የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት አራት ሳምንታት በአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ስለ ሰብአዊ መብቶች ቀላል፣ ግልጽ እና አስተማሪ በሆነ መንገድ እያቀረበ ለኢሳትም የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ የሰራው እውቁ አርቲስት ታማኝ በየነ የአውሮፓ ጉዞውን ቅዳሜ ማርች 2፣ 2013 በጀርመንዋ የፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ዝግጅትና ስነስርአት አጠናቋል። አርቲስት ታማኝ ጉዞውን በጄኔቫ ስዊዝርላንድ ጀምሮ በ ስዊድን ስቶክሆልም፣ በ ኖርዌይ ኦስሎ ፣በ ጀርመን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በጀርመን የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን ፣ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል። ”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!” ፣”የፕሬስ ነጻነት ይከበር!” ”ሃሳብን ...
Read More »117ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ዝግጅት በሄግ ፣ ኔዘርላንድስ ተካሄደ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ ያጠናቀረው ዘገባ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ድባቅ በመምታት የኢትዮጵያን ነጻነት ያስከበሩበትን 117ኛውን የአድዋ ድል፣ የተለያዩ ምሁራን በአካል በተገኙበትና በስካይፕ በተደረገ ንግግር ታስቦ ውሎአል። የቀድሞው የህወሐት መስራች እና መሪ የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ እና ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ በአካል ፣ ፕ/ር ጌታቸው መታፈሪያ እና አቶ ኪዳኔ አለማየሁ ...
Read More »በመላ አገሪቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ
የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች በነደፉት መርሐግብር መሰረት በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ተቃውሞዎች የተደረጉ ሲሆን፣ መንግስት የሙስሊሙ ጥያቄ ከእጁ እየወጣ መውጣቱን የሚያመለክት ሆኗል። በመቀሌ፣ በመቱ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር፣ በጅማ ፣ ወልቂጤ፣ ጎንደር ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞዎች ተነስተዋል። በአዲስ አበባ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ” መሪዎቻችን ይፈቱ ድምጻችን ይሰማ በቤታችን ሰላም ስጡን” የሚሉ ...
Read More »በፓትርያርኩ ምርጫ መንግስት ሙሉ በሙሉ እጁን አስግብቶ ነበር ተባለ
የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ 6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ መንግስት እጁን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ እንደነበርና ምርጫው ነጻ፣አሳታፊና ገለልተኛነት በሆነ መልኩ እንዳልተካሄደ ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ የቀድሞ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ለሶስት ዓመታት ያህል በውጪ አገር ካለው ስደተኛው ሲኖዶስ ጋር ሰላም ለመፍጠር ቀጥሎ የነበረው ጥረት እንዲከሽፍና የፓትርያርክ ምርጫው በተፋጠነ ሁኔታ እንዲካሄድ ...
Read More »ጉምሩክና ግብር ከፋዮች እየተወዛገቡ ነው
ካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በተከማቸ የአክስዮን ድርሻ ላይ 10 በመቶ ክፍያ እንዲፈጸም ያወጣው መመሪያ አሁንም ከከፍተኛ ግብር ከፋዮቹ ጋር እያወዛገበው ይገኛል፡፡ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 መሰረት አክስዮን ማኀበራት ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ካከፋፈሉት የአክስዮን የትርፍ ድርሻ 10 በመቶ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ቢሆንም ላለፉት ዓመታት በህግ አስፈጻሚው ችግር አዋጁ ...
Read More »የመቀሌ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጡ
የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች በውሀ እና በመብራት እጦት ለ ዓመታት እየተንገላታን እንገኛለን ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች ለኢሳት ዘጋቢ እንደገለፁት ማዘጋጃ ቤቱ በሰጣቸው ቦታ ቤት ሠርተው ከገቡ ሁለት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፤እስካሁን ድረስ ውሀ እና መብራት ሊገባላቸው አልቻለም። ችግራቸውን በተደጋጋሚ ለሚለከተው የመንግስት አስተዳደር ቢያቀርቡም ምንም ዓይነት መፍትሔ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ ...
Read More »በኢትዮጵያ “የጥበብን ስራ እንኳ በነጻነት ማካሄድ አይቻልም” ሲሉ አንድ የጀርመን ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ተናገሩ
የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከኢትዮጵያ ለቅቆ የወጣው የጀርመን ሄንሪክ ቦል ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ፓትሪክ በርግ ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ስለለቀቀበት ምክንያት ለብሉበርጉ ዊሊያምስ ዳቪሰን ሲናገሩ “በኢትዮጵያ የጥበብ ስራ እንኳን በአሁኑ ጊዜ በጥርጣሬ የሚታይ ነው፣ ከመብት ጋር የተያያዘውን ስራችሁን አቁሙ በመባላችን ስራችንን ለቀን ወጥተናል” ብለዋል። የሲቪክ ሶሳይቲና ቻርቲ ህግ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ውርስ መሆኑን ...
Read More »ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተሾሙ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ስት ከፍተኛ ድጋፍ የነበራቸው በትግራይ አጋሜ አውራጅ በስቡህ ወረዳ የተወለዱት ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የፊታችን እሁድ ይሾማሉ። በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ማትያስ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ እጁን የከተተው የሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት ምርጫም እንደሆኑ አስቀድሞም ሲነገር የነበር ሲሆን፣ እርሳቸውን ...
Read More »በጅጅጋ የአማራ ተወላጆች ቤታቸው እየተነጠቁ ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸውን ገለጡ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት ፣ ካለፉት 40 አመታት ጀምሮ በሶማሊ ክልል በጅጅጋ ከተማ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ቤቶቻቸውን እያስረከቡ ለጎዳና ህይወት ተዳርገዋል። እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ ዋና ዋና የንግድ ቦታዎች የነበሩዋቸው የአማራ ተወላጆች፣ ለሶማሊ ተወላጆች እንዲያስረክቡ በመዳረጋቸው ብዙዎች ድርጅቶቻቸውን አስረክበው ወደ መሀል አገር ሄደዋል። ተወልደው ያደጉበትን ቦታ አንለቅም በማለት እስካሁን ...
Read More »