የማይለወጥና የጸና ሆኖ መቀጠሉን ያመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማብራሪያ፤ አቶ ኃይለማሪያም የተናገሩት በአቶ መለስ ሲገለጽ የቆየና አዲስ ነገር አለመሆኑንም አክሎ ገልጿል። አቶ ሃይለማሪያም አቶ መለስ ከተናገሩት የተለየ ነገር ያስቀመጡት ወደ አስመራ እሄዳለሁ ማለታቸውን ብቻ ነው ሲልም ...
Read More »በአርባ ምንጭ ሰራተኞች ያላግባብ እየተባረርን ነው አሉ
ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ጥያቄና ተቃውሞ ስላነሱ ከስራቸው አየተፈናቀሉ መሆኑን ሰራተኞቹ ከአርባ ምንጭ ገለጹ። ፋብሪካው አቶ ሙስጠፋና አቶ አስራት ወደተባሉ ሁለት ኢትዮጵያዊያንና አንድ ቻይናዊ ባለሀብቶች ከተላለፈ በኋላ፤ ካለፈው አመት ግንቦት ወር ጀምሮ 200 ሰራተኞች በመባረርና በተለያየ ጫና ከስራ እንደለቀቁ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አብዛኞቹ ሰራተኞች የተባረሩት በአሰሪዎቹ እንደሆነ ታውቋል። ሰሞኑንም ስብሰባ ላይ ...
Read More »የአሜሪካን ኬነቲከት ግዛት ሟቾች ቀብር እየተፈጸመ ነው
ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው አርብ በኬነቲከት ግዛት ኒውስታውን ከተማ በሳንዲ ሁክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከተገደሉት 26 ህጻናት መካከል፤ የሁለቱ የቀብር ስነ-ስርአት ዛሬ እንደሚፈጸም ታወቀ። አዳም ላንዛ በሚባል የ20 አመት ወጣት የተገደሉትን ወጣቶች አስመልክቶ በትናነትናው እለት በኒውስታውን ከተማ በተደረገው የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ፤ ፕሬዚዳንት ኦባማ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። ግድያው በተፈጸመበት አርብ እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንባ እየተናነቃቸው ሀዘናቸውን የገለጹት ...
Read More »ከፍተኛው ፍርድቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ ብይን ሰጠ
ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ አቶ አቡበክር የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል በተከሰሱት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ብይን ሰጥተዋል። ችሎቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ እና ታሳሪዎች ወደ ማረሚያ ቤት እስኪመለሱ ድረስ ከልደታ እሰከ ኮካ ኮላ ድረስ ያለው አካባቢ በመላ በፌደራል ፖሊስ ተወጥሮ ነበር። ፍርድ ቤቱ ከቀረቡት ክሶች ውስጥ መንግስትን ...
Read More »የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ መማረራቸውን ገለጹ
ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሞት ከተለዩ ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በየመድረኩና በመንግስት መገናኛ ብዙሃን “የመለስን ራዕይ እናሳካለን” በሚል የሚነገረው ፕሮፖጋንዳ እጅግ የበዛና አሰልቺ እንደሆነባቸው ያነጋገርናቸው አንዳንድ የአ/አ ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ያሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ወሬያቸው ሁሉ በመለስ ራዕይ ማሳካት ጋር የተያያዘ ከመሆኑም ባሻገር አቀራረቡም ሆነ የድግግሞሹ ብዛት ...
Read More »