ታህሳስ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በከተማዋ በቆሚነት ደርድረውና እያዞሩ ጋዜጣና መጽሄት የሚሸጡ በመከልከላቸው ህዝቡ ጋዜጣ ማግኘት አለመቻሉን የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችና የቅርብ ምንጮች ያላቸውን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቦል:: ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁና በአካባቢው ጋዜጣና መጽሄት በመሸጥ የሚተዳደሩ ወጣቶች የጠቀሰው ዘገባ የከተማዋ ወያኔ ወረዳ ንግድና ኢንዱስትሪ አስተዳደር ስራው ህገወጥ መሆኑ ተገልፆላቸው ከታህሳስ 5፣2005 ጀምሮ በአካባቢው የገል ጋዜጣና መጽሄት የመሸጥ ስራ እንዳይሰራ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አወዛጋቢ መልሶችን ሰጡ
ታህሳስ ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት መልስ በርካታ አወዛጋቢ ነገሮችን ተናግረዋል። በኤርትራ ዙሪያ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለምልልሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተተቹት አቶ ሀይለማርያም በዛሬው ንግግራቸው በተተቹበት ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል። አቶ ሀይለማርያም ” አስመራ እሄዳለሁ ያልኩት በየትኛውም ቦታ እንደራደራለን የሚለውን የመንግስት አቋም አጽንኦት ለመስጠት ነበር” ሲሉ ተናግረዋል። ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ...
Read More »ተማሪዋን አስገድዶ የደፈረው የተማሪዎች ዲን በነጻ ተለቀቀ
ታህሳስ ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ዲን የሆኑት አቶ ናትናኤል ህዳር 27 ቀን 2005 ዓም የሚያስተምሯትን ተማሪ ስልክ በመደወል ከምሽቱ 1፡30 ገዳማ ቢሯቸው ድረስ ካስጠሩ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸሙባት መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ተማሪዎች እንደገለጹት ደግሞ የጸጥታ አካላት እንዲሁም የዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ለፖሊስ ሊተባባሩ ባለመቻላቸው የተማሪዋ ህይወት አደጋ ውስጥ ወድቋል። የተደፈረችው ተማሪ በግሏ ጥረት ወደ ዩኒቨርስቲው ሆስፒታል ...
Read More »በተውለደሬ ወረዳ አንድ ጠበቃ በክርክር በማሸነፋቸው በቀበሌው ባለስልጣናት ተደበደቡ
ታህሳስ ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ በተውለደሬ ወረዳ አቶ አበራ ካሳ የተባሉ ጠበቃ ከቀበሌው ሊቀመንበር ጋር በመሬት ጉዳይ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ክርክር በፍርድ ቤት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ፣ ሊቀመንበሩ ደጋፊዎቻቸውን አስተባብረው ጠበቃው እንዲደበደቡ አድርገዋል፡፡ ጠበቃውም በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ሆስፒታል ገብተዋል። የመሬቱ ባለቤት አቶ አስፋው ሽበሺ የሚባሉ አርሶአደር ሲሆኑ ፣ የቀበሌው 01 እና 02 ሊቀመንበሮች መሬቱን ለግላቸው ለማድረግ ተደጋጋሚ ...
Read More »በኩዌት አንድ ኢትዮጵያዊት ሞታ ተገኘች
ታህሳስ ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አረብ ታይምስ እንደዘገበው ኢትዮጵያዊቷ የሞተቸው ከቀጣሪዋ ድርጅት መስኮት ላይ ዘላ በመውደቅ ሳይሆን አይቀርም። ሰራተኛዋ በራስ ቅሏ አካባቢ ከፍተኛ ደም ፈሷት እንደሞተች የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል። በግቢው ውስጥ ሌሎች ሶስት ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች እንደነበሩ ቢገለጽም ኢትዮጵያውያኑ የቤት ሰራተኛዋ በምን ሰበብ እራሱዋን እንዳጠፋች እንደማያውቁ ገልጸዋል።
Read More »በአማራ ክልል 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀቁ
ታህሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀዋል። ፖሊሶች ስራቸውን መልቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በአንድ ስብሰባ ላይ አምነዋል። ፖሊሶች ስራቸውን የለቀቁት በአስተዳደር ጫና እና ከስራቸው ጋር የማይጣጣም እና የኑሮ ውድነቱን ለማቋቋም የማያስችል ክፍያ ስለማይከፈላቸው መሆኑን ይገልጻሉ። በክልሉ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነት ፖሊሶችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞችን ...
Read More »በደሴ መስኪዶች በሀይል እየተነጠቁ ነው
ታህሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተለያዩ የመንግስት አካላት ከፖሊስ ጋር በመተባባር በደሴ የሚገኙ መስኪዶችን ቁልፎች አዳዳስ ለተመረጡት የመጅሊስ አመራሮች እንዲያስረክቡ ማድረጋቸው ታውቋል። በዛሬው እለት በከተማ የሚገኙ ዋና ዋና መስኪዶች ቁልፎች ለአዳዲሶቹ የመጅሊስ ተመራጮች እንዲረከቡዋቸው ተደርጓል። በተመሳሳይ ዜናም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በሙስሊም መሪዎች ቤት ውስጥ ሆን ብሎ በማስቀመጥ ቪዲዮ እየተሰራ መሆኑንና ቪዲዮውም አመራሮችን ለመክሰስ እንደማስረጃ እንደሚቀርብ ታውቋል። በመንግስት እና ...
Read More »የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ
ታህሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተማሪዎቹ ባለፈው አርብ ምሽት በጀመሩት ተቃውሞ የመማሪያ ክፍሎች መስኮቶች መሰባበራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አረብ ምሽትና ቅዳሜ የፌደራል ፖሊስ አባላት ዩኒቨር ስቲውን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን ገሚሶቹ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተጠልለው እንደነበር ታውቋል። ተማሪዎቹ ተቃውሞአቸውን ያሰሙት አዲሱን የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ በመቃወም እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስላልተሟሉላቸው ነው። በግቢው ውስጥ 2 ሺ ...
Read More »የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ዲን ተማሪዋን አስገድደው ደፈሩ
ታህሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተማሪዎች ዲን የሆኑት አቶ ናትናኤል ህዳር 27 ቀን 2005 ዓ,ም የሚያስተምሯትን ተማሪ ስልክ በመደወል ከምሽቱ 1፡30 ገዳማ ቢሯቸው ድረስ ካስጠሩ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸሙባት ከጎንደር ያገኘነው ዜና ያስረዳል። የተደፈረችው ተማሪ በግሏ ጥረት ወደ ዩኒቨርስቲው ሆስፒታል በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምርመራ ያደረገች ሲሆን የምርመራው ውጤትም ተማሪዋ የአስገድዶ መደፈር ሰላባ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው። ተማሪዋን አስገድደው ...
Read More »የአረና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በዶዘር ፈረሰ
ታህሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሁመራ የሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት በዶዘር እንዲፈርስ ከተደረገ በሁዋላ የድርጅቱ ጽህፈት ቤትም ተዘርፎአል። በተመሳሳይ መንገድም የድርጅቱ አባል የሆኑት የአቶ ገብረእግዚ ናዩ ቤት ያለምንም ማስጠንቀቂያ እንዲፈርስ ተደርጓል። በተንቤን የድርጅቱ አባል የሆኑት አቶ ጸጋየም መታሰራቸው ታውቋል። በአቶ ገብሩ አስራት በሚመራው አረና ፓርቲ ላይ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የሚወስዱት እርምጃ እየከፋ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።
Read More »