.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ የሚታየው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ ነው

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ከፍተኛ የተባለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመላ አገሪቱ እየታየ መሆኑን ዘጋቢያችን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ገለጸ ከሁለት ሳምንት በፊት ከ35 በላይ ታንኮችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል የተጓዙ ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ ከ30 ያላነሱ ታንኮች ወደ ሰሜን ተንቀሳቅሰዋል። ገዢው ፓርቲ መሳሪያዎችን ለምን እንደሚያንቀሳቅስ በትክክል ለማወቅ ባይቻልም፣ አንዳንድ ...

Read More »

የዋልድባ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት አቀረቡ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ  ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ።   የሚደርስባቸውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በደብዳቤ የዘረዘሩት መነኮሳቱ ፤መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትንም ዝርዝር አቅርበዋል።   <<መብታችን እየተጣሰ ስለሆነ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድልን ስለመጠየቅ>>በሚል ርዕስ ...

Read More »

የህሊና እስረኞችን ለማነጋገር ወደ ቃሊቲ የተጓዘው የሽማግሌዎች ቡድን በተቃውሞ ተመለሰ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማስታወሻው ላይ እንዳሰፈረው ወደ ቃሊቲ በማምራት ርዕዮት አለሙን ያነጋገሩት ፓስተር ዳንኤል ‹‹የእስከዛሬው ተግባርህ የሚያስረዳው የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚክንፍመሆንህን ነው፡፡ ስለዚህም በምንም አይነት ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ አይደለሁም›› የሚልያልጠበቁትን መልስ በማግኘታቸው የይቅርታ አጀንዳውን ሳያነሱ ተመልሰዋል፡፡ የሙስሊሙማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በበኩላቸው ለፓስተር ዳንኤል እና ለፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ  ፦‹‹ያቀረባችሁትን የይቅርታ መጠየቅ ሀሳብ  በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነንም አንልም፣ አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› የሚል መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከርዕዮትና ከሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ያልጠበቁትን መልስ ያጘኙት  የሽማግሌዎቹ ልዑካን፤ እስክንድር ነጋን ሳያነጋግሩተመልሰዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በግል የፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ሀሙስ ጥር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎችውስጥ የተዘጋጀ ሶስት ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡ ከቡድኑ አባላትመካከል ፓስተር ዳንኤል እና ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ ለታሳሪዎቹ  ‹‹ጉዳያችሁበፍርድ ቤት እየታየ ነው፤ ስለዚህም ክሱ አሁን ባለበት ደረጃ ሊቋረጥ አይችልም፡፡ እናም ክርክራችሁን አቋርጡና ጥፋተኛ ነን በሉ፣ ከዛም ፍርድ ቤቱ ከፈረደባችሁበኋላ ‹ይቅርታ› ጠይቃችሁ እናስፈታችኋለን›› የሚል  መደራደሪያ አቅርበው ነበር፡፡ ሆኖም የሙስሊሙ መሪዎች ‹‹ይህንን በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነኝም አንልም፣አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› ሲሉ በድፍረትና በቁርጠኝነት መልሰውላቸው ወደ እስር ክፍላቸው መመለሳቸውንና በተጠቀሰው ዕለት እስክንድር ነጋ ዘለው   አንዱአለምአራጌን ነጥለው ማናገራቸውን ታውቋል። ተመስገንአክሎም  የሽማግሌ ቡድኑ ለሙስሊሙ መሪዎች ‹‹የመጣነው አንዱአለምን ፈልገን ነው፣እናንተን እግረ መንገዳችንን ሰላም እንበላችሁ ብለን ነው›› ሲሏቸው፣ ለአንዱአለምም በተመሳሳይ  <የመጣነው ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሙስሊሙ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ አንድ ሥራ-አስኪያጁን ማባረሩ ታወቀ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እየተባለ የሚጠራውን ክፍል በስራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብዱል ጀባር ሀሚድን ከስራ ያባረረው የአየር መንገዱ ሙስሊም ሰራተኞች ከሌሎች ወገኖች ጎን ተቀላቅለው ተቃውአቸውን እንዲገልጹ አደራጅቷል በሚል ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ስራ አስኪያጁ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። በተያየዘ ዜናም በሱፐርቫይዘርነት ደረጃ ...

Read More »

ፓሊሶች በአራት ኪሎ የሚገኙ ቤቶችን በእሳት አቃጠሉ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለረጅም አመታት በአራት ኪሎ አካባቢ የኖሩ  ሰዎች ቦታው ለሼራተን ሆቴል ማስፋፊያ ይፈለጋል በሚል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው እንደቆየ የተናገሩት አይን እማኞች፣ ነዋሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት ተተኪ ቤት እስካልሰጣቸው ድረስ አካባቢውን ለቀው እንደማይሄዱ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ዛሬ ጧት ወደ አካባቢው ያቀኑት ፖሊሶች ነዋሪዎቹ እቃዎቻቸውን ሳያወጡ በቤታቸው ላይ እሳት በመልቀቅ ቤታቸውን አቃጥለውባቸዋል። ነዋሪዎቹ በጩሀት ወደ ፓርላማ ...

Read More »

በጥምቀት በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሸጡ የነበሩ ሰዎች ታሰሩ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብዙውን ጊዜ በጥምቀት በዓል ጊዜ የሚጠቀሰውንና ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያሰፈረውን ፦“አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተፃፈበት ቆብ  የጥምቀት ዕለት ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ታፍሰው ታሰሩ። እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ፤ ጥር 11/2005 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ...

Read More »

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ12ኛው ክፍለ ዘመን ከአለት ተፈልፍለው የተሠሩት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ የመሰንጠቅ አደጋ ላይ መሆናቸውንና አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኙም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ቅርሶችን የተመለከተው የፓርላማ ቡድን ማመልከቱን ሪፖርተር ዘገበ የቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ ጐለጐታ፣ ቤተ መርቆርዮስና ቤተ ደናግል አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ደረጃ መጎዳታቸው ተገልጿል። ታሪካዊዎቹ ህንጻዎች እየተሰነጠቁ መሆናቸውም በዘገባው ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዳይሬክተር ...

Read More »

ወ/ሮ አዜብ የመለስ ፋውንዴሽንን በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፓርላማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ያጸደቀውና በቢሊየን ብር የሚቆጠር ዓመታዊ በጀት ይኖረዋል ተብሎ የሚገመተው የመለስ ፋውንዴሽንን ወ/ሮ አዜብ መስፍን  በፕሬዚዳትነት ይመሩታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ፡፡ ባለቤታቸውን በድንገት በነሐሴ ወር 2004 አጋማሽ በሞት ካጡ በኋላ  ከአራት ወራት በላይ በተመረጡበት የፓርላማ ወንበር ላይ ተቀምጠው ያልታዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ይኸን ሃላፊነት ...

Read More »

በአለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ የተሰቃየ የለም ያሉት አቶ ስብሀት ነጋ ዛሬ ያ ሁኔታ መቀየሩን ገለጡ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አንዱ ጠግቦ ሲያድር ያልጠገበው ደግሞ በሰላም ተኝቶ ያድራል ብለዋል:: አዲስ አበባ ለሚታተመው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ከቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህውሀት) መሪ የነበሩትና ዛሬ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ተጽዕኖቸው እየበረታ መሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ስብሀት ነጋ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህመም ወዲህ ሚዲያ ላይ በብዛት እየቀረቡ መገኘታቸውን በዚህም ...

Read More »

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ክፍያ ሳይፈጽም ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለ ኤል ሲ ቱ የተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ክፍያ ሳይፈጽም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛንቢያ ቡድን ጋር ያደረገውን ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ:: ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት የአፍሪካ ዋንጫ የቴሌቪዥን ስርጭት ባለመብት ለሆነው ለ ኤል ሲ 2 ክፍያ ሳይፈጽም ስርጭቱን ማስተላለፉ ተመልክቶል:: በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተፈጸመውና ውንብድና የተሰኘው ለስርጭቱ ባለመብት ...

Read More »