የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የ6ኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ በእጩነት ባቀረባቸው 5 ሊቃነ ጳጳሳት ዙሪያ ተወያይቶ ለማፅደቅ ባሳለፍነው ቅዳሜ የተሰበሰበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ፣ ያለ አንዳች ውሳኔ መበተኑ ታወቀ። እንደ ሃራ ተዋሕዶ ብሎግ ዘገባ የዕለቱ የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባዔ፣ በተለይም ለእጩነት በቀረቡት አባቶች መካከል ከረር ያለ የቃላት ልውውጥ የተስተናገደበት፤ ዋና ጸሐፊውን ተክቶ የኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረበውየሕዝብ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በብራሰልስ የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዘግጅት ተካሄደ
የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-እውቁ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ በተገኘበት ትናንት የካቲት 17፣2005 ዓም የተካሄደው የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት በቤልጂየም የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። ከሰአት በሁዋላ የተጀመረው ስብሰባ የተከፈተው በቤልጂየም የኢሳት የገቢ አሰባሳቢ ግብረሀይል ወኪል በሆኑት በአቶ ገበየሁ ደስታ ነበር። በመቀጠልም ሌላው የኮሚቴ አባል አቶ ኤፍሬም ሻውል ኢሳት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰጠውን ግልጋሎት የተመለከተ ጥናታዊ ...
Read More »ፓትሪያርክ ለማሾም የሚደረገ ው የምረጡኝ ዘመቻ ቀጥሏል
የካቲት ፩፮ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ የፓትሪያርክ የምርጫ ቅስቀሳ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች ገለጹ። ሰሞኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ሲዘገብ የቆየውን የፓትሪያርክ የምርጫ ቅስቀሳ፣ ፓትሪያርክ ይሆናሉ ተብሎ ባለፈው ሳምንት በተሰራጨው ዘገባ ላይ ስማቸው የተነሳው አቡነ ሳሙኤል አረጋግጠዋል። አቡነ ሳሙኤል ለአዲስ አድማስ በሰጡት አጭር ቃለምልልስ እንደገለጡት በምርጫው ዙሪያ የተለያዩ ቡድኖች ተፈጥረው ...
Read More »በብራሰልስ የሚካሄደው የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ቅድመ ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ዘጋጆች ገለጹ
የካቲት ፩፮ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እውቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ የሚሳተፍበት በቤልጂየም ብራሰልስ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ሲካሄድ መሰንበቱን የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገበየሁ ደስታ ለኢሳት ገልጸዋል። በቤልጂየም የኢትዮጵያውያን ኮሚቴ ማህበር ከኢሳት የቀረበለትን የትብብር ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ እንዳሳዘናቸው አቶ ገበየሁ አልሸሸጉም ። የኢሳት የገቢ መሳባሰቢያ አዘጋጆች ለማህበሩ ያቀረቡት ጥያቄ ፣ የኮሚኒቲውን ኔት ...
Read More »ካኤልም- ኤር ፍራንስ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን በረራ ሰረዘ
የካቲት ፩፮ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኔዘርላንድስ አየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን በረራ የሰረዘው አትራፊ ባለመሆኑ ነው ብሎአል። ድርጅቱ ለሪፖርተር እንደገለጠው ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን በረራ ከተለያዩ አየር መንገዶች በገጠመው ውድድር እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ ለመሰረዝ ተገዷል። “ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገው በረራ አትራፊ አይደለም” ያሉት የካኤል ኤም የኢትዮጵያና የሱዳን ወኪል ሚ/ር ዲክ ቫን ኒወንሀውዘን፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን በረራ ሸሪክ ...
Read More »በአጋሮ በርካታ ሙስሊሞች መደብደባቸው ታወቀ
የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጁመአን ስግደት ተከትሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ ቢሞክሩም የፌደራል ፖሊስ አባላት የሀይል እርምጃ ወስደዋል። በርካቶች መታሰራቸውን፣ መደብደባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል:: ከፍተኛ ተቃውሞ ከታየባቸው ከተሞች መካከል ሻሸመኔ አንዱ ሲሆን፣ በርካቶች በ04 መስጊድ ተገኝተው ድምጻችን ይሰማ መሪዎቻችን ይፈቱ ማለታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ተመሳሳይ ተቃውሞዎች በበደሌ፣ መቱና ድሬዳዋ መካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የኢትዮጵያ ...
Read More »ሰመጉ የተላለፈው ዘጋቢ ፊልም የተከሰሱ ሰዎችን ሕገመንግስታዊ መብት የጣሰ ነው ባወጣው መግለጫ አስታወቀ
የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰመጉ በዚሁ መግለጫው በፌዴራል ፖሊስና በብሄራዊ ደህንነት እና ጸጥታ ባለስልጣን ተዘጋጅቶ በኢቲቪ እንዲቀርብ የተደረገው ፊልም ተጠርጣሪዎቹ በሕገመንግስቱ መሰረት በተከሰሱበት ወንጀል ከፍርድ በፊት እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብታቸውን የጣሰ መሆኑን ጠቁሞ ይህ በመሆኑም ከአሁን በኋላ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤት የመከላከያ ምስክሮችን የማቅረብ አቅማቸው አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሶአል፡፡ የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ ደህንነት እና ጸጥታ ባለስልጣን እንደ ህገመንግስት ...
Read More »የካናዳ ኩባንያ በደቡብ ኦሞ ነዳጅ ፍለጋ እንዲያካሂድ ተጨማሪ መሬት ተሰጠው
የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ካናዲያን ኤክስፕሎረር አፍሪካን ኦይል የተሰኘው ኩባንያ አዲስ መሬት የተሰጠው በምስራቅ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው። ኤክስፕሎረር አፍሪካ በደቡብ ኦሞ የነዳጅ ፍለጋ በማካሄድ ላይ ካለው ቱሎው ኦይል ጋር በሸርክና የሚሰራ ድርጅት ነው። ቱሎው ኦይል በደቡብ ኦሞ የሚያካሂደው አሰሳ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ይናገራል። ድርጅቱ ተሳክቶለት ነዳጅ ማውጣት ከጀመረ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ...
Read More »ፕሬዚዳንት ሞርሲ ምርጫ እንዲደረግ አዘዙ
የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግብጹ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሞርሲ ጥሪውን ያቀረቡት በአገሪቱ የሚታየው ተቃውሞ እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ነው። የአስመራጮች እጥረት በመፈጠሩ ምርጫው ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ድረስ ባለው የጊዜ ገደብ እንደሚከናወን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ሞርሲና ፓርቲያቸው ምርጫው በየጊዜው የሚካሄደውን የመንገድ ላይ ተቃውሞ ያስቀራል ብለው ያምናሉ። .ግብጽ በሊበራል ዲሞክራሲ አቀንቃኞችና በሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ደጋፊዎች ስትታመስ መቆየቷ ይታወቃል። ፕሬዚዳንት ሞርሲ ...
Read More »የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በኢህአዴግ አመራር ተስፋ መቁረጣቸውን ተናገሩ
የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሚያዝያ ወር 2005 የሚካሄደውን የአዲስአበባ እና የአካባቢ ምርጫ ተከትሎ የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹማምንት በዘመቻ ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር በየክፍለ ከተማው በጀመሩት ውይይት ከፍተኛ ትችት እያስተናገዱ መሆኑን በስብሰባዎቹ ላይ የተገኙ ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ የወደፊቱ የከተማዋ ከንቲባ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቁትን አቶ ድሪባ ኩማን ጨምሮ የአሁኑ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው፣የመንግስት ተጠሪ ሚ/ር ...
Read More »