.የኢሳት አማርኛ ዜና

መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ከአገር ውስጥ ባንኮች ሊበደር ነው

ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:– የአገሪቱን  ኢኮኖሚና የዜጎችን ኑሮ እየተፈታተነ የሚገኘውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር  ከ እንግዲህ ከአገር ውስጥ አንበደርም ሲል የነበረው የ ኢትዮጵያ መንግስት ዘንድሮ ያጋጠመውን የበጀት ጉድለት መሸፈን ባለመቻሉ  ከ አገር ውስጥ ባንኮች ሊበደር እንደሆነ ሪፖርተር ዘገበ። ለኑሮ ውድነቱ ጣራ መንካት አንዱና ዋነኛው ምክንያት መንግስት ከ አገር ውስጥ መበደሩና ይህንንም ብድር ለማሟላት ብር እንዲታተም ...

Read More »

የጥምቀት በአል ተከበረ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በድምቀት ተከብሯል። በአዲስ አበባ በ ጃንሜዳ ማረፊያቸውን አድርገው የነበሩ ታቦታት አብዛኞቹ ወደ መጡበት በሰላም ተመልሰዋል።

Read More »

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን 70 በመቶው የአመራር ቦታ በህወሀት አባለት የተያዘ ነው ተባለ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ሁለተኛ ጥናቱ ላይ እንዳመለከተው በ11 መምሪያዎች የተዋቀረው በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን የሚያስተዳደርው የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይሬክተርነትና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ በ29 የከፍተኛ አመራር አባላት ነው። ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ...

Read More »

ፍረደም ሐውስ የ 2013 ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት ናት አለ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአለም ላይ ያሉ አገሮችን ነጻነት ( ፍሪደም) በማወዳደር ሪፖርቱን የሚያወጣው አለማቀፋዊ እውቅና ያለው ፍሪደም ሀውስ የ2013 ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጠው  ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት አገር ናት ብሎአታል። ፍሪደም ሐውስ የአለም አገራትን ነጻነት የሰፈነባቸው ከፊል ነጻነት ያለባቸውና ነጻነት የሌለባቸው አገራት በማለት በሶስት ከፍሎ የተመለከተ ሲሆን ፣ ነጻነት የሌለባቸው አገራት ተብለው የተፈረጁት መሰረታዊ የሆኑት የፖለቲካ ...

Read More »

በቦረና ዞን ህዝቡ ለሚሊሻ ማደራጃ ገንዘብ እንዲያወጣ እየተገደደ ነው

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቦረና ዞን የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መንግስት የአካባቢ ሚሊሻ ለማቋቋም በሚል ምክንያት እያንዳንዱ ዞኑ ነዋሪ 70 ብር በነፍስ ወከፍ እንዲከፍል አዟል። የአካባቢው ነዋሪዎች ” እኛን መልሶ ለሚበድለን ሚሊሺያ እንዴት ገንዘብ እናዋጣለን” በሚል ተቃውሞውን በማሰማቱ እስካሁን ድረስ፣ በቂ መዋጮ ሊዋጣ እንዳልቻለ ታውቋል። መንግስት በዞኑ እየተባባሰ የመጣውን ከብሄር ጋር በተያያዘ የሚነሳውን  ግጭት ...

Read More »

መንግስት በአገሪቱ በቂ ምርት አለ ቢልም ህዝቡ ግን ሸቀጦች ከገበያ እየጠፉ ነው ይላል

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ውስጥ የመሰረታዊ እቃዎች እጥረት በተለያዩ አካባቢዎች መታየቱን ተከትሎ 13 በመቶ የደረሰው ዋጋ ግሽበት ተመልሶ ያሻቅባል የሚል ስጋት ሰፍኗል። በተለይም በአገሪቱ የስንዴ፣ የዘይት እና ስኳር  እጥረት በስፋት መታየቱ፣ ህዝቡን ስጋት ላይ እንዲወድቅ አድርገውታል። ዳቦ ቤቶች በቂ የሆነ ስንዴ ለማግኘት ባለመቻላቸው በርካታ ዳቦ ቤቶች ዳቦ ማምረት ሊያቆሙ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። መንግስት ከዚህ ...

Read More »

መንግስት እግር ኳሱን ፖለቲካዊ መልክ ለማስያዝ ያሰበውን እቅድ እንዲያቆም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጠየቁ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ31 ዓመት በሁዋላ   የተገኘውን የስፖርት ውጤት በ አገር ቤት ውስጥ ለፖለቲካ ሲጠቀምበት የነበረው ገዥው ፓርቲ ፤በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው  29ኛው  የ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተመሣሳይ  ፖለቲካዊ  ቅስቀሳ  ለማድረግ ማቀዱ ኢትዮጵያኑን አስቆጥቷል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስተባባሪዎች  ፤እንደሚባለው መንግስት ፦<<ባለ ራዕዩ መሪ >>የሚል ጽሁፍ የተፃፈበትንና የአቶ መለስ ፎቶ ያለበትን ቲ-ሸርቲ ተጫዋቾቹም ሆነ ደጋፊዎቹ ...

Read More »

የከተራ በአል ዛሬ በኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ እየተከበረ ነው

ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመላ አገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች እየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበትን ቀን ለማሰብ የከተራ በአልን በድምቀት እያከበሩ ነው። በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ ታቦታት ከእየ አብያተክርስቲያናቱ ተነስተው በምእመናን ፣ ቀሳውስት እና ዘማሪያን ታጅበው ባህረጥምቀቱ ወደ ሚገኝበት ጃን ሜዳ አቅንተዋል። በአሉ በድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል አንዱ በሆነው ጎንደርም እንዲሁ ታቦታቱ ዛሬ ወደ ማደሪያቸው አቅንተዋል። ለ3ኛ ጊዜ ...

Read More »

በውጪ ያለው ሲኖዶስ በአገር ውስጥ የሚደረግን የፓትርያርክ ምርጫ አወገዘ

ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እርቀ-ሰላሙ ያልተሳካውም ሆነ የፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው የመመለስ ጉዳይ ተቀባይነት ያላገኘው ቤተ-ክርስቲያንን ለማጥፋት ቆርጦ በተነሳው ኢህአዴግ የተባለ ሀይል ምክንያት ነው ሲል በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ አስታውቋል። “ ለ እግዚአብሔር ተገዙ፤ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ”በሚል ርዕስ በስደት ያለው ሲኖዶስ ባወጣው ባለ 7 ገጽ መግለጫ ላይ፤ አራተኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ በከፍተኛ ባለስልጣናትና ትዕዛዝ በወታደሮች ተገደው እንዴት ከቦታቸው ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንድ ነን አንከፋፈልም አሉ

ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “አንድነን አንከፋፈልም” በማለት የሰደቀና የአንድነት ፕሮግራም አዘጋጅተው ውለዋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ በኑር መስጊድ በተካሄደው የሰደቃና  የአንድነት ስነስርአት ላይ ተካፍለዋል። ድርጊቱ ገዢው ፓርቲ ሙስሊሞችን ከሁለት ለመክፈል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመቃም የታለመ መሆኑን በስነስርአቱ ላይ የተካፈሉ ሙስሊሞች ገልጸዋል። ተመሳሳይ ዝግጅቶች በሻሸመኔ፣ በጅማ እና በመቱ መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል። ...

Read More »