ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀፈው ትብብር ባወጣው መግለጫ የባህርዳር ከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት መቅጠፉን አስታወሶ፣ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል ማጉደል ማድረሱ፣ በምንም መለኪያና ሁኔታ፣ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን አስጠነቀቁ
ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋር በቀጥታ እየተገናኙ የሀገራችንን ጥቅምና ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አሉ ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፓለቲካ ፓርቲ አባላት እየታሰሩ መሆናቸውን አስመልክቶ በቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አሸባሪ ከሚባሉ ቡድኖች በቀጥታ እየተገናኙና እያቀዱ ሀገር ለማሸበር እየዶለቱ የሚውሉ ሃይሎች መሆናቸውን ...
Read More »የገዢው መንግስት ወታድሮች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ እንዲቆም የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ፡፡
ታኀሳስ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትላንትናው እለት በባህርዳር ከተማ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ የገዢው መንግስት ወታደሮች በህዝቡ ላይ እያደረሱ ያለውን ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ የባህርዳር ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች በአስቸኳይ እንዲያቆም በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የሃይማኖት አባቶችን ከሁለት ቀን በፊት በመሰብሰብ በመስቀል አደባባይ ላይ ሊሰሩት ያሰቡትን ጉዳይ እንዳወያዩዋቸው የገለጹት የሃይማኖት አባቶች ይህንን ጉዳይም ለሚመለከታቸው የእምነቱ ተከታዮች ...
Read More »በባህር ዳር ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ ፡፡
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለምዶ የመስቀል አደባባይ ተብሎ የሚጠራውን የታቦት መውረጃ ቦታ ለግል ባለሃብቶች ለመሸጥ ታስቧል በሚል ሰሞኑን እንቅስቃሴ በጀመረው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የከተማ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ድርጊት የተቆጡት የከተማዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እና በፖሊስ መካከል በተነሳው ግጭት ከ 3-5 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል፡፡ 27 ሰዎች ታስረው እየተደበደቡ ነው። የእምነቱ ተከታዮች በከተማው መካከል ...
Read More »በታላቁ የኑር መስጊድ ድንገተኛ ተቃውሞ ተደረገ
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድንገተኛ ተቃውሞው የተካሄደው በመላ አገሪቱ ያለውን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብት ጥያቄን በሃይል መቆጣጠራቸውን የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያምንና አዲስ አበባ መስተዳድር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ባስታወቁ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። ዶ/ር ሽፈራው ሙስሊሙ በአደባባይ የሚያደርገውን ተቃውሞ ማቆሙንና ሌላ ስልት መጠቀም መጀመሩን ተናግረው ነበር። ይሁን እንጅ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም ሲያደርገው እንደበረው ማስታወቂያዎችን በማህበራዊ ...
Read More »በአጋሮ 4 የታጠቁ የፖሊስ አዛዦች ዝርፊያ በመፈጸም ሂደት ላይ አንድ ነጋዴ ገደሉ
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በጅማ ዞን ኤዳ ደሌ ቀበሌ ታዋቂ ቡና ነጋዴ የሆኑት አቶ ነፍሶ ላቫዥ ለዝርፊያ በሄዱ በአራት የፖሊስ አመራሮች ተገድለዋል። አቶ ነፍሶ ጅማ ውስጥ ቡና ነግደው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ አድብተው ይጠብቁዋቸው የነበሩት ፖሊሶች የያዙትን ገንዘብ እንዲሰጧቸው ሲጠይቋቸው ነጋዴው ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረቸው ፣ ሊያጋልጡን ይችላሉ በሚል ተኩሰው በመግደል ለማምለጥ ከሞከሩ በሁዋላ በህዝቡ ...
Read More »ምርጫውን አስታኮ ለፖሊሶች የማእረግ እድገት እየተሰጠ ነው
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር ሰሞኑን ለክልሉ 5ሺ473 ፖሊሶች የሰጡት የማዕረግ ዕድገት መጪውን ምርጫን በመንግስት መዋቅር፣ በጀትና ጊዜ ተጠቅሞ ለማሸነፍ ኢህአዴግ የዘረጋው ስትራቴጂ አካል እንደሆነ ታዛቢዎች ተናገሩ፡፡ መጪው ምርጫ ሊካሄድ አምስት ወራት ብቻ በቀሩት በዚህ ጊዜ የማእረግ እድገት በብዛት መስጠት ለምርጫ ከሚሰጥ የጉቦ ቀብድ ተለይቶ አይታይም ያሉት ሰማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ምሁር በዚህ ...
Read More »ነዳጅ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት በሰሜንና በደቡብ የአገሪቱ ክፍሎች የነዳጅ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል፡ በአዋሳ ነዳጅ ለመቅዳት መኪኖችና ሞተረኞች ተሰልፈው ሲጠባባቁ ታይቷል። የነዳጅ ዋጋ በመላው አለም በከፍተኛ ደረጃ ቢቀንስም በኢትዮጵያ መጥፋቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል።
Read More »በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የተገዙ የማምረቻ መሳሪያዎች በኤሌክትሪክ ሃይል ችግር ከአገልግሎት ውጭ እየሆኑ ነው ሲሉ ሚኒስትር አለማየሁ ገለጹ
ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውሃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ህዳር 26 ቀን 2007፣ በቁጥር ውመአሚ 1/01/67 በጻፉት ደብዳቤ ” በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው ለበርካታ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያና መሸጫ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎችና ሼዶች በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ለታለመላቸው አላማ ለማዋል ” አልተቻለም ብለዋል። “በእነዚህ ማእከላት ውስጥም በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የገቡና ሊገቡ የተሳቡ የማምረቻ ማሽነሪዎች ምርትን ...
Read More »በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት በድጋሜ ተቀጠሩ
ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቤት ቢቀርቡም ሌላ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ...
Read More »