.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሜዲትራንያን ውቅያኖስ 130 አፍሪካዊ ስደተኞች ሞቱ

ከሊቢያ ወደ ጣሊያን 500 አፍሪካውያ ስደተኞችን ይዛ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የእሳት አደጋ በትንሹ 130 ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸው ተሰማ፡፡ ከአቅሟ በላይ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ጣሊያን የሚሄዱ ስደተኞችን የጫነችው ጀልባ በመጨናነቋ ከተሳፋሪዎች አንዱ እርዳታን ለማግኘት ሲል በለኮሰው እሳት ጀልባዋ መቀጣጠሏን አሶሼትድ ፕሬስ ከጣሊያን ዘግቧል፡፡ የእሳት ምልክትን ከሩቅ አይተው ሰዎች ለእርዳታ ይደርሱልናል በሚል የተለኮሰው እሳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጀልባዋን በእሳት ...

Read More »

ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ማፈንና አደባባይ መከልከል በህግም በታሪክም ያስጠይቃል ሲል አንድነትና 33 ፓርቲዎች በጋራ አስታወቁ

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲዎቹ ባወጡት መግለጫ የሶስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄችን ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የከንቲባው ጽ/ቤት መስከረም 3 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሠላማዊ ሠልፉን በመስከረም 19 ቀን ማድረግ እንደምንችል  የሚገልፅ የዕውቅና ደብባቤ ቢሰጠንም ፣  በእጅ አዙር ሠልፉን በመስቀል አደባባይ እንዳናደርግ ከመከልከሉም በላይ ከሕግ ውጨ በመከላከያ በፀጥታ ተቋማት አካባቢ እንድንሰለፍ ለማስገደድ በመሞከርና  ቅስቀሳ እንዳናደርግ ...

Read More »

በጀልባ መስጠም ከ130 በላይ ሰዎች አለቁ

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአብዛኛው የኤርትራንና የሶማሊያን ዜጎች ከጣሊያን በመጫን ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ የነበረችው ጀልባ ላምፔዱሳ በሚባለው የጣሊያን ደሴት አካባቢ ስትደርስ በመስጠሙዋ በውስጧ ከተሳፈሩት መካከል ከ130 በላይ የሚሆኑት መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር አስታውቋል። እስካሁን 150 ሰዎችን ለማትረፍ የተቻለ ሲሆን፣ የ130 ሰዎች አስከሬን ደግሞ በወደብ ሰራተኞች  ተሰብስቧል። ጀልባዋ 500 የሚሆኑ ሰዎችን ይዛ ጉዞ መጀመሩዋ ...

Read More »

ምክትል ጠ/ሚሩ በአቶ መለስ ዜናዊ አሰራር ላይ የመጀመሪያውን ትችት አቀረቡ

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት  ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አፈጻጸም ላይ ድክመት ማምጣቱን በመገምገም የማሻሻያ እርምጃ መወሰዱን  ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር   አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡ አቶ ደመቀ ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉትና ትላንትናና ዛሬ ታትሞ በወጣው ቃለምልልሳቸው ላይ አቶ መለስ ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አንዳንድ ዘርፎችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሸ ችግር እንዳጋጠመ ...

Read More »

የፖሊዩ ቫይረስ በሺታ በኢትዩጵያ እና ሶማሊያ በወረርሺኝ መልክ መከሰቱን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ።

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፖሊዩ ቫይረስ በተከሰተበት አካባቢ ሳይታወቅ ጉደት አድርሶዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት በበሺታው መጠቃታቸውን በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ በቀለ ለጋዜጠኖች ተናግረዋል፡፡ በሐገራችን ኢትዩጵያ እና አጎራባች አገሮች የተከሰተውን የፖሊዮ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት የፖሊዩ ቫይረስ መከላከያ ክትባት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ...

Read More »

በባህርዳር ድሆች መኖሪያ ቤታቸውን እየተቀሙ ለጎዳና ተዳዳሪነት ተዳርገዋል

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የድሃ ድሃ ተብለው ተመርጠው ኑሮቸውን በጉስቁልና የሚመሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከደርግ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድርስ በቀበሌ ቤቶች ሲገለገሉ ቢቆይም ያለ አግባብ በባለስልጣናት እየተቀሙ መሆኑ ለከፍተኛ ችግር እንዲጋለጡ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል። የመንግስት ባለስልጣናት ደሀዎችን “ተተኪ ቦታና ቤት ይሰጣችሁዋል” በማለት ቤቶችን እየቀሙ ለባለሐብቶች እና ለራሳቸው በሊዝ እየገዙ አዳዲስ ህንጻዎችን መገንባታቸውን ተከትሎ ድሆች ጎዳና ላይ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ውስጥ የሚታየው የንብረት ውድመትና ሙስና አስከፊ ነው ተባለ

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶባቸው በተዝረከረከ የንብረት አስተዳደር ሥርዓት ምክንያት ለብክነት፣ ለምዝበራ እና ለብልሽት የተጋለጡ ንብረቶችን ለመታደግ ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መጥፋቱን፣ የመስሪያ ቤቱ ባለስልጣናትም ያለጠያቂ በሙስና መዘፈቃቸውን  የፌድራል የስነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሺን ገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውስጥ የDCI እና የDN  የቧንቧ መገጣጠሚያዎች ቁመታቸው እና ውፍረታቸው በናሙና እየተለካ ሌሎች መመዘኛዎች ግን ...

Read More »

ካራቱሬ 62 ሚሊዮን ብር የንግድ ባንክን እዳ አለመክፈሉ ተዘገበ

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋምቤላ ክልል ከ300 ሺ ሄክታር ያላነሰ መሬት በነጻ በሚባል ዋጋ የተረከበው የህንዱ የእርሻ ኩባንያ ካራቱሬ ፣ በተሰጠው መሬት ላይ የልማት ስራ አለማከናወኑንና የባንክና ሌሎች እዳዎችን ለመክፈል አለመቻሉን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት የስራ ሒደት ባለቤት የሆኑት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለጋዜጣው  እንዳስረዱት ፣ ካራቱሪ ከባንኩ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 2011 ወደ ...

Read More »

በአዲስአበባ ከሚገኙ 58 የአሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ብቃት ያላቸው 10 ብቻ ናቸው

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ ያደረገውን ግምገማ ውጤት ተከትሎ ማንኛውም የመንጃ ፈቃድ ሰልጣኝ ከጥቅምት1 ቀን 2006 በፊት በማናቸውም የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ትምህርት እንዳይጀምሩ አስጠነቀቀ፡፡ ዛሬ ይፋ በተረደገው የጥናት ውጤት መሰረት ከ58 የማሰልጠኛ ተቋማት ዝቅተኛውን መስፈርት ማሟላት የቻሉት 10 ያህሉ ብቻ ...

Read More »

በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረው ከተፈቱት 39 ሰዎች መካከል 14ቱ ዛሬ የስራ ስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቁጫ ከወራት በፊት የነተሳውን ተቃውሞ መርታችሁዋል በሚል 40 ሰዎች በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረው ከቆዩ በሁዋላ ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ቢያዝም ፖሊስ አልፈታም በማለቱ ሰዎቹ ለተጨማሪ ወራት ከታሰሩ በሁዋላ ከቀናት በፊት መፈታታቸው ይታወቃል። ይሁንና የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ ወደ መስሪያ ቤታቸው ሲያቀኑ ለ14ቱ የስራ ስንብት ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል። ከስራ ከተሰናበቱት መካከል አቶ ቲንኮ ...

Read More »