ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ በሚካሄደው 50ኛው የአፍሪካ ህ ብረት ስብሰባ ኢትዮጵያ የሊቀ-መንበርነቱን ቦታ እንደምትረከብ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ በህብረቱ አገራት ዘንድ ጥ ያቄ ማስነሳቱ ተዘገበ። የደቡብ አፍሪካ የውጪ ፖሊሲ ኢኒሺየቲቭ (ሳፍፒ) እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበርነቱን ቦታ ከቤኒን እንደሚረከቡ በ ኢትዮጵያ የተሰጠው መግለጫ የህብረቱን ፕሮቶኮል የጣሰ እና ጊዜውን ያልጠበቀ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ የሚገኘው ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ ህዝብን እያነጋገረ ነው
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት አዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጠው አዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ የሆኑትን ምእመናንን እያነጋገረ ነው። ሲኖዶሱ ትናንት ባወጣው መግለጫ በውጭ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር ሲደረግ የነበረው የእርቅ ድርድር ያለውጤት በመጠናቀቁ 6ኛ ፓትሪያሪክ ለማሾም መወሰኑን አስታውቋል። መግለጫው 4ኛው ፓትሪያርክ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ክብራቸውና ደረጃቸው ተጠብቆ በጸሎት ተወስነው እንዲኖሩ ቢሞከረም እንዲሁም ውግዘት ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘ
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እንደ ቢቢሲ ዘገባ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አዲሱ ቦይንግ ድሪምላይነር ለጊዜው አገልግሎት እንዳይሸጥ በአሜሪካ አቪየሺን ባለስልጣን ታግዷል። በመላው ዓለም ላይ 50 የሚሆኑ ቦይንግ ድሪም ላይነር እንዳሉ ያመለከተው የዜና አውታሩ ዘገባ፤የቴክኒክ ፍተሻ እስኪደረግ ድረስ የሁሉም አገራት ቦይንግ ድሪምላይነር ፍላግሺፖች አገልግሎታቸውን እንዲያቆሙ የዩ.ኤስ ፌዴራል አቪየሺን አሳስቧል። አዲሱ ድሪም ላይነር ነዳጅ የመትፋት፣ የኮክ ፒት ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንቱን የሚተካ ሰው ጠፍቷል ተባለ
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ከ3 አመት በፊት የተመረጡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ከተመረጡበት ማግስት ጀምሮ በህመም ምክንያት በስራቸው ላይ ለመገኘት ባይችሉም እርሳቸውን ለመተካት በኦህዴድ ባለስልጣናት መካከል ስምምነት በምጥፋቱ ተተኪ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ አልተቻለም። አቶ አለማየሁ አቶምሳ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ በሁዋላ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚናገሩት በምግብ መመረዝ ሳቢያ በተነሳ ችግር እስካሁን ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ በእስልምና እምነት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንደሚቃወም ገለጠ
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የተደነገጉትን አንቀጾችና የእምነት ነጻነቶችን በመታስ ባለፈው አንድ አመት በእስልምና እመነት ተከታዮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ችግር ፈጥሯል ብሎአል። ፓርቲው አያይዞም የኢህአዴግ መንግስት የሙስሊሞች ተቃውሞ ከሽብር ጋር ይያያዛል በማለት ቢገልጽም እስካሁን በታየው እንቅስቃሴ ጉዳዩ ከሽብር ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የሚታይ ምንም ነገር የለም ብሎአል። ከዚያ ይልቅ በሚያስደንቅና ጥንቃቄ በተሞላበት ...
Read More »የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ባለው የስኳር ፕሮጀክት ዙሪያ ቅሬታቸውን ገለጹ
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጡት ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም አቶ አባይ ጸሐየ ወደ አካባቢው በመሄድ ነዋሪዎችን ማነጋገራቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች በፕሮጀክቱ ደስታቸውን እንደገለጡ ተደርጎ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን የቀረበው ትክክል አይደለም። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የጅንካ ከተማ ነዋሪ እንደገለጡት “አቶ አባይ ጸሀየ ነዋሪዎች ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ የተገባላቸው ቃል ባለመከበሩ ተቃውሞ አስነስተዋል በሚል ምክንያት” ወደ አካባቢው ...
Read More »የአሜሪካ ፌደራል በረራ መስሪያ ቤት በቦይንግ ድሪም ላይነር 787 አይሮፕላን ላይ መርምራ ሊያደርግ ነው
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል መስሪያ ቤቱ ዋና ሃላፊ ሚሸል ሁሬታ አንዳስታወቁት በአውሮፕላኑ ላይ በደረሰው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የአውሮፕላኑን ዲዛይና ኣመራረቱ ምርመራ ይደረግበታል። አውሮፕላኑ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የጃፓን ኣየር መንገድ ቦስተን ላይ ከቶኪዮ ተመልሶ በሚያርፍበት ሰአት እሳት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ባለፈው አርብ የጃፓን ኦል ኒፖን አየር መንገድ ሪፖርት አንዳደረገው በሚበርበት ሰኦት በፓይለቱ በኩል ያለው መስኮት በመሰንጠቁ የመመለሻ በረራውን ...
Read More »ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ልትሆን እንደምትችል ተጠቆመ
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የህብረቱ ሊቀ-መንበር ለማድረግ ኢትዮጵያ ቀደም ካለ ጊዚ ጀምሮ ጥረት ስታደርግ መቆየቷ ተገልጿል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ኢታዮጵያ በመጪው ሳምንት 20ኛውን የ አፍሪካ ጉባኤ ታስተናግዳለች። ከህብረቱ 50ኛ ዓመት የምስረታ በ ዓል ጋት ተጣምሮ ይካሄዳል በተባለው በዚህ ጉባኤ ላይ፤የሁለቱ ሱዳኖች ...
Read More »ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልፁ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ በትናንትናው እለት ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልጸዋል:: መንግስትም አቡነ መርቆሪዎስ መንበራቸው ላይ ተመልሰው ማየት እንደማይፈልግ በአቶ አባይ ጸሀዬ በኩል ግልጽ አቆሙን ያንጸባረቀ በመሆኑ የዕርቁ ጉዳይ ፍጻሜ ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሎል:: በውጭ የሚገኙ አባቶች በዛሬው እለት በሎስ አንጀለስ በጀመሩት ...
Read More »የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ:: በተለይ የቴሌኮም ዘርፉ ለከፍተኛ ሙስና የተጋለጠ መሆኑን አስታወቀ:: ባለፈው አርብ በአለም ባንክ ይፋ የተደረገ ሪፓርት እንዳመለከተው በተለይ በግዥና በአቅርቦት ሂደቶች የሚታዩት ክፍተቶች ለሙስና አደጋ በመጋለጥ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን ሪፓርቱ አመልክቶል:: የሀገሪቱን የሙስና መጠን ላለፉት ስድስት ወራት ሲያጠና የቆየው የአለም ባንክ በተለይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ...
Read More »