.የኢሳት አማርኛ ዜና

አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፓርላማ መቅረቡ ተገለጠ

ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸውና ከኢህአዲግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው የተባረሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፓርላማ መቅረቡ ተገለጠ:: ሪፖርተር ጋዜጣ በሮብ እትሙ የምክር ቤቱ የቅርብ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አቶ ጁነዲን ሳዶ በፓርላማ የስነስርአት ደንብ መሰረት ሊጠየቁበት የሚችል የህግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል በም/ቤቱ አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ም/ቤት እንዲያነ ሳ በመንግስት ...

Read More »

የተቃዋሚ 33 የፓለቲካ ድርጅቶች ያቆቆሙት ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሊከሰው መሆኑን አስታወቀ

ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የምርጫ  ቦርድ ከፍተኛ ሀላፊ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለክልልምምክር ቤት አባልነት ምርጫ መወዳደራቸውንም አጋልጦል:: ጊዜዊ ኮሚቴው ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው 18 ጥያቄዎች ማስረጃ ያላቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ምርጫ ቦርድን ለፓርላማ አፈጉባኤ እንደሚከስ አስታውቆል:: የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረቡት 18 ጥያቄዎች ማስረጃ የላቸውም ብሎ ጥያቄዎቹን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው ወሳኝ ያላቸው ማስረጃዎች ለሀገር ውስጥና ...

Read More »

ሽምግልናውን ሲያካሒድ ከነበሩ አስታራቂዎች የቤተክርስትያን ኣባቶች መካከል ኣንደኛው ከኢትዮጲያ ሲባረሩ ሁለተኛው የደረሱበት ኣይታወቅም

ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኣዲስ ኣበባዎቹ ተደራዳሪ ኣባቶች ባለፈው ሳምንት ያወጡት መግለጫ ተገደው የፈረሙበት መሆኑም ተገለጸ።በቅርቡ በዳካስ ቴክሳስ የረካሄደውን ሶስተኛ ዙር በሶሳንጀለሰ ካሊፎርንያ ለማካሔድ ቀጠሮ ይዘው ከተነሱት ኣባቶች ኣንደኛው የሆኑት ብጹነ ብጹነ ኣቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ኣሁንም በዮኤስ ኣሜሪካ አንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉኣል።ቅዳሜ ታህሳስ 20/2005 ኣሜሪካ የደረሱት ሊቀ ካህናት ኃይለሰላሴ ኣለማየው ታግደው መባረራቸውን ለሾይስ ኦፍ ኣሜሪካ የአማርኛ ...

Read More »

በቡሬ ግንባር የሚገኙ እና በግጭቱ ታስትፈዋል የተባሉ ወታደሮች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ታዘዙ

ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በሰራዊቱ መካከል የተፈጠረውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ከሆኑ በሁዋላ ባለፈው ሀሙስ ከመቀሌ እ             ከአፍዴራ የተንቀሳቀሱ ወታደራዊ አዛዦች በግጭቱ የተሳተፉት ሁሉ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ማድረጋቸው ታውቋል። በእለቱ ከፍተኛ ግምገማ መካሄዱንም ለማወቅ ተችሎአል። በአሁኑ ሰአት አንጻራዊ ሰላም መስፈሩን በአካባቢው የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል። በቡሬ ግንባር ...

Read More »

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት ጉባኤ እንዳናካሂድ ተከለከልን አሉ

ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ብርሀኑ ተግባረእድ እና ምክትል ሊቀመንበሩ ወጣት ሚካኤል አለማየሁ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጉባኤያቸውን ለማዘጋጀት አዳራሽ ፍለጋ ቢንከራተቱም የጸጥታ  ሀይሎች በሚያደርሱባቸው ተጽእኖ ለመከራየት አልቻሉም። ወጣቶቹ በመጪው እሁድ ጉባኤ ለማካሄድ የተከራዩትን አዳራሽ፣ የጸጥታ ሀይሎች ባሳረፉት ጫና ሆቴሉ ፈቃደኝነቱን እንደሰረዘባቸው ገልጸዋል። ሀሳባችንን በነጻነት መግለጽ አልቻልንም የሚሉት ወጣቶቹ፣ ለማን አቤት እንደሚባልም ግራ እንደገባቸው ...

Read More »

በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ

ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ ወረዳ አለንጌ በተባለ ቦታ ጥቃት ፈፀመ

ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ታህሳስ 18 ቀን 2005.ዓ.ም በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አለንጌ በተባለው አካባቢ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ 8 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ኪሳራ ማድረሱን ግንባሩ ገልጿል። ግንባሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መማረኩንም ገልጿል። መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው መልስ የለም። ዜናውንም ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልተቻለም።

Read More »

በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ

ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ...

Read More »

መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ

ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡ ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ ...

Read More »

በአዲስአበባ አቶ መለስን የሚያወድሱ ፖስተሮች እየተነሱ ነው

ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ራዕይህን እናሳካለን”፣“አባይን የደፈረ መሪ”፣“ቃልህን እንጠብቃለን” እና የመሳሰሉ የውዳሴ ቃላት ጋር የአቶ መለስን ምስል የያዙና በውድ ዋጋ የተሰሩ ፖስተሮች አዲስአበባ ከተማን ጨምሮ ክልሎችን ከማጥለቅለቃቸው ጋር ተያይዞ ግንባሩ ባልተለመደ ሁኔታ ግለሰብ ወደማምለክ ደረጃ ማሽቆልቆሉ በራሱ አባላት ጭምር ከፍተኛ ትችትን አስከትሎበታል፡፡ ሰሞኑን በአዲስአበባ በተለይ ከኡራኤል ቤ/ክ እስከ ፍትህ ሚኒስቴር የመኪና መንገድ አካፋይ መሃል ላይ ...

Read More »