የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና የኢሳት የኮምፒዩተር ባለሙያ በሆነው ተቀማጭነቱ ቤልጂየም በሆነው የኢሳት ባልደረባ ላይ የተገኙ ባእድ የመሰላያ ሶፍትዌሮች ከጣሊያኑ ሃኪንግ ቲም የተላኩ መሆናቸውን ሲትዝን ላብን በመጥቀስ ታዋቂው ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። ጋዜጣው ባወጣው ሰፊ ዘገባ መረጃዎችን ከኮምፒዩተሮች ላይ ለመውሰድ የሚያስፈልገው ባእድ ሶፍትዌር የተላከው ከጣሊያን ኩባንያ ጋር ቢሆንም፣ ኩባንያው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሀገረ-ማርያም ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የሀገር ሽማግሌዎች ታሰሩ
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአርሴማ ቤተክርስቲያን የተነሳውን የውስጥ ችግር ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላት ታስረዋል። በህዝቡ የተመረጡት 15ቱ ሽማግሌዎች ችግሩን ለመፍታት በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የቀጠናው ሃላፊ የሆኑት አቡነ ገብርኤል የሰበካ ጉባኤ አባላቱ እንዲበተኑና ችግሩን ለመፍታት እንደሚሞክሩ መግለጻቸው ህዝቡን አስቆጥቷል። ጳጳሱ ለፌደራል ፖሊሶች በማመልከት የአገር ሽማግሌዎች እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ዛሬ ጳጳሱ ወደ አካባቢው በመሄድ ...
Read More »የብአዴን ዋና ጸሃፊ ቤት በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ተወላጆች ላይ በጅምላ ፀያፍ ስድብ የሰነዘሩት የብአዴኑ አመራር እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የ አቶ ኣለምነው መኮነን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የዘገበ ሲሆን፣ ዜናውን ተከትሎ ኢሳት ባደረገው ማጣራት የባለስልጣኑ መኖሪያ ቤት በ11 ፖሊሶች ሌትና ቀን እየተጠበቀ ነው። አቶ አለምነው የአማራው ህዝብ የትምክህት ለሃጩን በማራገፍ ከሌላው ህዝብ ጋር ለመኖር ...
Read More »የጋዜጠኛው ጥያቄ ጠ/ሚኒስትሩን አስቆጣ
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጽ/ቤታቸው ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ በቀረበላቸው ጥያቄ በመቆጣት ዘለፋ ሰነዘሩ፡፡ አቶ ታምራት ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ በአሁን ሰዓት አገሪትዋን የሚመራት ማንነው ነው የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩም ብስጭታቸውን በምላሻቸው ወቅት አንጸባርቀዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጋዜጠኛውን ሂድና ...
Read More »በኦሮምያ ማንኛውም የፍርድ ቤት ጉዳይ በኮምፒዩተር ተጽፎ እንዲቀርብ ታዘዘ
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የፍትህ ቢሮ በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ ማንኛውም ባለጉዳይ አቤቱታዎችን በኮምፒዩተር ካላስጻፈ ጉዳዩ እንዳይታይለት ወስኗል። በክልሉ የሚገኙ ዳኞች በበኩላቸው ውሳኔው የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እና የእድገት ደረጃ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ይላል። ዳኞች እንደሚሉት አብዛኛው ህዝብ አቤቱታዎችን አስጽፎ የሚያቀርበው በወረቀትና በእስክር ቢቶ ሆኖ ሳለ፣ የድሆችን የኑሮ ሁኔታ ግምት ውስጥ ሳያስገቡ፣ ...
Read More »የግብፅ እና የኢትዮጵያ ውይይት ከጅምሩ ተቋረጠ
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ በጠየቁት መሠረት ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ቢገቡም፣ የዓባይ ግድብ ግንባታ እንዲቆም በመጠየቃቸው ውይይቱ በሰዓታት ውስጥ ተቋረጠ፡፡ ሪፖርተር እንደዘገበው የግብፅ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑና ከባልደረቦቻቸው፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተወከሉ ባለሙያዎች ጋር ባለፈው ሰኞ ተገናኝተዋል። ይዘዋቸው የመጡት አጀንዳዎችም ...
Read More »የአራጣ ብድር በአስከተለው ቀውስ ከ250 በላይ ነጋዴዎች ተሰደዋል
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ቋሪትና ጃቢጠህናን ወረዳዎች ይካሄድ የነበረው መረን የለቀቀ ህገወጥ የአራጣ ብድር ስርዓት በአስከተለው ቀውስ ከ250 በላይ ጠንካራ ነጋዴዎች ተሰደዋል ተባለ፡፡ ከፍተኛ ማታለል የነበረበት ይህ ህገወጥ የአራጣ ብድር ስርዓት ነጋዴዎችን ባዶ ያስቀረና ያሰደደ ከመሆኑ ባለፈ ብዙዎችን ለእብደትና ለቤት መፍረስ ዳርጓል ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉና ከ121 ሺህ ብር በላይ ተወሰደብኝ ያሉ አንድ የገነት ...
Read More »መንግስት በአገሪቱ እየታየ ላለው ረሀብ በቂ ዝግጅት እያደረገ አለመሆኑን መረጃዎች አመለከቱ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛ የግብርና ምርት እንደተገኘ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ካላገኙ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ መረጃዎች አመልከተዋል። የዓለም ባንክ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በመግብ ለስራ የታቀፉ ዜጎችን ሳይጨምር ከ3 ሚሎዮን ያላነሱ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በምስራቅ አማራ፣ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ በአፋር እና ኦሮምያ የተከሰተውን ረሀብ ለማስታገስ ...
Read More »በ500 ብር ደሞዝ የሚተዳደረው የህወሃት ታጋይ ከ10 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት ማካበቱ ተገለጠ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደህንነት ሃላፊ ከነበሩት ከአቶ ወልደስላሴ ወልደ ሚካኤል ጋር በግብረ-አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዮች ከደሞዛቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሃብት አግበሰው መገኘታቸው ታውቋል። በተለያዩ አለመግባባቶች የተነሳ እየተመሰረቱ ያሉ ክሶች የህወሃት ተጋዮች በህገወጥ መንገድ የሰበሰቡትን የሃብት መጠን ለማወቅ እየረዳ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን ከአቶ ወልደስላሴ ጋር በግብረ አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዩ የአቶ ወልደስላሴ ወንድም አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ...
Read More »አንድ የአየር ሃይል ባልደረባ የአርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የኢህአዴግን ስርአት በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላለቀሉን ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል። ም/መ/አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የ L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ እንደነበር መረጃው ያመለክታል። ም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ “ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ከእነሱም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለህ በሚል ምክንያት ተጠርጥሮ ያለምንም ወንጀል ለአምስት ...
Read More »