ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እየተካሄደ ባለው 29ኛው የ አፍሪካ ዋንጫ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ነገ ከናይጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል። ዋልያዎቹ እና ንስሮቹ የሚያደርጉት የነገው ጨዋታ በከፍተኛ ደረጃ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቧል። ምድቡን ቡርኪናፋሶ በ4 ነጥብ ስትመራ ዛምቢያና ናይጀሪያ በ2 ነጥብ ይከተላሉ። ዋልያዎች በ 1 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በዳውሮ ዞን የህዝቡን ተቃውሞ መርተዋል የተባሉ ሰዎች ታሰሩ
ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን በማረቃ ወረዳ ከወረዳ እና ከሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ግጭት መርተዋል ከተባሉት መካከል አቶ ዱባለ ገበየሁ፣ አቶ ጎሳሁን ዶሳ ዶሻና አቶ ግዛቸው ታደሰ ከበደ በትናትናው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። በዞኑ የሚታየው አለመረጋጋት ያሳሰበው መንግስት ግለሰቦቹ በአካባቢው የሚደረገውን ተቃዎሞ በማደራጀት በኩል እጃቸው አለበት በሚል እንዳሰራቸው፣ ቤቱ ለፍተሻ በሄደበት ...
Read More »አዲስ ታይምስ መጽሄት ገበያ ላይ አለመዋሉ ታወቀ
ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይዘጋጅ የነበረውና ከ1997 ዓም ወዲህ ከታተሙት የግል ጋዜጦች መካከል በጠንካራ ዘገባዎቹ እና በአንባቢ ብዛቱ ቀዳሚ የነበረው ፍትህ ጋዜጣ በመንግስት ጫና ከተዘጋበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ ይዘጋጅ የነበረው አዲስ ታይምስ መጽሄት በገዢው ፓርቲ በደረሰበት ጫና ዛሬ ለንባብ አለመብቃቱ ታውቋል። በአራት ኪሎ ፣ ስድስት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ መርካቶ፣ ብላሚንጎ ፣ ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከዋሊያዎች ጎን እስከመጨረሻው እንደሚቆሙ ገለጹ
ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ያነጋገራቸው ደጋፊዎች እንዳሉትምንም እንኳ ብሄራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር በተጫወተበት እለት ያገኘው ውጤት አሳዛኝ ቢሆንም፣ በቀጣዩ ጨዋታ የናይጀሪያን ቡድን በማሸነፍ ለቀጣዩ ዙር ለማለፍ ድጋፋቸውን አጠንከረው እንደሚሰጡ ገልጸዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚኖረው ደጀኑ በቀለ ድሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚሆን ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል ከቡርኪና ፋሶ ከነበረው ጨዋታ በፊት ኢትዮጵያውያን ኮከብ ካለው ሰንደቃላማዎች ውጭ ሌሎችን ...
Read More »የኢሳት ቀን በሳንድሽን ኖርዌይ ካምፕ ውስጥ ተከበረ
ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ተነሳሽነት ስለ ኢሳት አላማ ለ ኖርዌጅያን ማህበረሰብ ፣ በ ሳንድሽን አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በሙሉ ለማሳውቅ እና ኢሳትንም እንዲደግፉ ለማድረግ የኢሳት ቀን በሚል ያዘጋጁት በአል መከበሩን ገልጸዋል። በእለቱም በሳንድሽን ለሚኖሩ ኖርዊጅያን የተለያዩ የፖለቲካ ተወካዮች ፣ የስደተኞች አስተማሪዎች በሙሉ ስለ ኢሳት የሚገለጽ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት ...
Read More »ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን ስርጭት በተሻለ ሳተላይት ለማስተላለፍ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት አስተዳደር እንደገለጸው የአሞስ የሳተላይት ስርጭት ለጊዜው በቴክንክ ችግር ምክንያት ቢቋረጥም፣ ቦርዱ ባወጣው ስታራቲጂካዊ እቅድ መስረት ኢሳት ስርጭቱን በአስተማማኝና በዘላቂ መንገድ ማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ከልዩ ልዩ የሳተላይት ኩባንያዎች ጋር ተስማምቶ አገግሎቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ በስፋትና በጥራት ለማድረስ እየሰራ ነው ብሎአል። የኢሳት ሬዲዮናችን በአጭር ሞገድ በየቀኑ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ...
Read More »በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ዋሉ
ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ በተካሄደውና በብዙ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር መስጊድ እና ከመስጊዱ ውጭ ያሉ መንገዶችን ሞልተው የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል። “በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደረግ ጭቆና ይብቃ፣ በቃል ኪዳናችን እንጽና፣ ውሸት ሰለቸን፣ ኮሚቴዎች ይፈቱ፣ የሀሰት ምስክሮች አይቅረቡ ” የሚሉ መፈክሮች በብዛት መታየታቸውን የዘገበው ሪፖርተራችን፣ አንዳንድ አማንያንም “መንግስት የለም” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል። አብዛኛው ...
Read More »ገቢዎች እና የከፍተኛ ግብር ከፋይ ኩባንያ ባለአክስዮኖች እንደተፋጠጡ ነው
ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በንግድ ማኀበራት ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ የ10 በመቶ የጣለው የግብር ውሳኔ ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን ኩባንያዎችና ባለአክስዮኖችን አስቆጥቷል፡፡ ባለስልጣኑ በተሻሻለው የገቢ አዋጅ ቁጥር 286/94 በአንቀጽ 4 ላይ የአክስዮን ማኀበራትና ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ካከፋፈሉት የአክስዮን ድርሻ ትርፍ ገቢ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው ባገኘው ገቢ ላይ የ10 በመቶ ግብር እንደሚከፍል ይደነግጋል፡፡ ባለስልጣኑ ከዚህ ...
Read More »አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ራሱዋን መስቀሉዋ ተዘገበ
ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኩዌት በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ራሱን በገመድ በስቀል አረብ ታይምስ በፎቶግራፍ አስደግፎ ያወጣው ዘገባ ያመለክታል። የጸጥታ ሀይሎች በአካባቢው ሲደርሱ ስሟ ያልተጠቀሰው ኢትዮጵያዊት ራሱዋን አንቃ መግደሉዋ ለመመልከት መቻላቸውን በዘገባው ተመልክቷል። የልጂቱ አስከሬን ለምርመራ መወሰዱ ቢታወቅም፣ ሰራተኛዋ ራሱዋን ማጥፋቱዋንና አለማጥፋቱን የኩየት የደህነነት ሰራተኞች ከገለጹት ውጭ በሌላ ወገን የተረጋገጠ ነገር የለም። የኢትዮጵያ ኢምባሲም ...
Read More »ለመጪው የአካባቢ ምርጫ የተመዘገበው ህዝብ ከ30 በመቶ ከፍ ሊል አልቻለም
ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከምርጫ ቦርድ የውስጥ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት በምርጫው ለመሳተፍ የተመዘገበው ሰው ቁጥር ድርጅቱ በይፋ ከተገለጠው በእጅጉ ያነሰ ነው። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከ89 በመቶ በላይ መራጭ ህዝብ እንደተመዘገ በይፋ ቢያስታውቅም፣ እስካሁን በትክክል የተመዘገበው ግን 33 በመቶ ብቻ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። በህዝቡ የምርጫ ፍላጎት ማጣት ግራ የተጋባው ኢህአዴግ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ አመራሮችን ” ...
Read More »