ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት በአጀንዳ መልክ ለፓርላማ ቀርቦ የነበረውና ባልታወቀ ምክንያት ፓርላማው እንዳይወያይበት በተደረገው የቀድሞ የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ _ሕግ አስፈጻሚው አካል አሁንም ዝምታን መምረጡ አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል፡፡ ፓርላማው ከሁለት ሳምንት በፊት ባቀረበው አጀንዳ የአንድ የም/ቤት አባል ያለመከሰሰ መብት ስለማንሳት በሚል ለውይይት አጀንዳ መያዙን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ ዱባለ ገበየሁና ሁለቱ ዐቃብያነ ህጎች ክስ ተመሰረተባቸው
ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን ተነስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ አቶ ዱባለ ገበየሁ ፣ አቶ ጎሳሁን ዶሳ ዶሻና አቶ ግዛቸው ታደሰ ከበደ ትናንት ከሰዓት በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ግለሰቦቹ ሕዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳትና በማሳመጽ ፣ ሕገመንግስ ቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር እንዲሁም የመንግሥትን ንብረት በአመጽ በማስወደም ወንጀል ተከሰዋል። ኢሳት ያለውን የመረጃ ሰንሰለት ተጠቅሞ አቶ ዱባለን በእስር ቤት ውስጥ ...
Read More »ከግብርና የተገኘው የውጭ ምንዛሬ ከግማሽ በታች ቀነሰ
ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በግብርና ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት የሆልቲካልቸር፣ሥጋና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ገቢ በአስደንጋጭ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን አቶ ተፈራ ደርበው የግብርና ሚኒስትር ዛሬ ለፓርላማው ያቀረቡት ሪፖርት ጠቆመ፡፡ በ2005 የኢትዮጵያ የበጀት ቀመር የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከሥጋና ከቁም እንስሳት ከወጪ ንግድ(ኤክስፖርት) 299 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው ከግማሽ በታች ማለትም 130 ሚሊየን ወይም የዕቅዱን 44 ...
Read More »ምርጫ ቦርድ እንደተጠበቀው ተጨማሪ የመመዝገቢያ ቀን ሰጠ
ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተመዝጋቢዎች ድርቅ የተመታው መጪው የወረዳና የአካባቢ ምርጫ ምዝገባ ለሁለት ቀናት የተራዘመ ሲሆን፣ ኢህአዴግ ካድሬዎች በዩኒቨርስቲዎች ሳይቀር እየገቡ፣ ግለሰቦች እንዲመዘገቡ ካልሆነ ግን ችግር እንደሚደርስባቸው እየገለጡ ነው። የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካድሬዎቹ በዩኒቨርስቲዎች እየዞሩ ሰራተኞችን ተመዝግባችሁዋል አልተመዘገባችሁም እያሉ ሲጠይቁ ውለዋል። የኢህአዴግ ካድሬዎች በምርጫው ያልተመዘገቡትን ” ከእኛ ጎን ናችሁ ወይስ ከአሸባሪዎች ” በማለት እያስፈራሩ እንደሚገኙ ኢሳት ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለት ለዜሮ በሆነ ውጤት ተሸነፈ
ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዋልያዎች የመጀመሪያውን ግማሽ ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ ቢጨርሱም፣ በ79ኛው ደቂቃ ላይ ናይጀሪያዎች ያገኙነትን የፍጹም ቅጣት ምት በቪክቶር ሞስስ አማካኝነት አግብተዋል። የናይጂሪያ ቡድን 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ሌላ የፍጹም ቅጣት አግኝተው ሁለተኛውን ጎል በድጋሜ በሞስስ አማካኝነት አስቆጥረዋል። ጥፋቱን የሰራው ጎል ጠባቂው ሲሳይም በቀይ ወጥቷል። ብሄራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ካደረገው ጨዋታ ጋር ሲተያይ ዛሬ ...
Read More »የከምሴ ነዋሪዎች የሀይማኖት መሪያችንን አናስወስድም በማለት ተቃውሞአቸውን ገለጡ
ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢሉባቦር ዞን ከመቱ ከተማ 15 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ከምሴ ቀበሌ ፖሊሶች ሼህ ሳሊህ አብዱልቃድር የተባሉትን የእስልምና ሀይማኖት መሪ ለመውሰድ በሄዱበት ወቅት ህዝቡ ግለሰቡን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ችግር መፈጠሩ ታውቋል። ሼህ ሳሊህ አብዱልቃድር ከዚህ ቀደም በሽብርተኝነት ተከሰው 8 ወራት ከታሰሩ በሁዋላ መረጃ አልተገኘባቸውም በሚል በነጻ ተለቀው ነበር። ባለፈው ሳምንት ፖሊሶች እንደገና ወደ ...
Read More »በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 13 ሚሊዮን ብር በማውጣት ፎርጅድ ቀለሞችን የገዙ ሰዎች ተያዙ
ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከዩኒቨርስቲው ምንጮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዩኒቨርስቲው ፋይናንስና ሂውማን ሪሶርስ ክፍል ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች 13 ሚሊዮን ብር ዋጋ የሚያወጣ ፎርጅድ ( የተጭበረበረ)የፕሪንተር ቀለምና የኮምፒተር እቃዎችን ገዝተዋል ተብለው በፌደራል ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውለዋል። የተያዙት ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩና ላለፉት 20 አመታት በተለያዩ መንገዶች ለአካባቢው ህዝብ የሚላከውን ገንዘብ በመዝረፍ የሚታወቁ ናቸው። አንድ ...
Read More »የኦሮሞ ተወላጆች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቁ
ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሞ ጥናት ማኅበር፣ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ድርጅት፣ የኦሮሞ ወጣቶች ራስ አገዝ ማኅበር፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግና የኦሮሞ ድጋፍ ቡድን የተዘጋጀው ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ኦልባና ሊሌሳን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የአሜሪካ ድምጽ እንደዘገበው ከአቶ በቀለ ገርባ እና ከአቶ ኦልባና ሌሊሣ በተጨማሪ በስም የተጠቀሱት ወልቤካ ...
Read More »የአርቲስቷ ባል ኢትዮጵያ ውስጥ ታሰረ
ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱ ለንደን የሆነው የኢትዮጵያ ዳንኪራ የዳንስ ግሩፕ አባል የሆነችው አርቲስት እስከዳር ታምሩ እና ባለቤቷ አበበ ወንድምአገኝ በደህንነት ሃይሎች የዛሬ ሳምንት ቦሌ አካባቢ ታሰሩ። እንደ ደብረ ብርሀን ብሎግ ዘገባ ፤ጥንዶቹ የሁለት አመት ልጃቸውን ይዘው ከሎንዶን ወደ አዲስ አበባ የሔዱት በአል ለማክበር ነበር። እዚያ እንደደረሱ ከታሰሩ በሁዋላ አርቲስት እስከዳር ስትለቀቅ ባለቤቷ አበበ አሁንም እስር ቤት ...
Read More »ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነቱን ወሰደች
ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ለመጪው አንድ ዓመት የ አፍሪካ ህብረትን በሊቀ-መንበርነትን እንዲመሩ ተመረጡ። እሁድ አዲስ አበባ በተካሄደው የ አፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የመሪዎች ስብሰባ ኢትዮጵያ የሊቀመንበርነቱን ቦታ ከቤንን መረከቧን የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ዘገቧል። ይህን ታላቅ ድርጅት ለመጪው አንድ ዓመት እንድመራ በመመረጤ ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል-አቶ ሀይለማርያም። <<ሹመቱንም የምቀበለው በታላቅ አክብሮትን የደስታ ስሜት ነው>> ...
Read More »