.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሞቃዲሹ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ደረሰ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንዳደረሰው በሚገመተው የአጥፍቶ መጥፋት እርምጃ 12 የጸጥታ ሃኢሎች መገደላቸው ታውቋል። ጥቃቱ የጸጥታ ሃይሎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በፕሬዚዳንቱ ግቢ ውስጥ በደረሰ ጥቃት የሶማሊያ መንግስት ነባር የአመራር አባላት መገደላቸው ይታወሳል። አልሸባብ ከአፍሪካ አገራት በደረሰበት ጥቃት ሞቃዲሹን ለቆ ቢወጣም፣ በተደጋጋሚ እየወሰደ ባለው የፈንጅ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው።

Read More »

ብአዴን ባህርዳር ላይ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ እንዳይሳካ ለማድረግ የቀየሰው ስትራቴጂ ሳይሳካ መቅረቱን የውስጥ ምንጮች ገልጹ

የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ መዝለፋቸውን ተከትሎ አንድነት ፓርቲና መኢአድ የጠሩተን ሰልፍ ለማደናቀፍና ህዝብ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ የተቀየሰው ስትራቴጂ ሳይሳካ መቅረቱን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል። በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው ብአዴን ሰላማዊ ሰልፉን ለማጨናገፍ ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች አንዱ በአንጻራዊነት የተሻለ ተሰሚነት ያላቸውን ወደ አዲስ አበባ ከመጡት የክልሉን ተወላጅ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮችን መካከል ...

Read More »

በኦሮምያ የክልል ፐሬዚዳንት ለመሾም የሚደረገው ሽኩቻ ቀጥሎአል

የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ምክር ቤት ሳያቀውቀው በስራ አስፈጻሚው እውቅና ከስልጣን የተነሱትን አቶ አለማየሁ አቶምሳን ማን ይተካቸው የሚለው አጀንዳ የአቶ አባ ዱላ ገመዳንና የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ቡድኖች እያወዛገበ ነው። አቶ አለማየሁ አቶምሳ ወደ ስልጣን እንደመጡ የአቶ አባዱላን ቡድኖች በመምታት ከስልጣን ውጭ ያደረጉዋቸው ሲሆን፣ አባ ዱላ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ተመልሰው የእርሳቸውን ሰዎች ለማሾም እየሰሩ ነው። ...

Read More »

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ለተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችን የኢንፎርሜሽን መረቦችን የመሰረተልማት እንደሚዘረጋ ታወቀ

የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎችን የኢሜል መልእከቶች እና ሌሎችንም የመገናኛ ዘዴዎች በመሰለል ክስ እየቀረበበት የሚገኘው የኢትዮጵያ   የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችን ጋር ውል በመዋዋል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እያካሄ ነው። ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር የ70 ሚሊዮን ብር የኢንፎርሜሽን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ውል ተዋውሎ ስራ በመስራት ላይ ሲሆን፣ በአዋሳና ሌሎችም ...

Read More »

የአዲስአበባ የ24 ሰዓታት የቴሌቭዥን ስርጭት እቅድ ተግባራዊ መሆን አልቻለም

የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመገናና ብዙሃን ኤጀንሲ የመረጃ ውጤቶችን ለሕዝብ ተደራሽ ያደርግልኛል በሚል ከፍተኛ በጀት በመመደብ ባለፉት ዓመታት በአዲስአበባ ማዘጋጃ ቤት ሕንጻ ውስጥ ዘመናዊ ስቱዲዮና መሳሪዎች ግንባታና ግዥ ቢያከናውንም የ24 ሰዓታት ቴሌቪዥን አገልግሎት ዕቅዱን በአቅም ማነስ ምክንያት ማሳካት ሳይችል ቀርቷል፡፡ የኦሮሚያ፣ የአማራ እንዲሁም የሶማሌ ክልሎች በዓረብ ሳተላይት ላይ ጭምር የክልሎቻቸውን ዜናዎችና መረጃዎች ...

Read More »

የስዊስ አቃቢ ህግ የረዳት ሃይለመድህን አበራን ሰብአዊ መብቶች ያከብራል ሲሉ ቃል አቀባዩዋ ተናገሩ

የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰዊስ አቃቢ ህግ ቃል አቀባይ ሚስ ያኔት ባልመር በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ የምርመራ ሂደቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ገልጸው፣ የሰብአዊ መብቱን በመጠበቅ በኩል ለተነሳው ጥያቄ ግን ስዊዘርላንድ የሰብአዊ መብቶችን በጠበቅ በኩል ታዋቂ አገር መሆኑዋን በመግለጽ የሃይለመድህንን የሰብአዊ መብቶች እንደሚያከብሩ ገልጸዋል። ሃይለመድህን ጠበቃ ተቀጥሮለት ጉዳዩን ...

Read More »

ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ በአባይ ግድብ ግንባታ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ሪፖርተር ዘገበ

የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጣው በእሁድ እትሙ እንደገለጸው ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ” በህዳሴው ግድብ ላይ 60 ከመቶውን የትራንስፖርት፣ ሎጂስቲክና አፈር የማንሳት ሥራዎችን ከሳሊኒ በተቋራጭነት በመውሰድ እየሠራ እንደሚገኝም ባለፈው አመት ኩባንያው በቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ በወ/ሮ አቲኮ ስዩም አምባየ መመስረቱን ፣  በግልገል ጊቤ አንድ እና ግልገል ጊቢ ሁለት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ...

Read More »

በአርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከስራ ተባረሩ

የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው አባላት በመንግስት ስራ ውስጥ ድርሻ አይኖራችሁም ተብለው መባረራቸውን የተባረሩ የፓርቲው አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። አብዛኞቹ ለሱዳን እየተሰጠ ያለውን መሬት በተመለከተ ተቃውሞ በማሰማታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል። የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አንጋው ተገኝ፣ በድንበር ጉዳይ ጥያቄ በማንሳታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል ከተባረሩት የፓርቲው አባላት መካከል አወቀ ብርሃኑ፣ አባይ ዘውዱ ፣ አንጋው ተገኝ፣ አብርሃም ...

Read More »

መንግስት ኢማሞችን በመሾም በኩል ጣልቃ መግባቱን የሚያሳይ መረጃ ይፋ ተደረገ

የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማህበራዊ ድረገጾች የተለቀቀው ይህ መረጃ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ አበባ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበ ነው።  ወንጀል ዝርዝር በሚለው ክፍል ውስጥ ” 2ኛ ተከሳሽ መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም፣ ሳይፈቀድለት የነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊ ሙስሊም እንዳይሰገድ በማድረግና መስኪዱ በመታወቁ በወና ወንጀል አድራጊነት ተከሷል” ይላል ምንም እንኳ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ...

Read More »

“የባህርዳር ህዝብ አንግቦ የተነሳው በአገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የለውጥ ጥያቄ ነው” ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ28 አመቱ ሙላት የመሸንቲ ነዋሪ ነው፤ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘሁት በአገዛዙ ተማርሬ ነው ይላል። ለምን ተማረርክ በማለት ዘጋቢያችን ላቀረበችለት ጥያቄ፣ “ምን የማያስመርር ነገር አለ፣ ሁሉም ነገር እየተበላሸ እንጅ እየተሻሻለ ሲሄድ አታይም፣ ይህም አልበቃ ብሎ ይዘልፉናል” በማለት በሰልፉ ላይ የተገኘበትን ምክንያት ገልጿል። የባህርዳር ነዋሪዎች አንድነትና መኢአድ በጋራ በጠሩት ሰልፍ ላይ በነቂስ ወጥተዋል። ...

Read More »