የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፉትን ሶስት የሥልጣን አመታት በህክምና ያሳለፉትና ከሳምንት በፊት በገዛ ፈቃዳቸው ከሃላፊነታቸው የተሰናበቱት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን ለማሳከም ክልሉ ከአንድ ሚሊየን አሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉ ተሰማ፡፡ በጰጉሜ ወር 2002 ዓ.ም ኦህዴድ ባካሄደው ጉባዔ ባልተጠበቀ መንገድ አቶ አባዱላ ገመዳን ተክተው ወደስልጣን የመጡት አቶ አለማየሁ በስራ ገበታቸው ላይ ብዙም ሳይሰነበቱ በመታመማቸው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ ካሃሰ ወ/ማርያም የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በከንቲባ ድሪባ ኩማ ፊርማ ተጽፎ በወጣው ደብዳቤ አቶ ካሓሰ ወ/ማርያም ከየካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር በቢሮና በኃላፊ ደረጃ ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል። “የተለያየ መ/ቤት ስያሜ እያወጡ እና ለህዝቡ ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተቋማትን ...
Read More »በኒውዚላንድ የኢሳትን የኔነው ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈዉ ቅዳሜ የካቲት 15፣ 2006 ዓም በ ኒዉዚላንድ አገር በኦክላንድ ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረዉ የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በሂደቱ በርካታ ችግሮች ተጋርጠውበት የነበረ ቢሆንም፣ ለአገራቸዉ ነፃ መዉጣትና ኢሳትን አሁን ካለበት እጥፍ አድጎ ማየት በሚፈልጉ ቀናኢ ኢትዮጵያዉያን ጥረት የገንዘብ ማሰባሰቡ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስተባባሪዎች ገልጸዋል። በርካታ ኢትዮጵያን የነበረዉን መሰናክል ...
Read More »መኢአድና አንድነት በጋራ የጠሩት የባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄ ነው ሲሉ አስተባባሪዎች ገለጹ
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት የመኢአድ ሰሜን ቀጠና አደራጅና የተቃውሞ ሰልፉ ግብረሃይል ለኢሳት እንደገለጹት የተቃውሞ ሰልፉን ለመከልከል መንግስት የተለያዩ መንገዶችን ቢጠቀምም፣ አስፈላጊውን መስዋትነት በመክፍል ቅስቀሳቸውን እያደረጉ ነው። የክልሉ መስተዳደር ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ፈቃድ መስጠቱንም አቶ ሽፈራው ተናግረዋል። የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ለማስተባበል የሞከሩት ህዝቡን ይበልጥ ማስቆጣቱንም ...
Read More »የአዲስአበባ አስተዳደር ጋዜጠኞች ለአባይ ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ሳይቀበሉት ቀሩ
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ጋዜጠኞችና ሠራተኞች ለአባይ ግድብ ቦንድ ግዥ በድጋሚ እንዲያዋጡ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ የአስተዳደሩ ሹማምንትና ካድሬዎች ከሁለት ዓመት በፊት ሠራተኛውን ካወያዩ በኃላ በራሳቸው ውሳኔ ሠራተኛው የአንድ ወር ደመወዙን በአንድ ዓመት ከፍሎ ለማጠናቀቅ እንደፈቀደ አድርገው በመገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ሰፊውን ሠራተኛ በማስቆጣቱ ወዲያውኑ ስብሰባ እንዲጠራለት በመጠየቅ ተቃውሞውን ...
Read More »በሱዳን ጎረምሶች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት በአንድ ወር ተቀጣች።
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድንጋይ ተወግራ ልትገደል ትችላለች በማለት የእንግሊዙ ዘ ጋርድያንና ኢንዲፕንደት የተባሉት ጋዜጦች ቢዘግቡም፣ የሱዳን ፍርድ ቤት ወጣቱዋን በአንድ ወር ብቻ ቀጥቷታል። ይሁን እንጅ ነፍሰጡር በመሆኗ ከእስር ነጻ ሆና ወደ አገሩዋ እንድትመለስ እና 4 ሺ የሱዳን ፓውንድ እንድትከፍል መወሰኑዋን ቢቢሲ ዘገበ። ከልጅቷ ጋር ጾታዊ ግንኙነት የፈጸሙት 3ቱ ወጣቶች 100 ጊዜ እንዲገረፉ፣ ፊልሙን በመቅረጽ ...
Read More »አልሸባብ በሱማሌው ፕሬዚዳንት ግቢ ውስጥ ጥቃት ፈጸመ
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጥቃቱ የሶማሊ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች ሲገደሉ ፕሬዚዳንቱና ጠ/ሚንስትሩ መትረፋቸው ታውቋል። አልሸባብ በፕሬዚዳንቱ ግቢ ውስጥ ወታደሮቹ እንደሚገኙ ቢገልጽም የሶማሊያ መንግስት ግን ሁሉም የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገድለዋል ብሎአል። አልሸባብ ከሞቃዲሾ ለቆ ቢወጣም በከተማዋ ውስት የሚፈጽመውን ጥቃት አላቆመም።
Read More »የብአዴን ድንጋጤና የእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ
የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የብአዴን የወጣቶች ሊግ ለአባለቱ የስልጠና እና የግምግማ ስራ በባህር ዳር ፤ ደሴ እና ጎንደር እያከናወነ ነው። የካቲት 16 አንድነትና መኢአድ በጋራ የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ በባህር ዳር ከተማ ባሉ ዘጠኝ ክፍለ ...
Read More »ረዳት ፓይለት ሃይለ-መድህን አበራ ብቃት ያለው አብራሪ ነው ተባለ
የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያን አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አውሮፕላን በመጥለፍ ጄኔቫ ያሳረፈው ሃይለመድህን አበራ፣ ከጸባዩ በተጨማሪ ብቃት ያለው አብራሪ መሆኑን ግለሰቡን የሚያውቁ ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ከስልጠና ጀምሮ የሚያውቁት ጓደኞቹ እንደተናገሩት ሃይለመድህን ለሰዎች ህይወት የሚጨነቅና ጥንቃቄ የሚያደርግ፣ አውሮፕላኑን ከጠለፈ በሁዋላ ተሳፋሪዎች ሳይቸገሩ እንዲያርፍ ማድረጉ የፓይለቱን ብቃት ያሳያል ብለዋል። ምንም እንኳ በረዳት አብራሪነት ደረጃ ...
Read More »የፌደራል ፖሊስ አባላት በአያያዛቸው ላይ ቅሬታቸውን አሰሙ።
የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባላቱ ቅሬታቸውን የሰነዘሩት በ2ኛው የመከላከያ ሰራዊት በአል ላይ ነው። በቀን አንድ ዳቦ እና ሁለት ጭልፋ ወጥ ለእራትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሚቀርብላቸው የመከላከያ ስራዊት አባላት፣ የቀን የምግብ ፍጆታ በጀታቸው ከህግ ታራሚዎች ያነሰ ነው። ወታደሮቹ በቀን ስምንት ብር ከሃምሳ ሳንቲም በሆነ የምግብ በጅትየሚተዳደሩ ሲሆን፣ የሚቀርብላቸውን ዳቦ እንኳን ለመብላት እንደሚቼገሩ እና ለምግብ እየተባለ በየወሩ ከደሞዛቸው ...
Read More »