ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፍሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ካፍ ኢትዮጵያን 10 000 የአሜሪካ ዶላር መቅጣቱን አስታወቀ:: ሳላሀዲን ሰኢድ ከዛምቢያ ጋር በተደረገው የመጀመሪያ ግጥሚያ ምርጥ ተጫዋች ተባለ:: በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው ግጥሚያ ደጋፊው ህዝብ የተለያዩ ነገሮችን ወደ ሜዳው በመወርወር በዛምቢያ ቡድን ላይ ላሳየው ተቀባይነት የሌለው ተቃውሞ ቅጣቱ መጣሉን ቢቢሲ አመልክቶል:: በደቡብ አፍሪካ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሞተዋል ተብለውት የተገነዙትና የተለቀሰላቸው አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት የቀብራቸው እለት ህይወት መዝራታቸው ተገለጠ
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሞተዋል ተብለውት የተገነዙትና የተለቀሰላቸው አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት የቀብራቸው እለት ህይወት መዝራታቸው ተገለጠ:: አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ድርጊቱ የተፈጸመው በትግራይ መቀሌ ሲሆን ከመቃብር ተርፈው ህይወት የዘሩት እናት ወ/ሮ ወይኒ ጸጋዬ እንደሚባሉ ተዘግቦል:: በመቀሌ ከተማ 03 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ወይኒ ጸጋዬ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ማለዳ ላይ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿ አስከሬናቸው ...
Read More »የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው ወጡ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ስር በሚገኙት በፔዳ ፣ ፖሊ፣ ይባብና ዘንዘልማ ካምፓሶች ይማሩ የነበሩ ከ95 በመቶ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው መውጣታቸውን የተወሰኑትም ወደ መጡበት አካባቢ መመለሳቸውን ተማሪዎች ገለጹ። ተማሪዎቹ ግቢአቸውን በመልቀቅ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የወሰኑት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው አስተዳዳሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚደረግ ጸሎት እንዲቆም፣ ሴቶች ጂሃብም ኒቃምብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን ተከትሎ ነው። አንዳንድ ተማሪዎች ...
Read More »በአላማጣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎች ቀኑን ሙሉ በልዩ ሀይሎች ታግተው ዋሉ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ጋርቬ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ጧት ወደ ስራ ለመሄድ ሲነሱ አካባቢያቸው በሙሉ በፌደራል ልዩ ሀይል ፖሊሶች ተከቦ አግኝተውታል። ማንም ከቤት እንዳይወጣ በማገድ የመንግስት ባለስልጣናት በስም ጽፈው የያዙዋቸውን ከ300 በላይ ቤቶች ሲያስፈርሱ ውለዋል። በእያንዳንዱ ቤት በር ላይ ሁለት ሁለት ልዩ ፖሊሶች ቆመው የእያንዳንዱን ሰው ቤት እንቅስቃሴ በሚከታተሉበት ሁኔታ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን እያበረረ በኢህአዴግ አባላት እየሞላ ነው
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአየር መንገዱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በኢህአዴግ አባሉ ስራ አስኪያጅ በአቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ በተጠባባቂው ስራ አስኪያጅ በአቶ ኢሳያስ ወልደማርያም እና በኦዲተሩ በአቶ ዋሱ ዘለለው አነሳሽነት ነባር ሰራተኞች ከስራ እየተቀነሱ በኢህአዴግ የወጣት ፎረም አባላት እየተተኩ ነው። በቅርቡ 36 የትኬት ሽያጭ ሰራተኞች እና 14 ኤጀንቶች ከስራ ተባረው በፎረሙ አባላት ...
Read More »“በአስመራ ሁሉም ነገር የረጋጋ ነው” ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ተናገሩ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አቶ የማነ ገብረቀመስቀል ለኤኤፍ ፒ አስመራ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም የተረጋጋች ናት በማለት ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት ሳሊህ ኦማር በበኩላቸው ምንም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራም ሆነ ምንም አይነት የአመጽ እንቅስቃሴ አልታየም ብለዋል። ቢቢሲ ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ የማስታወቂ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤትን የተቆጣጠሩት አማጺዎች፣ መስሪያ ቤቱን ለቀው ወጥተዋል። ተቋርጦ የነበረው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ስርጭቱን ...
Read More »የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ ኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቀ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በኢትዮጵያና በዛምቢያ መካከል ትናንት ምሽት የተደረገውን እግር ኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከማሰራጫ ቻናል በድብቅ በመውሰድ ማስላለፉን ደርሸበታለሁ ሲል የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን(ካፍ) መግለጹን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ዘገበ እንደ ዘገባው የ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሌሎች የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያሰራጩትን ጨዋታ በመስረቅ ጫዋታውን እንዳስተላለፈ የተደረሰበት በእረፍት ሰዓት የጨዋታው ስፖንሰር እንደሆኑ አድርጎ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ ሢሰራ ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስደናቂ ውጤት አገኘ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:– ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ ከአምናው ሻምፒዮን ዛምቢያ ጋር ተጫውቶ አቻ ተለያይቷል። ዋልያዎች ጀግንነታቸውን አስመሰከሩ በ29ኛው አፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ቀትር ላይ ከዓምናው ሻምፒዮን ከዛምቢያ ቡድን ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ 10 ሰው ተጫውቶ 1ለ1 ተለያዬ። በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው የእልታ ዜማ ታጅበውና ከላይ እስከ ታች በቢጫ አሸብርቀው ወደሜዳ የገቡት ዋልያዎች ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ ተቃውሞአቸውን አሰሙ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:– በኢትዮጵያ እና በዛምቢያ መካከል የተካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ ተከትሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ መንግስት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚወስደውን እርምጃ ተቃውመዋል። ሙስሊሞቹ መሪዎቻችን ይፈቱ፣ በእምነታችን አንደራደርም፣ የሀይማኖት ነጻነት ይከበር፣ የሚሉ መፈክሮችን በእንግሊዝኛ በመጻፍ ለአለም የቴሌቪዥን ተመልካቾች አሳይተዋል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ብሄራዊ ቡድኑን በከፍተኛ ስሜት ከመደገፍ አልፈው በእረፍት ሰአቶቻቸው ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ተስተውሎአል።
Read More »ልዩ ሀይል በአላጣማ መግባቱን ተከትሎ በከተማው ያለው ውጥረት አይሏል
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:– የኢሳት የአላማጣ ምንጮች እንደተናገሩት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰአት አካባቢ ከመቀሌ የተነሱ በ3 መኪኖች የተጫኑ ልዩ የፌደራል ፖሊስ አባላት አላማጣ በመግባት ህዝቡን እያሸበሩት ነው። በከተማዋ ጋርቬ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ 200 የሚጠጉ የቤት ባለንብረቶች ንብረቶቻቸውን ነገ ማክሰኞ የማያወጡ ከሆነ ፣ ቤቶቻቸው በዶዘሮች እንደሚፈርሱ ንብረቶቻቸውም እንደሚወረሱ እንደተነገራቸው ታውቋል። ...
Read More »