ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በአንድ ወር ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የአመራሩ ሚስጢሮች ተላልፈው የተሰጡበትና በአደገኛ ሃይሎች እጅ የወደቁበት ሁኔታ መከሰቱን ፣ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተወስቷል። 3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ትናንት ሲጠናቀቅ ብአዴንና ደኢህዴን በከፍተኛ ድክመት ውስጥ እንደሚገኙና ከዚህ ድክመታቸው በአስቸኳይ እንዲወጡ እርምጃ እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። በዝግ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
መንግስታዊው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የእስር ቤት አያያዝን የሚተች ሪፖርት አቀረበ
ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያሰብዓዊመብትኮምሽን «በጥበቃሥርያሉሰዎችመብትአከባበርበኢትዮጵያፖሊስ ጣቢያዎች» በሚልርዕስባካሄደውየዳሰሳጥናትጣቢያዎቹለእስረኞችእንደምግብ፣ውሃ፣ መኝታና፣ሕክምና እና የመጸዳጃ አገልግሎቶችበመንግስትወጪማሟላትየነበረባቸው ቢሆንምከፍተኛጉድለቶች በጥናቱማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የዳሰሳጥናቱሰሞኑንበአዳማጀርመንሆቴልይፋበሆነበትወቅትእንደተጠቆመውየዳሰሳጥናቱ በሁሉምክልሎች በሁለትከተማአስተዳደሮችበአ/አእናድሬዳዋከሚገኙ 1ሺህ 81 ፖሊስ ጣቢያዎችውስጥበ170 ዎቹመካሄዱንጠቅሶግኝቱንአስቀምጧል፡፡ በዚሁመሠረትፖሊስጣቢያዎቹውስጥከሚገኙየተጠርጣሪእስረኞችመቆያክፍሎች አብዛኛዎቹደረጃቸውንያልጠበቁ፣እንደፍራሽናአልጋያሉመተኛዎችያልተሟሉላቸውናበእስረኞች የተጨናነቁ ናቸው፡፡የህክምናወጪበመንግስትየሚሸፈንላቸውበአዲስአበባእናበድሬደዋ በሚገኙፖሊስጣቢያዎች ለታሰሩት ብቻሲሆንበሌሎችክልሎችይህአገልግሎት አለመኖሩተመልክቷል፡፡ ጥናቱአያይዞምየእስረኞችቃልንበዛቻበማስፈራራትናአካላዊጥቃትበመፈጸምመቀበል በፖሊሶችናመርማሪዎችየተለመደአሰራርመሆኑንከማመልከቱምበላይበሕጉመሠረትበ48 ሰዓታትፍርድቤትየማይቀርቡእስረኞችመኖራቸውንምአጋልጧል፡፡ በተጨማሪምጥናቱየተካሄደባቸውየፖሊስጣቢያዎችበዘመናዊመረጃአያያዝበኩልችግር እንዳለባቸው፣የበጀት እጥረት፣የቁሳቁስናየሰውኃይልአለመሟላትአገልግሎትአሰጣጣቸው ላይአሉታዊተጽዕኖ ማሳረፉንጠቁሟል፡፡ ጥናቱእንደመፍትሔካስቀመጣቸውነጥቦችመካከልበጣቢያዎቹየሚመደበውበጀትናየሰው ኃይልማሻሻልእንደሚገባ ይመክራል፡፡በተጨማሪምሴቶች፣ከእናቶቻቸውጋርያሉሕጻናት፣ ወጣትተጠርጣሪዎች፣ የአእምሮወይንምየአካል ጉዳትያለባቸውተጠርጣሪዎችበቂድጋፍእንዲገያኙመደረግአለበትብሏል፡፡ የኢትዮጵያሰብዓዊመብትኮምሽንበሕገመንግስቱየሰፈሩመብቶችንናኢትዮጵያተቀብላ ያጸደቀቻቸውዓለምአቀፍ የሰብኣዊመብትድንጋጌዎችተፈጻሚመሆናቸውንእንደሚ ከታተልየተጠቀሰሲሆንየዚህን የዳሰሳጥናትውጤትጠቅላይ ሚኒስትሩንጨምሮለሚመለከታቸውአካላትናለዓለምአቀፍተቋማት መላኩተጠቅሷል፡፡
Read More »በማዳበሪያ እዳ ከታሰሩት ውስጥ ሶስቱ ላይ ከፍተኛ ድበደባ ደረሰባቸው
ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቦንኬ ወረዳ ላታ ቀበሌ ከታሰሩት 9 አርሶደአሮች መካከል 3ቱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። አዳነ አለማየሁ፣ አስኔ አለማየሁ፣ ክልክሌ አባ፣ ልልቱ ኮዳ፣ አይማ ዳዳ፣ ጋላሂ ጋሞ፣ ዳንኤል ጉዳ፣ አብሌ አለማየሁ እና አባተ እንዳለ የተባሉት አርሶአደሮች “ተጨማሪ ማዳበሪያ አንፈልግም ቀድሞ ለወሰድነውም እዳችንን ለመክፈል አልቻልንም” በማለታቸው መታሰራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ሙና ሄና፣ ካንጅራ ...
Read More »የወረዳው ገንዘብ ያዥ ገንዘብ ይዘው ተሰወሩ
ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃድያ ዞን ሚሻ ወረዳ ሞርሲጦ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አባይነህ ቁጥሩበውል ያልተወቀ ከፍተኛ ገንዘብ ይዘው መጥፋታቸውን የኢሳት አካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። አቶ አባይነህ ገንዘቡን ይዘው እንደጠፉ ስልክ ሲደወልላቸው ” የድርሻየን ወስጃለሁ” የሚል መልስ መስጠታቸውንና ስልካቸውን ማጥፋታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ለወረዳው ስራ ማስኪያጃ የሚውለውን ገንዘብ ይዘው በመጥፋታቸው የወረዳውን ስራ ለማካሄድ ችግር መፍጠሩን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል። ግለሰቡን ለመያዝ ...
Read More »የኢትዮጵያመንግስትየሚፈጽማቸውን ወንጀሎች ለዓለም ማህበረሰብ የማጋለጥ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት በተከታታይ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎችለዓለምማህበረሰብየማጋለጥተግባርበተለያዩሃገሮችበተለይምየአቶአንዳርጋቸውጽጌንህገወጥእገታተከትሎተጠናክሮቀጥሏል።ሰላማዊሰልፎች አሁንምበበርካታከተሞችእየተደረገሲሆንበጀርመንየሚኖሩኢትዮጵያዊያንየኢትዮጵያውንገዢስርዓት ህገወጥተግባራትየሚያስረዱጽሁፎችንአዘጋጅተውለጀርመንነዋሪዎችእያዳረሱሲሆንየጀርመንመንግስት ለኢትዮጵያመንግስትየሚሰጠውንእርዳታከሰብዓዊመብትአኳያእንዲያጤንየሚጠይቅፊርማም እያሰባሰቡይገኛሉ። በሌላ ዜና ደግሞ ግንቦት7 በሜልቦርን ስብሰባ ማካሄዱን ዘጋቢያችን ኤልሳቤጥ ግዛው ከአውስትራሊያ ዘግባለች
Read More »የቀድሞው የጋምቤላ መሪ በክልሉ ለደረሰው ጭፍጨፋ የህወሃት ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረጉ
ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኦሞድ ኦባንግ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ 400 ሰዎች የተገደሉበት የጋምቤላወኢ ጭፍጨፋ እንዴት እንደተከናወነ በዝርዝር አስረድተዋል። የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አባይ ጸሃየ ግድያውን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በክልሉ ስለሚፈጸመው ሙስናና የመሬት ወረራ የቀድሞው ባለስልጣን በዝርዝር ገልጸዋል። አቶ አዲሱ ለገሰ በቅርቡ ባወጡት ጽሁፍ በጋምቤላ ለኢህአዴግ ታማኝ የሆነ ሰው ለማግኘት እንዳልተቻለ ገልጸው ነበር። አቶ ኦሞድ ...
Read More »ገዢው ፓርቲ ለመንግስት ሰራተኛው የፖለቲካ ስልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱ ታወቀ
ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ የኢህአዴግን ፖሊሲዎች ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለዳኞችና አቃቢያን ህጎች፣ ለፖሊሶች እንዲሁም ለኢህአዴግ የተለያዩ ፎረም አባላት ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና ለመንግስት ሰራተኛው በሙሉ ለመስጠት ማቀዱ ታውቋል። እስካሁን ድረስ በተካሄዱት ስልጠናዎች ኢህአዴግ ከአባላቱ ጭምር ሳይቀር ከፍተኛ የጥያቄ ናዳዎችን ሲያስተናግድ የቆየ ቢሆንም፣ ውይይቱን ከማቋረጥ ይልቅ ወደ መንግስት ሰራተኛው በማውረድ አስፋፍቶ ለመስጠት ማቀዱን ምንጮች ገልጸዋል። በተለያዩ የማሰልጠኛ ጣቢዎች ...
Read More »በሆሳ እና የከዱ ወታደሮች አባላቸውን አስፈቱ
ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመከላከያ ሰራዊት የከዱ 10 የሚደርሱ ወታደሮች ከሆሳእና ከተማ ባለስልጣናት ጋር የፈጠሩትን ውዝግብ ተከትሎ፣ አንድ የከተማው የምክር ቤት አባል በደረሰበት ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ አንደኛው ወታደር ሲያዝ ቀሪዎቹ አምልጠዋል። ይሁን እንጅ ወታደሩ ነሃሴ 30 ቀን 2006 ዓም ታይዞ መታሰሩን የገለጹት ምንጮች፣ ያልተያዙት ወታደሮች በምሽት እስር ቤቱን በመስበር ባልደረባቸውን አስፈትተው ማምለጣቸው ታውቋል። በተለያዩ ...
Read More »የአፍሪካህብረትሰላምአስከባሪሀይልአባላትየሶማሊያሴቶችን በመድፈርተከሰሱ
ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ፦ሂዩማን ራይትስ ዎችን በመጥቀስእንደሰገበውውሃእናህክምናፍለጋቀያቸውንለቀው ወደሞቃዲሾየሰላምአስከባሪሀይሉወደሰፈረበትካምፕየሄዱየሶማሊያ ልጃገረዶችናሴቶችበህብረቱየሰላምአስከባሪሀይላትበሀይልተደፍረዋል። አንዲትየ 15 ዓመትሙስሊምወጣትልጅ ከአንገቱዋበላይየተሸፋፈነች በትንልብስበሀይልእንድታወጣናእንድት ገላለጥከተደረገችበሁዋላ መደፈሩዋንየሰብዓዊመብትተቁዋሙጠቅሱዋል። በሶማሊያ አልሸባብንናአክራሪእስላሚስቶችንለመዋጋትወደ 22 ሺህጦርያሰፈረውየአፍሪካህብረትየሰብዓዊመብትተቁዋሙየመሰረተውን ክስአስመልክቶ ማጣራትእንደሚያደርግአስታውቁዋል። የመንግስታቱድርጅትየስደተኞችጉዳይከፍተኛኮሚሽንሪፖርትእንደሚያመለክተው በ2012 ብቻ ከቀያቸውበተፈናቀሉ 1700 የሶማሊያሴቶችላይየአስገድዶመድፈርወንጀልመፈጸሙተመስግቡዋል። ባለፈውዓመት አንዲትየሶማሊያሴትበህብረቱሰላምአስከባሪናበሶማሊያ ጦርአባላትበጋራመደፈሩዋንተከትሎከፍተኛውስግብተነስቶእንደነበር ቢቢሲአስታውሱዋል። የመደፈርአደጋእያጋጠማቸውያሉትአብሳኞቹሴቶችበተለይከ2011 ጀምሮ እያየለበመጣውየእርስበርስግጭትና በድርቅምክንያትከቀያቸውተፈናቅለው ወደተለያዩመጠለያካምፖች የገቡናቸው። የአፍሪካህብረትየሶማሊያሰላምአስከባሪልኡክከእንግዲህእንዲህያለውንነገር አላየኹምብሎዓይኑንሊጨፍንአይችልም፤ይህንድርጊትማድበስበስ በአካባቢው በዋነኝነትየተሰለፈበትንሰላምየማስከበርአላማን ዋጋያሳጣዋል” ብለዋል- የሂዩማንራይትስዎችየሴቶችጉዳይዳሬክተርሊየስልጌርንቶልትስ። ከ 12 ዓመትጀምሮያሉ 21 ሴቶችበተደረገላቸውቃለ-ምልልስአብሳኞቹበኡጋንዳናበብሩንዲወታደሮችእንደተደፈሩመናገራቸውን የቢቢሲሰገባያመለክታል።
Read More »ኢህአዴግ በአንድ አመት ውስጥ ለተለያዩ ዝግጅቶች ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱ ተሰማ
ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለፈው አንድ አመት ውስጥ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለፓርቲው የፖለቲካ ስራ የሚጠቅም ከመንግስት ባጀት ከ900 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ማውጣቱን ምንጮች ገለጹ። ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን፣ ለባንዲራ ቀን፣ ለመከላከያ ቀን፣ ለተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የፖለቲካ ስልጠና፣ ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ የኢህአዴግ አባላት ስልጠና፣ ለፖሊስ ሰራዊት የተሰጠው ስልጠና፣ እንዲሁም በተለያዩ ታሃድሶ የሚል ስያሜ በተሰጣቸው ስልጠናዎችና ስብሰባዎች ከመንግስት ...
Read More »