ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በቢዝነስ ዜናዎች ላይ እያተኮረ አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ 37፡6 ከመቶ ደኖን አታለች:: በሀገሪቱ ያለው እንጨትን በማገዶነት የመጠቀም ፍጆታ በአመት 50 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያመለከተው ይህ ዘገባ የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ ጠቅሶታል:: ይህም ሀገሪቱ ከምትጠቀመው አጠቃላይ ሀይል 80 ከመቶውን ከእንጨትና ከእንጨት ውጤቶች መሆኑ በዘገባው ተመልክቶል:: ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ማህበሩን ለሚቀጥለው አንድ አመት የሚመሩ 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡን አስታወቀ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህ መሰረት ማህበሩ ከተቆቆመበት ጀምሮ ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት በመሩት በዶ/ር ሼክስፔር ፈይሳ ምትክ አቶ አበበ ሀይሉ ም/ፕሬዚዳንት ደግሞ ዶ/ር ሰለሞን ረታ አድርጎ ሠይሞል:: በተዋረድ በዋና ጸሀፊነት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በፋይናንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንትና በመድረክ አስተባባሪነት በቀድሞ የስራ አስፈጻሚዎች ምትክ አዲስ ተመርጦል:: የቀድሞ የማህበሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ለአዲሶቹ ተመራጮች የስራና የንብረት ርክክብ የፈጸሙ መሆኑን የገለጠው የማህበሩ መግለጫ ...
Read More »የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የእስር ቅጣት ከወሰነባቸው ውስጥኬኒያዊው ሀሰን ጃርሶ እንደሚገኙበት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል:: ከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ባህሩ ዳርቻ በኬኒያው ጃርሶ ላይ የ17 ዓመት የ እስርፍርድ ወስነውበታል:: በዚህ ከአሸባሪነት ተግባር ጋር በተያያዘ ክስ በቅድሚያ የተካተቱት 11 ሰዎችእንደነበሩ ሲታወቅ አንደኛው በነጻ ተሰናብቷል ስድስቱ ደግሞ በሌሉበትተወስኖባቸዋል:: የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ አልሸባብ ከተባለውየሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 15 ሰዎች መያዙንማስታወቁን ይህ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል:: በምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጎላ በመምጣበት ጊዜ ነውይህ የፍ/ቤት ውሳኔ የተላለፈው ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን በ2011 ወደሱማሊያ ዳግም መዝመቶንም አስታውሷል::
Read More »የዩናይትድ ስቴት የሴኔት ኣባላቶችን ያቀፈ የልዑካን ቡድን ደቡብ ሱዳን ነዳጆንበኢትዮጵያ በኩል ለተቀሪው ኣለም አንድትልክ ፕሬዝዳንቱን ሳልሻ ኬርን አስጠነቀቁ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሱዳን ትሪቡንን ዋቢ ያደረገው ኦል ኣፍሪካ አንደዘገበው የመሴኔቱ ኣባላቶችየደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬርን ነዳጃቸውን ለኣለም ገበያ ለማቅረብካርቱምን መጠቀምና መጠበቅ አንደሌለባቸው ኣሳስበዋል:: ባለፈው ኣመት ግንቦት ወር የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ሚኒስቴር ስቲፍን ዶ ለዎልስትሪት ጆርናል አንደገለጹት ቢያንስ ቢያንስ የነዳጅ ምርታቸውን 10 በመቶወይም ሰላሳ አምስት ሺ በርሜል በቀን በከባድ መኪና (በቦቴ) ኢትዮጵያንናኬንያን አቆራርጠው በጅቡቲ ለአለም ገበያ ለማቅረብ አቅደዋል:: በዚህ ሳምንት የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን የጎበኙት የአሜሪካ የሴኔት አባላቶች የሰሜን ሱዳን የነዳጅ ዘይት ማጎጎዝን የማስ ፉከራ ትርጉም የለውም ካሉ በሆላ ነዳጃቸውን ለአለም ገበያ ለማቅረብ ከባድ መኪናንና ኢትዮጵያን መጠቀም አለባቸው ሲሉ አስታውቀዋል::
Read More »33ቱ ፓርቲዎች ” በህዝባዊ ንቅናቄ ትግላችንን እንቀጥላለን” አሉ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ የከረሙት 33ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ዛሬ ባወጡት መግለጫ ለምርጫ ቦርድና ለመንግስት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ ” ስለምርጫ ተሳትፎ ማሰብ ‘ ተጨፈኑ ላሞኛችሁን’ መቀበል በመሆኑ በጋራ ይዘን ለተነሳነው ጥያቄ ምርጫ ቦርድም ሆነ ገዢው ፓርቲ ተገደው እንዲሰሙ ለማድረግ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠርና በማስተባበር የተባበረና የተቀናጀ ትግላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል። ፓርቲዎቹ ” ጥያቄያችን ባልተሟሉበት እውነታ ...
Read More »አምባሳደር ስዩም መስፍን ቻይና በአካባቢ ውድመት ላይ የሚቀርብባትን ክስ መከላከል አያስፈልጋትም አሉ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የቻይና አምባሳደር ስዩም መስፍን ከሲሲቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ቻይና በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ማእድናትን በምታወጣበት ጊዜ የአካባቢ ውድመት ታደርሳለች እየተባለ በአፍሪካውያንና በምእራባዊያን ዜጎች የሚደርስባትን ወቀሳ መከላከል አያስፈልጋትም ብለዋል። አምባሳደሩ ይህን መልስ የሰጡት የሲሲቲ ጋዜጠኛ ” ብዙውን ጊዜ አገራችን በሌሎች አገሮች ማእድናትን ስታወጣ የአካባቢውን ህዝቦች ታፈናቅላለች፣ በአካባቢውም ላይ ውድመት ታደርሳለች ...
Read More »20 የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሁንም እንደታሰሩ ነው
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በቅርቡ በድሬዳዋ ከምግብ ጋር በተያያዘ ተነስቶ በነበረው ግጭት ታስረው ከነበሩት መካከል 300 የሚሆኑት ሲፈቱ አሁንም 20 ተማሪዎች ታስረዋል። የዩኒቨርስቲው ምንጮች እንደገለጡት የፌደራል ፖሊስ አባላት በጊዜው በተማሪዎች ላይ ካደረሱት ከፍተኛ ድብደባ በተጨማሪ የተማሪዎችን ሞባይሎች ሳይቀር መወሰዳቸው ታውቋል። በእለቱ በተፈጠረው ችግር ግምቱ ከ150 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ወድሟል። የግጭቱ መንስኤ ከምግብ ...
Read More »በመከላከያ ሰራዊትና በሱሪዎች መካከል የተካሄደው ግጭት ቀጥሎ 3 ሱሪዎች መገደላቸው ታወቀ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በሱሪዎችና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተነሳ ግጭት 3 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በግጭቱ በርካታ የሱሪ ከብቶች መገደላቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ባለፈው ቅዳሜ በአካባቢው ግጭት ተነስቶ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።
Read More »በአዲስ አበባ የባዶ መሬትና የንግድ ቤቶች ሽያጭ ጣራ ነካ
ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ በመንግስት የሚቀርቡ የቤት መስሪያ ቦታና የንግድ ሱቆች ሽያጭ ከግዜ ወደ ግዜ በአስደንጋጭ መልኩ ዋጋቸው እየተሰቀለ መምጣቱን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ የአዲስአበባ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በልደታ ክፍለከተማ የተሰሩ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ጋር ተያይዞ የሚገኙ 150 የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለመሸጥ ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ለአንድ ካሬሜትር እስከ ብር 56 ሺ164 ከ11 ሳንቲም ...
Read More »ምርጫ ቦርድ 33ቱን ፓርቲዎች ጨምሮ ምልክት ያልወሰዱ በምርጫው እንደማይሳተፉ ገለጸ
ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምርጫ ቦርድ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀርበው የምርጫ ምልክቶቻቸውን ያልወሰዱ ፓርቲዎች በሚያዝያው ምርጫ መሳተፍ እንደማይችሉ በይፋ አስታወቀ፡፡ ከ33ቱ ፓርቲዎች መካከል የአንዱ የአመራር አባል የምርጫ ቦርድ እርምጃ 33ቱ ፓርቲዎች ከምርጫው ወጥተናል ከማለታቸው በፊት “አባረናቸዋል” ለማለት የተወሰደ ስልታዊ እርምጃ ነው በሚል አጣጥለውታል፡፡ ቦርዱ ባወጣው ፕሮግራም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች በማዕከል በቦርዱ ጽ/ቤት ተገኝተው የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የሚወስዱበት ጊዜ ህዳር ...
Read More »