.የኢሳት አማርኛ ዜና

የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ

ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ  “የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን  ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የመንግስት ሹሞችም ተገኝተው ነበር። ...

Read More »

መንግስት የቻይና ኩባንያዎች ላቀረቡት አቤቱታ መልስ ሰጠ

ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ብድር የሚሰጡ 2  ባንኮችን ጨምሮ 17 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት ስራዎችን ለተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ብቻ እየሰጡ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተከትሎ ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር መልስ መስጠቱን ሪፖርተር ዘግቧል። ጋዜጣው እንዳለው መንግስት ቅሬታዎችን ለማስተካከል ቃል ገብቷል። መንግስት የግዢ ስርአት እንደሚዘረጋና የመሰረተ ልማት ተቋማት ኮንትራት እንደ አዲስ እንደሚያዋቅር ገልጿል። ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ጦርነቱ ቀጥሏል

ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በአዲስ አበባ ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ለማስማማት ውይይት ቢጀመርም፣ በመሬት ላይ እየተደረገ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አልተቻለም። በዩጋንዳ መንግስት የሚደገፈው የመንግስት ጦር ቦር እየተባለ የሚጠራውን ስትራቴጂክ ከተማ ከተቆጣጠረ በሁዋላ በቅርቡ የተነጠቀውን ማላካልን መልሶ ለመያዝ ከፍተኛ ትግል እያደረገ ነው። መንግስት ከተማዋን መልሶ መያዙን ቢያስታውቅም፣ አማጽያኑ ግን ከተማዋ አሁንም በቁጥጥራቸው ስር ...

Read More »

በዩክሬን የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ያንኮቪች መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን በተመለከተ ያወጣው አዲስ ህግ ያስቆጣቸው ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት ከፖሊሶች ጋር እየተጋጩ ነው። መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን ለመገደብ ያወጣው አዲሱ ህግ በሌሎች የአውሮፓ አገራት ሳይቀር ተወግዟል። ተቃዋሚዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ከመወርወራቸውም በተጨማሪ፣ መኪኖችን ሲያቃጥሉ ታይቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ያንኮቪች ድርጊቱ የዩክሬንን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት እርምጃ ...

Read More »

የሩዋ ፈለግ ቀበሌ ነዋሪዎች ለሁለተኛ ቀን ከፖሊሶች ጋር ተፋጠዋል

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጽቢ ወንበርታ ወረዳ በሩሃ ቀበሌ ከመስኖ ግድብ ጋር በተያያዘ ሃሙስ እለት የተጀመረው ህዝባዊ  ተቃውሞ እስከ አርብ ምሽት የቆየ ሲሆን፣ የወረዳው የአስተዳደር ሰራተኞች እና የደህንነት ሀይሎች አመጹን የቀሰቀሱት እነማን ናቸው አውጡ በማለት ከህዝቡ ጋር እየተወዛገቡ ነው። ህዝቡ በበኩሉ ጥያቄው የህዝብ እንጅ የተወሰኑ ግለሰቦች ባለመሆኑ በግፍ የታሰሩት ሰዎች ይፈቱና ለጥያቄው መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጥ ...

Read More »

የአማራ ክልል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ይኖራቸል ብለው የሚጠረጥሩትን ሁሉ እንዲይዙ ታዘዙ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ወር በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር የተካሄደውን የብአዴን እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዞን እና የወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ኢህአዴግ አሸባሪ እያለ ከሚጠራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ በሚጠረጠሩት ወጣቶች ላይ  የቁጥጥር ዘመቻ እንዲካሄዱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል። ጥር 8፣ 2006 ዓም በሁሉም የአማራ ...

Read More »

በደቡብ ክልል 60 አቃቢ ህጎች ከስራ መባረራቸው ተሰማ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቃቢ ህጎቹ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ መባረራቸው ተግልጿል። የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች እንደገለጹት ከ100 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ የተለያዩ የዲሲፒሊን እርምጃዎችን ወስደዋል። ከ40 በላይ በሚሆኑ የእስር ቤቶች ሃላፊዎች ላይም እንዲሁ የዲሲፒሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን 10 ከስራ ተባረዋል። ጉቦ መቀበል፣ ወገናዊነት፣ ፍትህ ማዛባት እንዲሁም እስረኞችን እየፈቱ መልቀቅ ከዋና ዋና ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል። የኢሳት የደቡብ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እስካሁን ውጤት አላሳየም

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት እና በአማጽያን መካከል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ድርድር እንደቀጠለ ቢሆንም፣ ሁለቱም ሀይሎች በሚያቀርቡዋቸው ቅድመ ሁኔታዎች እስካሁን ውጤት አለመገኘቱ ታወቀ። አማጽያኑ የታሰሩት ባልደረቦቻቸው እንዲፈቱ፣ የዩጋንዳ ጦር አገሪቱን ለቆ እንዲወጣና የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያበቃ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡ ሲሆን፣ በመንግስት በኩል ደግሞ በአማጽያኑ የቀረቡትን በተለይም እስረኞችን መፍታት የሚለውን ቅድመ ሁኔታ አልተቀበለውም። ነገሮች እየባሱ ሄደው ...

Read More »

በሶማሊያ ክልል 47 ሰዎች መገደላቸውን የአገር ሽማግሌዎች ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በላኩት ደብዳቤ ገለጹ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀላፎ አካባቢ የሚኖሩ የየረር ባሬ ጎሳ  የአገር ሽማግሌዎች ለጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ያስገቡትና መረጃው ለኢሳት እንዲደርስ በሚል በላኩት መረጃ ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር እና ጄኔራል አብርሀም በቅጽል ስማቸው ኳታር የሚመራው ልዩ ሚሊሺያ እየተባለ የሚጠራው ሀይል ታህሳስ 1 እና 2 በከፈተው ተኩስ በትምህርት ላይ የነበሩ ህጻናትንና ወጣቶችን ጨምሮ 47 ሰዎችን ...

Read More »

የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ጸደቀ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከተሞች ሥር የሰደደውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል የተባለ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ፡፡ አዋጁ በተበታተነና በልማዊ መንገድ ሲካሄድ የነበረውን የመሬት ባለቤትነት ይዞታ አሰራርን በዘመናዊ መልኩ እንዲካሄድ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የህዝቦችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው ተብሎአል፡፡ የመሬት ይዞታ መብት ይፋዊ ምዝገባ ከመነሻው መሰረቱ የከተማ ቁራሽ መሬት ...

Read More »