መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ ማድረጉን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ የሸዋስ ከጳጉሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአዳማ ምክትል ከንቲባ ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ሳምንት በፊት ለአጭር ቀን ስልጠና ወደ አሜሪካ ለመብረር ዝግጅታቸውን ጨርሰው ቦሌ አየር ማረፊያ የተገኙት ምክትል ከንቲባው፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ከአገር እንዳይወጡ ተደርጓል። ዋናው ከንቲባና አንድ ባለሙያ ስልጠናውን ተካፍለው መመለሳቸው ታውቋል። ምክትል ከንቲባው የእስልምና እምነት ተከታይ እና በኦነግ አባልነት እንደሚጠረጠሩ ምንጮች ገልጸዋል። በከንቲባውና በምክትሉ መካከል የተፈጠረው ልዩነት እየሰፋ መምጣቱም ይነገራል። ምንጮች እንደሚሉት ...
Read More »በሞያሌ ለተነሳው ግጭት ተጠያቂ የተደረጉ ተፈረደባቸው
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት አመት በኦሮምያና በሶማሊ ክልሎች የድንበር ከተሞች የተነሳውን ግጭት መርተዋል የተባሉና ቁጥራቸው በውል ላልታወቀ ዜጎች ሞትና ለንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የሞያሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች 29 ሰዎች እስከ 19 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። 21 ተከሳሾች በሌሉበት ሲወሰንባቸው የሞያሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጉዩ ዋርየን በ14 አመት፣ ዳማ ዱዮን የተባሉት ደግሞ ...
Read More »በ 2007 ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2007ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ድምፁን እንዳይሰጥ ለማፈን በሚያስችል ሁኔታ በክልሉ የሚገኙ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ሚሊሽያ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ ሰሞኑን ለታማኝ አመራሮች በሰጡት ድርጅታዊ መግለጫ ላይ በያዝነው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ህዝቡ የተለያየ ፅንፍ በመያዝ ገዢው ፓርቲ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ ...
Read More »የተከፋፈሉት የሶማሊ ክልል ስራ አስፈጻሚ አባላት አንዱ ሌላውን ከስልጣን ማገዳቸውን አስታወቁ
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት የሶማሊ ክልል መሪዎች፣ የደህንነት ሃላፊዎችና በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በተገኙበት በተደረገው ግምገማ በፕሬዚዳንቱ አብዲ ሙሃመድ ላይ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ከቀረቡ በሁዋላ ፣ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ በሚፈልጉት የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና በክልሉ የመከላከያ ሹም ጄኔራል አብርሃ መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። ውሳኔ ለመስጠት የተቸገሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ ግምገማው ...
Read More »ባለፈው አመት በርካታ የመካላከያ ሰራዊት አባላት መልቀቃቸውን ወታደሮች ገልጹ
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጳጉሜ ወር የመከላከያ ሰራዊትን ጥለው የጠፉ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ በጠጠናቀቀው አመት በርካታ ወታደሮች እየለቀቁ የተቃዋሚ ድርጀቶችን ከመልቀቅ ባሻገር ወደ ማሃል አገር እየሄዱ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው። የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ትወስዳለህ ተብሎ ያለፍለጎቱ መከላከያን የተቀላቀለና ባለፈው ሳምንት መስሪያ ቤቱን በመልቀቅ የግል ኑሮውን ለመምራት የፈለገ ወታደር እርሱ በነበረበት የሁመራ እና በአድሜ አካካቢዎች በሰራዊቱ ላይ ...
Read More »በጋምቤላ የተነሳውን ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመዠንገር ብሄረሰብ ተወላጆች ጎደሬና ሜጫ በሚባሉት አካባቢዎች እንደ አዲስ በጀመሩት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስካሁን አስከሬኖች እንዳልተነሱ የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከጋምቤላ ብሄረሰብ ውጭ ያሉ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች በሙሉ ይወጡ በሚል የተጀመረው ግጭት ፣ ደም አፋሳሽ ሆኖ ከመቀጠሉ ባሻጋር፣ በትናንትናው እላት ብቻ ከ1 ሺ ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለው ቴፒ ከተማ መግባታቸው ታውቋል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት ...
Read More »በሽብርተኝነት የተከሰሱት አርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ተወሰዱ
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሆነው ለግንቦት7 የአርባ ምንጭና አካባቢው ወጣቶችን በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካሉ በሚል ጥርጣሬ ተይዘው ለሳምንታት በአርባ ምንጭ እስር ቤት ታስረው የቆዩት የፓርቲው የአርባ ማንጭ ምክትል ሰብሳቢ በፍቃዱ አበበ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ኢንጂነር ጌታሁን ወደ ማእከላዊ እስር ቤት መወሰዳቸውን የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጸዋል። ኢንጂነር ጌታሁን በየነ ቀደም ብሎ ...
Read More »በባጃጅ መኪና ንግድ የተሰማሩ የውጭ አገር ዜጎችና አንድ ኢትዮጵያዊ ተከሰሱ
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢ ህግ በ17 የጅቡቲ፣ ህንድ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ሲሪላንካና እና አሸራፍ አወል አብዲ በሚባል ኢትዮጵያዊ ላይ በመሰረተው ክስ፣ ግለሰቦቹ ለኢትዮጵያውያን በተፈቀደው የንግድ ስራ ህገወጥ በሆነ መንገድ በመነገድ መንግስት ማግኘት የነበረበትን 700 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ እንዲያጣ አድርገዋል ብሎአል። በክሱ ዱባይ ኦቶ ጋላሪ ኤል ኤል ሲ እና ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያ ሰራተኞች የሆኑት 2 የሲሪላንካ ዜግነት ...
Read More »የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው
መስከረም ፩(አንድ)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሉ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተከበረ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያውያን ስልክ በመደወል የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክቶችም አስተላልፈዋል ከበአሉ ጋር በተያያዘ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች መከናወናቸውን የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። በበአሉ ዋዜማ ወቅት ከፍተኛ አደጋ የታየው በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ዞን በጎሸም ቀበሌ ሲሆን፣ የመዠንገር ብሄረሰብ አባላት 9 ሰዎችን ገድለዋል። ግጭቱ አሁንም ድረስ የቀጠለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ...
Read More »