.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጠለፈበትን ምክንያት ለማወቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ነው

የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን በማምራት ላይ በነበረበት ጊዜ  ረዳት አብራሪው የጉዞውን አቅጣጫ በመቀየር ጄኔቭ አውሮፓላን ማረፊያ በማሳረፍ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የሆኑት ሬድዋን ሁሴን አየር መንገዱ የተጠለፈው ሱዳን በቆመበት ጊዜ በተሳፈሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ነው በማለት መጀመሪያ ላይ ለረዩተርስ መግለጫ ቢሰጡም፣ የስዊዘርላንድ ፖሊስ ግን ፈጥኖ ጠላፊው ...

Read More »

በሀገረማርያም ጳጳሱ ለአንድ ሰአት ታግተው ተለቀቁ

የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአርሴማ ቤተክርስቲያን የውስጥ ችግር ጋር በተያያዘ ከመንግስት ጋር በመሆን የድርጅት ስራ ሰርተዋል ተብለው የተወቀሱት አቡነ ገብርኤል፣ ትናንት ለአንድ ሰአት ያክል ታግተው ተለቀዋል። ህዝብ በመወከል ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የአገር ሽማግሌዎች ታስረው በህዝብ ግፊት እንዲፈቱ ከተደረገ በሁዋላ፣ ለችግሩ መፍትሄ ያስገኛል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም፣ ችግሩ እልባት ሳያገኝ ቀርቷል። ጳጳሱ በህዝቡ ከታገቱ በሁዋላ በአገር ሽማግሌዎች ማግባባት ...

Read More »

የቡና ኤክስፖርት ለሙስናና ብልሹ አሰራር ተጋልጧል

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቡናን ኤክስፖርት ከማድረግ ጋር በተያያዘ በክትትልና ቁጥጥር፣ በመረጃ አያያዝ፣ ያለብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ቡናን ወደውጭ ኤክስፖርት ከማድረግ እና በሁሉም አካባቢ የቡና ድርጅቶችን መጋዘኖች ክምችት ቆጠራ በወቅቱ ባለማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያጠናው አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ጥናቱ  ኤክስፖርት በማያደርጉ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ያለመውሰድ፣ በንግድ ፈቃድ ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር ያለማድረግ እና ...

Read More »

የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ መቱ

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታክሲ ሹፌሮች አድማውን የመቱት አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም ነው። በከተማው መሃል ላይ አሽከርካሪዎቹ ተሰብስበው የመኪና ጥሩምባ ማጮሃቸውን የገለጸው የኢሳት ወኪል፣ ከሰአዓታት በሁዋላ ታክሲዎቹ ከአደባባይ ላይ በመሰወራቸው ነዋሪዎች ታክሲዎችን ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል። የገዢው ፓርቲ ሰዎችና ትራፊኮች፣ በመንገድ ላይ ያገኙትን ታክሲ በማስገደድ ሰዎችን እንዲጭን ለማድረግ ሞክረዋል። ፈቀደኛ ያለሆኑ ሾፌሮች ጥያቄዎች ይቀርቡላቸው ነበር። አዳመው ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክ/ከተማ ለሚገኙ ሁሉም የጽ/ቤት ኃላፊዎች የጉርሻ ክፍያ እንዲሰጣቸው ፈቀደ፡፡

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጉርሻ ክፍያው ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ እንዲሰጣቸው ተብሎ የጸደቀበትና የክፍያ ማዘዣው ከከተማ  አስተዳድሩ ለሁሉም ወረዳዎችና ክ/ከተሞች በያዝነው ሳምንት እንደተላለፈላቸው ለማዎቅ ተችሎአል። የጉርሻ ገንዘቡ ከ1 ሺ 700  እስከ 4 ሺ 000 ብር የሚደርስ ሲሆን አገልግሎቱም ለስልክ፣ ለቤት ኪራይ እና ለትራንስፖርት መደጎሚያ ታስቦ የሚሰጥ ነው። ክፍያው በፋይናንስ መክፍያ  ሰነድ ወይም ፔሮል ላይ ሳይቀመጥ ከማንኛውም ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ችግር ዙሪያ የተጀመረው ድርድር ቀጥሎአል

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በሚካሄደው ድርድር በቅርቡ ከእስር የተፈቱት 7ቱ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳታፊዎች ሆነዋል። ይሁን እንጅ ባለስልጣኖቹ ከሁለቱም ወገኖች ሳይሆኑ በገለልተኛነት በድርደሩ ላይ መገኘታቸውን ተናግረዋል። ገለልተኝነትን የመረጡበትም ምክንያት ሲናገሩ ደግሞ የጦር መሳሪያ የለንም የሚል ነው። የሳልቫኪር መንግስት ባለስልጣኖችን ያሰረው ከተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ነበር። በሌላ በኩል ዩጋንዳ ጦሩዋን ከደቡብ ...

Read More »

በርካታ የየረር ጎሳ አባላት የአገር ሽማግሌዎች ታሰሩ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በቀላፎ አካባቢ የሚኖሩ 19 የየረር ባሬ ጎሳ የአገር ሽማግሌዎች በክልሉ ውስጥ የተፈጸመውን ከፍተኛ እልቂት ለጠ/ሚንስትሩ አቤት ለማለት ወደ አዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት  አካባቢውን በሚጠብቁ ልዩ ሃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከእስር ያመለጡ አንዳንድ ሽማግሌዎች በትናንትናው እለት ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከዚህ ቀደም በልዩ ሚሊሺው በቀጥታ የተገደሉትን የ47 ሰዎች ...

Read More »

በሀገረ-ማርያም የተፈቱት የሀገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮሚያ ክልል በቡሌ ሆራ ወረዳ፣ በሀገረማርያም ከተማ ከአርሴማ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ የተነሳውን የውስጥ ችግር ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላት ታስረው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በሁዋላ ህዝቡ ባሰማው ከፍተኛ ተቃውሞ የአገር ሽማግሌዎቹ በዛሬው እለት የተፈቱ ሲሆን፣ ህዝቡ በድል አድራጊነት ስሜት በሆታ አጅቦ ወደ ቤተክርስቲያን ወስዷቸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ ትናንት ረቡእ እንዲፈቱ ...

Read More »

በርካታ ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ ነው

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አሸባሪ ካላቸው ግንቦት ሰባት እና ሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ የአዲስ አበባና አማራ ክልል ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በጀመረው አዲስ አሰሳ በሀገሪቱ አንድንድ ቦታዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ ስልክ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም የመከላከያ ሀይል ተበትኗል፡፡ የዚህን ዜና ዝርዝር  በሌላ ጊዜ ...

Read More »

የአዲስ አበባ እድሮች ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በድጋሜ መዋጮ እንዲያዋጡ ታዘዙ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቲት 2፣ 2006 ዓም ከእድር ተጠሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እያንዳንዱ እድር በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እንዲከፍል ታዟል። ትእዛዙ የተጣለው የካቲት 2 ቀም 2006 ሲሆን፣ 650 እድሮች በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ይከፋላሉ። በዚሁ ከላይ በወረደው መመሪያ መንግስት ከእድሮች በአንድ ጊዜ 5 ሚሊዮን 200 ሺ ብር ...

Read More »