.የኢሳት አማርኛ ዜና

10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ተገደሉ

አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው 10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮ -ሱዳን ድንበር አካባቢ ከተገደሉ በሁዋላ በድንበር አካባቢ ውጥረት ሰፍሯል። እሁድ እለት ደግሞ ተጨማሪ 13 የሱዳን ወታደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ጥቃቱም በኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ሳይፈጸም እንዳልቀረ ተዘግቧል። የሱዳን ኮማንዶ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሃይሉን እያሰባሰበ መሆኑን የገለጸው ዘገባው፣ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መካሄዱን ጠቅሷል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ከተሞቻቸውን ከታጣቂዎች ጥቃት ለመከላከል በሚል  አንዱ ...

Read More »

“እንደ ከሳሾቼ 100 ሺ የማከራየው ቤት የለኝም” ሲሉ አቶ ገብረውሃድ ተናገሩ

መንግስት በሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ የእምነት ክህደት ቃላቸውንለፌዴራልከፍተኛፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ገብረውሃድ “በኢትዮጵያቴሌቪዥን 16 ቤትአለውተብሎበካሜራተቀርፆመነገሩየሚያሳዝንመሆኑን ፣ እርሳቸውበአዲስአበባውስጥአንዲትጐጆእንደሌላቸውና ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸው መጠለያ እንደማያጡ ተናግረዋል። ‹‹እንደከሳሾቼ 100,000 የማከራየውቤትየለኝም፤›› በማለት ንጽህናቸውን ለማስረዳት የሞከሩት አቶ አቶ ገብረውሃድ፣ ከሳሾቼ ያሉዋቸውን ሰዎች  በስም ከመጥቀስ ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ” ለአንድነታችን በጽናት እንቆማለን” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት የረመዳንን ጾም ጀመሩ

ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሰላማዊ ተቃውሞ ታሪክ ውስጥ ረጅም ጊዜ በማስቆጠር ክብረወሰን የሰበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ፣  በረመዳን ጾም መግቢያም ” በአንድነታችን እንጸናለን” በሚል መፈክር ተካሂዷል። እንደወትሮው ሁሉ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአንዋር መስጊድ በተካሄደው  የጸሎት ስነስርአት፣ ሙስሊሙ “በአንድነታችን እንጸናለን” የሚሉ በወረቀት ላይ የተጻፉ መፈክሮችን ከፍ አድርጎ በማሳየትና እጅ ለእጅ በመያያዝ መልእከቱን አስተላልፏል። ዝግጅቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ...

Read More »

በሃረር ታስረው ከሚገኙት መካከል የ3ቱ የዋስትና መብት ተከበረ

ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በሃረር ከተማ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ከታሰሩት ነጋዴዎች መካከል የዋስትና መብት ተከልክለው የነበሩት በቢንያም መንገሻ መዝገብ የተከሰሱት 3ቱ ነጋዴዎች በ20 ሺ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጥቷል። ነጋዴዎቹ ያወስትና መብት መከልከላችን ትክክል አይደለም በሚል ይግባኝ ብለው ነበር። በሌላ መዝገብ የተከሰሱት 21 ተከሳሾች ደግሞ ዳኛ አልተሟላም በሚል ለፊታችን ሃሙስ ሰኔ 25 ...

Read More »

የደመወዝ ጭማሪው ጡረተኞችን ስለማካተቱ አለመነገሩ ጡረተኞችን አሳስቦአል

ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርም ደሳለኝ የሲቪል ሰርቪስ ቀንን በማስመልከት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ከሃምሌ 1 ቀን 2006 ኣ.ም እንደሚደረግ ሲገልጹ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጡረተኞችን ጭማሪው ስለ መመልከቱ አለመነገሩ እንዳሳሰባቸው አንዳንድ ያነጋገርናቸው ጡረተኞች ገለጹ፡፡ በአጼው ዘመነ መንግሥት ሰዎች በስራ ላይ እያሉ ጉልበታቸው ሳይደክም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ...

Read More »

የቀድሞ የሶቭየት ህብረት ግዛቶች የአውሮፓ ህብረትን ሊቀላቀሉ ነው

ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጦርነት ውስጥ የምትገኘዋ ዩክሬን፣ ጆርጂያና ሞልዶቫ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ አገሮቹን  በሂደት የህብረቱ ሙሉ አባል  ያደርጋቸዋል። የሩሲያው መሪ ቭላድሜር ፑቲን ውሳኔውን አጥብቀው ሲቃወሙት፣ ስምምነቱ አገሮቹን ከሁለት እንደሚከፍላቸው አስጠንቅቀዋል። አዲሱ የዩክሬን መሪ ስምምነቱን ታሪካዊ ሲሉ አወድሰውታል። የአውሮፓ ህብረት ካውንስል ፕሬዚዳንት ቫን ሮምፑይ በበኩላቸው  ስምምነቱ ለአውሮፓ ታላቅ ድል ነው ብለዋል።

Read More »

ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የሃረር ውሃ ፕሮጀክት መክኖ መቅረቱን መረጃዎች ጠቆሙ

ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከክልሉ ውሃ ልማት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የሃረር ከተማን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በሚል በተለያዩ ወቅቶች ከ747 ሚሊዮን 175 ሺ ብር በላይ ወጪ ቢደረግም አብዛኛው ፕሮጀክቶች በመክሰማቸው የከተማው ህዝብ ለአሳሳቢ የውሃ ችግር ተዳርጓል። የከተማውን የውሃ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ከፍተኛ ግምት የተጣለበት የሃሰሊሶ መስመር መጠናቀቁን ተከትሎ ለምረቃ የተዘጋጀው መጽሄት  ” ውሃ በፈረቃ ድሮ ቀረ!” በሚል ...

Read More »

የደሞዝ ጭማሪ እንደሚኖር መነገሩን ተከትሎ የእቃዎች ዋጋ ወደ ላይ እየወጣ ነው

ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሃምሌ ወር መጨረሻ የደሞዝ ጭማሪ ይኖራል በማለት ከተናገሩ በሁዋላ ደሞዙ ሳይለቀቅ፣ የቤት ኪራይ እንዲሁም የምግብ እና የአላቂ እቃዎች ዋጋ ጭማሬ እያሳየ ነው። ጭማሪው በመላ አገሪቱ የሚታይ ሲሆን በአንዳንድ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሚባል ጭማሪ እየታየ ነው። መንግስት ስለጭማሪው ተጨማሪ ማብራሪያ ባይሰጥም፣ ነጋዴውና ቤት አከራዮች ጭማሪ በማድረጋቸው የደሞዙን ጭማሪ ለማየት በሚጓጓው ...

Read More »

የኦሮምያ ክልል ራዲዮና ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች አባረረ

ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ 17 ጋዜጠኞች ከስራ መባረራቸው ተገልጾላቸዋል። ጋዜጠኞች የተባረሩበት ዝርዝር ምክንያት ባይታወቅም፣ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ተቃውሞ እንዲሁም ባህርዳር ላይ ተደርጎ ከነበረው የስፖርት ዝግጅት የቀጥታ ስርጭት ጋር በተያያዘ ሳይሆን አይቀርም። ቀድም ብሎ ውስጣዊ ግምገማዎች ሲካሄዱ እንደነበር የኢሳት የመረጃ ምንጮች ጠቁመው፣ 6 የሚሆኑ ጋዜጠኞች ቀደም ብለው እንዲታገዱ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበርኞች ግንባር ሰራዊት በወልቃይት ድል መቀዳጀቱን ገለጸ

ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 16፣ 2006 ዓ/ም በወልቃይት አድነጣ በተሰኘ ስፍራ በስርዓቱ የሚሊሻ ታጣቂ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ 18 ገድሎ ቻለው ሲሳይ  እና  ተጫነንጉሱ የተባሉ 2 ወታደሮችን መማረኩን አስታውቋል። ሰራዊቱ ለሁለቱም ምርኮኞች ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታና ስለድርጅቱ አላማና ግብ በማስተማር እንደለቀቃቸውም ድርጅቱ ገልጿል። ሰኔ 18-2006 ዓ/ም ደግሞ   የኢሕአግሰራዊት ከመንግስት የልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር በወልቃይት አወርቂ በተባለ ቦታ ከጠዋቱ ...

Read More »