ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም ከ 20 ያላነሱ ሰዎች ታስረው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። አብዛኞቹ ወጣቶች ወደ ማይጨው እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል አቶ አባተ ያለው እስከ ልጃቸው፣ አቶ አሰፋ ዳርጎ ከሴት ልጃቸው ጋር ፣ ሽበሺ አለሙ፣ አሰፋ አሰግድ ፣ ውዱ ቸኮል፣ አቶ ዝናቡ ቸኮል ከሴት ልጃቸው ጋር እንዲሁም አቶ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ቴዲ አፍሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ ለመስጠት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያመራ ነው
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሙዚቃው ለማነቃቃትና ለመደገፍ በመጪው ቅዳሜ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያመራ ቢቢሲ ዘገበ። ከአርቲስቱ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረገው ቢቢሲ ፊከስ ኦን አፍሪካ፤ ቴዲ አፍሮን፦ “የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ልጅ የሆነ ድንቅ የፖፕ ስታር ሙዚቀኛ” ብሎታል። ቀደም ሲል ባለለፈው የእስር ጊዜ እና በአዲሱ አልበሙ ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ...
Read More »በኦስትሪያ ዜጋ ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው ከተረጠሩት መካከል ሁለቱ መያዛቸውን መንግስት አስታወቀ
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው ተጠርጣሪዎቹ በአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። ወንጀሉ ተራ የዘረፋ ሙከራ መሆኑን መንግስት ይናገራል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ድርጊቱን መፈጸማቸውን ይናገራሉ። የሟቹ አስከሬን ከትናንት በስቲያ ወደ ሀገሩ መላኩ ታውቋል።
Read More »በአላማጣ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ታሰሩ
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከተማዋን የወረሩዋት የፌደራል ፖሊሶች ተቃውሞውን አስነስተዋል በማለት የጠረጠሩዋቸውን ሰዎች ይዘው በማሰር ላይ ናቸው። ወጣቶችን ጨምሮ በከተማዋ እና በዙሪያ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች የሚታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ታስረዋል። ወረዳው ባለስልጣናትን ህዝቡን ለማነጋገር ስብሰባ መጥራታቸውም ታውቋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በነገው እለት መንግስት የሚያቀርበውን አማራጭ በመስማት ምናልባትም ተመሳሳይ ተቃውሞ ሊካሄድ ይችላል። ተማሪዎች ዛሬ ትምህርት አለመጀመራቸውን ...
Read More »ልጃቸው በፖሊስ ኮማንደር የተገደለባቸው አባት ከሆስፒታል ወጥተው በወቅቱ ስለተፈጠረው ድረጊት ተናገሩ
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ታህሳስ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ልጃቸው በፖሊስ ኮማንደር የተገደለባቸው አባት ከሆስፒታል ወጥተው በወቅቱ ስለተፈጠረው ድረጊት ተናገሩ በጌዲዮ ዞን በዲላ ከተማ ኮማንደር ግርማ በየነ የተባለ የዞኑ የፖሊስ የሰው ሀብት ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ ከ10 ቀናት በፊት አንድ የ14 አመት ታዳጊን ወጣት በሽጉጥ ገድሎ አባቱን ደግሞ ማቁሰሉን መዘገባችን ይታወሳል። የማቹ አባት አንገታቸው አካባቢ በመመታታቸው ...
Read More »የዋጋ ንረቱ መቀነሱን ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ::
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ባሳላፍነው ወር የነበረው የዋጋ ግሽበት ወደ 12 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማለቱን የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል። አሀዙ ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በ1 ነጥብ ሁለት መቀነሱን ኤጀንሲው አስታውቋል። ይሁን እንጅ በምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ግሽበቱ ጭማሪ አሳይቷል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ8 ወራት በፊት ሰኔ ወር ላይ ባደረጉት ንግግር የዋጋ ...
Read More »አርቲስቶች በየካቲት ወር ለሚከበረው የመከላከያ ቀን ቅስቀሳ ጀመሩ
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአርቲስ ሰራዊት ፍቅሬና ሙሉአለም ታደሰ የሚመራው ግብረሀይል ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከቲያትሪካል አርት ተማሪዎች ገር ተገናኝቶ ስለመከላከያ ቀን አከባበር ውይይት ማድረጉ ታውቋል። የኔነሽ ወልደገብሬልና ሌሎችም አርቲስቶች በስፍራው መገኘታቸውን የዩኒቨርስቲ ዘጋቢያችን ገልጿል። አርቲስቶች በቅርቡ የአትዮጵያ አየር ሀይልን ጨምሮ የመከላከያን ኢንጂነሪንግን እንዲጎበኙ መደረጋቸው ይታወቃል። የጉብኝቱ አላማ አርቲስቶቹ በመጪው የመከላካያ ቀን በአል አከባበር ላይ ከፍተኛ ...
Read More »በጋዜጠኛ አበበ ገላው ላይ ታቅዶ የነበረውን የግድያ ሴራ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አወገዙ
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ላይ ሊቃጣ የነበረውን የግድያ ወንጀል ተከትሎ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩ የመንግስት ሰላዮችን ለማጋለጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጠው መነሳታቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቃል። “በአበበ ገላው ላይ ሊሰነዘር የነበረው የግድያ ወንጀል በኤፍቢአይ መርማሪዎች መክሸፉ ቢያስደስተንም፣ በስደት፣ ዲሞክራሲና ነፃነት በሰፈነበት አገር ወያኔዎች እንዲህ አይነት አስከፊ ወንጀል ለመፈፀም ማሰባቸው ...
Read More »በፓሪስ ሶስት የኩርድ አማጽያን አባላት ተገደሉ::
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ግድያው የተፈጸመው ሀሙስ ጧት ሲሆን ሶስቱም ግንባራቸው ላይ በጥይት ተመትተዋል። ከማቾቹ መካከል አንደኛዋ የኩርድ የሰራተኞች ፓርቲ መስራች ናቸው። ሳኪና ካንዚስ የተባለችዋ ሟች ፒኬኬ በአውሮፓ ውስጥ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ቁልፍ ሰው እንደነበረች ዘገባዎች ያመለክታሉ። በሶስቱ ሴት ታጋዮች ላይ የተፈጸመው ግድያ የቱርክ መንግስት በእስር ላይ ከሚገኘው የፒኬኬ መሪ አብደላ ኦቻላን ጋር ንግግር በጀመረ ማግስት ነው። ...
Read More »በፓሪስ ሶስት የኩርድ አማጽያን አባላት ተገደሉ::
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ግድያው የተፈጸመው ሀሙስ ጧት ሲሆን ሶስቱም ግንባራቸው ላይ በጥይት ተመትተዋል። ከማቾቹ መካከል አንደኛዋ የኩርድ የሰራተኞች ፓርቲ መስራች ናቸው። ሳኪና ካንዚስ የተባለችዋ ሟች ፒኬኬ በአውሮፓ ውስጥ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ቁልፍ ሰው እንደነበረች ዘገባዎች ያመለክታሉ። በሶስቱ ሴት ታጋዮች ላይ የተፈጸመው ግድያ የቱርክ መንግስት በእስር ላይ ከሚገኘው የፒኬኬ መሪ አብደላ ኦቻላን ጋር ንግግር በጀመረ ማግስት ነው። ...
Read More »