ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ የሙባረክን መንግስት ያስወገደችበት 3ኛ አመት ለማክበር በምትዘጋጅበት ወቅት ነው አምነስቲ መግለጫውን ያወጣው። የሙባረክን መንግስት ከተወገደ በሁዋላ አገሪቱ ልትረጋጋ አለመቻሉዋን የገለጸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ በተለይም የሙርሲ መንግስት በወታደራዊ መሪዎች ከተወገደ በሁዋላ 1 ሺ 400 ሰዎች መገደላቸውን ከ500 በላይ በሚሆኑ ሟቾች ግድያ ዙሪያ ምንም አይነት ምርመራ አለመጀመሩን ገልጿል። የሙባረክን መንግስት በማስወገድ ከፍተኛ ሚና ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ፈቃድ ከወሰዱ የውጭ ባለሃብቶች ብዙዎቹ ወደስራ አለመግባታቸው መንግስትን አስደነገጠ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ባለፉት 15 ዓመታት ከኤጀንሲው ፈቃድ የወሰዱ 6ሺህ 500 ፕሮጀክቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ ወደሥራ ባለመግባታቸው የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸውን ለመሰረዝ መወሰኑ ታወቀ፡፡ በዚሁ መሠረት 2 ሺህ 500 ፕሮጀክቶች ፈቃዳቸው እንደሚሰረዝ ታውቋል፡፡ ከኤጀንሲው የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የቱርክ፣የሕንድና የቻይና ባለሃብቶች በአገሪቱ በግብርና በማኒፋክቸሪንግ እና በአገልግሎት ዘርፎች ለመሰማራት በቅደም ተከተል ...
Read More »አወዛጋቢው ሱዳናዊ ባለሀብት የአማራን ክልል ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አባይ ወንዘን ተንተርሶ በሱዳናዊው ባለሀብት የተቋቋመው የስጋ ፣ የዶሮ፣ የዘይት፣ የአትክልትና ፍራፍሮ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ላለፋት አምስት ዓመታት የተወራለትን ያህል ማምረት እና ማሰራጨት ባለመቻሉ የክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቤሮ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ ወስኗል። የከተማ አሰተዳደረም ቦታውን ለሌላ አልሚ እንዲሰጥ ታዟል፡፡ የክልሉ መንግስት ለሱዲናዊው ባለሃብት ሚ/ር አሽራፍ፣ በባህርዳር የሚገኘውን የዘይት ፋብሪካ እና ...
Read More »በመንግስት ተቋማት ላይ ሙስና መስፋፋቱ ተነገረ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከለጋሽ አገሮች ባገኘው ድጋፍ ተመስርቶ የውጭ ባለሀብቶችን በማሳተፍ ባስደረገው ጥናት የመንግስት ግዢዎችና ኮንትራቶች ግልጽነት የጎደላቸው መሆናቸውን አረጋግጧል። የውጭ ባለሀብቶች አራት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ሙሰኞች ብለው እንደፈረጁዋቸው ሪፖርተር ዘግቧል። 71 በመቶ የሚሆኑ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ቢዝነስ ለማቀላጠፍ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። ባለሀብቶቹ በዋናነት ያነሱትም ሙስና ተስፋፍቷል የሚል ነው። ውስብስብ የሆነው ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ግብጽ ወደ አለማቀፉ ማህበረሰብ ለመሄድ ማሰቡዋን አጣጣለው
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ ባለስልጣናት የአባይን ግድብ በተመለከተ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር ሲያደርጉት የነበረውን ድርድር ካቋረጡ በሁዋላ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች ለጋሽ አጋራት ለመውሰድ መወሰናቸውን የግብጽ ባለስልጣኖች መናገራቸውን ተከትሎ ግብጽ በየትኛውም መድረክ ብትሄድ ምንም የምታመጣው ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እየተናገሩ ነው። አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን የመንግስትን ባለስልጣናት በመጥቀስ ግብጽ የአባይን ግድብ ግንባታ ለማስቆም ...
Read More »መቶሺዎች የተሰውበትን የሶሪያን ጦርነት ለማስቆም ድርድር ተጀመረ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶሪያ መንግስት እና የተቃዋሚዎች ተደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ የተሰበሰቡ ሲሆን ፣ሁለቱም ተደራዳሪዎች ከማለዳው ሃይለ ቃሎችን ተለዋውጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለቱም ተደራዳሪዎች ወደ ገንቢ ውይይት እንዲመጡ ቢጠይቁም እስካሁን ተስፋ የሚሰጥ ነገር አልተገኘም። አንዱ እና ዋናው አጀንዳ ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ ስልጣን ላይ ስለመቆየታው ሲሆን፣ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ ፕሬዚዳንት ባሽር ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ...
Read More »ከሱዳን ጋር የሚደረገው የድንበር ውዝግብ የሞራልና የሶሻል ጥያቄ እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌና በሱዳኑ አቻቸው ጃፋር ኤሊ ሜሪ መካከል የተጀመረ እና እስካሁኑም የዘለቀ መሆኑን ባለስልጣኑ አውስተዋል። ሱዳኖች “ኢትዮጵያውያን የጉዊን መስመር እየተባለ ...
Read More »በምስራቅ ሃረርጌ ከ59 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የኦሮሞ ጥናት ማህበር አስታወቀ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ኢሌሞ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ጥቂት ወራት በአንያ፣ ማቶ እና ሙለቄ ቆላማ ወረዳዎች ላይ በፌደራል መንግስቱ እውቅና የተቋቋመውና ስልጠና የሚሰጠው ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ሃይሎች በኦሮሞዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት 59 ገድለው፣ 42 አቁስለዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከልም ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል። “በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ሰላም ካገኙ ለተቃዋሚዎች ምቹ ቦታ ...
Read More »አዲሱ የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመት በግል ጋዜጦች ላይ ለሚወሰደው እርምጃ አመላካች ነው ተባለ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አቶ ዘርዓይ አስገዶምየኢትዮጵኢያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው መንግስት ከምርጫ 2007 በፊት በፕሬሱ ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠንካራ አስፈጻሚ በማስፈለጉ ሊሆን እንደሚችል ኢቲቪን የለቀቁ አንዳንድ ጋዜጠኞች ተናገሩ። የአቶ ዘርዓይ ከቴሌቪዥን ዳይሬክተርነት መነሳት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ የድርጅቱ ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ከወራት ...
Read More »የደቡብ ሱዳን መሪ ተመድን ወቀሱ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ላይ ወቀሳቸውን የሰነዘሩት ድርጅቱ ራሱን እንደ ሁለተኛ መንግስት በመቁጥር የጦር መሳሪያዎችንና አማጽያንን አስጠልሏል በማለት ነው። ፕ/ር ሳልቫኪር የተመድ ዋና ጸሀፊ አገሪቱን ማስተዳደር የሚፈልጉ ከሆነ በግልጽ ይንገሩን ያሉ ሲሆን፣ ተመድ ወደ አገራቸው ሲገባ ተጓዳኝ መንግስት ሆኖ መግባቱን አላውቅም ነበር ብለዋል። ተመድ በበኩለ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የቀረበውን ...
Read More »