መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የያዘውን የአምስት ዓመት ዕቅድ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ወደሁለት ዓመት ካጠፈ በኋላ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ያለውን መልሶ ማልማት ሥራ በሰፊው እንደሚያከናውን አስታውቆአል፡፡ በዚህ የመልሶ ማልማት ሥራ በመሃል ከተማ የሚገኙ በርካታ ቁልፍ ቦታዎች የሚፈርሱ ሲሆን ነዋሪዎችም የመፈናቀል አደጋ ተደቅኖባቸዋል፡፡ በ2006 እና በ2007 በጀት ዓመትም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በ10 ቀናት ውስጥ አንድ ባለ አንድ ፎቅ ተገነባ
መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር፣ ሕንጻ ግንባታ እና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት ከጀርመኑ ባዉሃዉስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዊመር እና ከደቡብ ሱዳኑ ጁባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ ተማሪዎች አማካይነት በ10 ቀናት ውስጥ የባለ አንድ ፎቅ ተገጣጣሚ ሕንጻ ገነባ፡፡ ይህ በዓይነቱ አዲስ የሆነውን ቴክኖሎጂ በነገው ዕለት ይፋ ለማድረግ ፕሮግራም ተይዞአል፡፡ ቴክኖሎጂው በተለይ በጀርመን አገር የሚሰራበትና ...
Read More »የደመራ በአል ተከበረ
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው ደመራ በአል በመላ አገሪቱ ተከብሮአል። በአዲስ አበባ የሀይማኖቱ አባቶች ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የውጭ አገር ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተከብሮአል።
Read More »የመንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ከወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች አመጽ ጀርባ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን አሉበት አለ
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል። በቅርቡ በወልድያ ከተማ የወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች ባነሱት ...
Read More »በአማራ ክልል አንድ የፖሊስ አመራር ተገደለ
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደልጊ አካባቢ ከግጦሽ ሳር ጋር በተገናኘ በተነሳ ግጭት የአካባቢው ኗሪዎች በወሰዱት የመከላከል እርምጃ የፖሊስ አዛዡ ህይወት አልፏል፡፡ የፖሊስ አዛዡ ነዋሪዎችን ” መሬት የመንግስት በመሆኑ በተከለከለ ቦታ ላይ ከብቶችን ማሰማራት እንደማይችሉ መናገሩን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ” መሬት የኛ መሆኑን ነው የምናውቀው፣ መሬት የህዝብ እንጅ የመንግስት አለመሆኑን ነው የምናውቀው” የሚል መልስ በመስጠታቸው ጉዳዩ ...
Read More »አቶ ሬድዋን ኢትዮጵያና ቻይና በሚዲያ ዙሪያ በቅርበት እንዲሰሩ ጠየቁ
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱ የኮምኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ከቻይና ከህዝብ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያና ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በተመለከተ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ሁለቱም ልማታዊ መንግስታት በመሆናቸው በመገናኛ ብዙሀን ረገድ የሚሰሩት ብዙ ስራዎች አሉዋቸው ያሉት አቶ ሬዲዋን፣ የቻይናን ብሄራዊ ቴሌቪዥንና የዢኖዋን እንቅስቃሴ አድንቀዋል። ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በማፈን ከሚታወቁት አገራት ...
Read More »አሜሪካ የዲቪ ሎተሪ ከ5 ቀናት በሁዋላ እንደሚጀመር አስታወቀች
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ ዲቪ 2015 በፈረንጆች አቆጣጠር ኦክቶበር 1 ተጀምሮ ኖቬንበር 2 ይጠናቀቃል ብሎአል።
Read More »የቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በርካታ ወረዳዎች በጨለማ እንደተዋጡ 3 ወራትን አስቆጠሩ
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተከል ዞን በሚገኙ ከተሞች እንዲሁም በአዊ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ መብራት እንደተቋረጠባቸው ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። በፓዊ የኤሊክትሪክ ሐይል መቆጣጠሪያ እና ማከፋፋያ ዲስትሪክት ስር የሚገኙት እና የቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ወረዳዎች፤ወንበራ ፤ ጉባ ፤ድባጢ ፤ ግልገል በለስ ፤ፓዊ ፤ ዳንጉር ፤ ማንኩሺ ፤ማንዱራ ፤ ማንቡክ፤ ቡለን፤ ሞራ ከ500 ሺ ባለይ ...
Read More »የቀድሞው ፕሬዚዳንት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከእስር ተፈቱ
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዶ/ር ነጋሶ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ሽሮ ሜዳ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ከገለጹ ከሰአታት በሁዋላ ፣ ሊቀመንበሩ ማምሻውን ተፈትተዋል። አንድ ግለሰብ “የፓርቲው የሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ግብረሀይል አባላት ያለፍላጎቴ ፎቶግራፍ አንስተውኛል” በሚል ክስ መመስረቱን ተከትሎ ፣ የቅስቀሳ አባላቱ መያዛቸውንና እነሱን ለማስፈታት ወደ ስፍራው ያቀኑት ...
Read More »ወታደራዊ መኮንኖች የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄ አቀረቡ
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ ስብሰባ ላይ ሲሆኑ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ታውቋል። ከመቶ አለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባዎችን እያካሄዱ ያሉት የጄኔራሎች ስብሰባ ከወር በፊት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በጄኔራሎቹ ስብሰባ ላይ ለሰራዊቱ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፣ “ሰራዊቱ አሁን የሚያገኘው ደሞዝ ለኑሮው ...
Read More »