የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ከሕንድ መንግስት በተገኘ 640 ሚሊየን ዶላር በተገኘ ብድር እ.ኤ.አ በ2008 ሥራ የጀመረው ይህው ፋብሪካ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጥራት ያለው ማሽነሪግ ባለመከናወኑና ሥራው በተገቢው ቁጥጥርና ክትትል ባለመታገዙ ተጠናቆ ወደ ስራ መግባት የነበረበት እ.ኤ.አ በ2010 መጨረሻ ቢሆንም ፋብሪካው እስካሁን ወደስራ መግባት እንዳል ቻለ ታውቋል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች በዚህ ዓመትም ፋብሪካው ስራ ይጀምራልበሚልበ ተደጋጋሚ መግለጫ ከመስጠታቸው ባሻገር ፣ ጋዜጠኞችን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የመከላከያ ቀንን ለማክበር ፈቃደኛ ያልሆኑ የባጃጅ ሹፌር አሽከርካሪዎች እየተቀጡ ነው
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በባህርዳር የሚከበረውን የመከላከያ ሰራዊት ቀን የሰልፍ ትርኢት እንዲያጅቡ ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ የባህርዳር ባጃጅ አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃዳቸውን እየተነጠቁ ቅጣት እንደተጣለባቸው፣ አንዳንዶችም በፖሊስ መዋከባቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ሹፌሮች ለኢሳት ተናግረዋል። ሹፌሮቹ መብታችን ተገፏል በማለት ባቀረቡት አቤቱታ፣ ያለፍላጎታቸው ስራ አቁመው ሰልፍ እንዲያጅቡ መጠየቃቸው አግባብ ባለመሆኑ አንዳንዶች መኪኖቻቸውን አቁመው ስራ ፈተው ለመዋል ተገደዋል። መንግስት የመከላከያ ቀን የሚል በአል ማክበር መጀመሩ ...
Read More »በኦሮምያ ክልል የፌደራል ፖሊሶች ሁለት የቤተሰብ አባላትን በጥይት መትተው አመለጡ
የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በምእራብ ሸዋ ዞን በባኮ ወረዳ በቴቢ ከተማ ከሩሰንጎት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት አቶ ተሙሻ በርጫ እና የ13 አመት ታዳጊ ልጃቸው ፋንቱ ተሙሻ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች በጥይት ተመትተው አምቦ ሆስፒታል መግባታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ታዳጊዋ ወጣት አንገቷ አካባቢ በጥይት ስትመታ፣ አባቷ ደግሞ እግራቸውን በሁለት ጥይቶች ተመተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በታዳጊዋ ላይ የደረሰው ...
Read More »የኢትዮጰያ መንግስትና የኦጋዴ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር በኬንያ ናይሮቢ ድርድር ጀመሩ።
የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የኦጋዴንየዜናአገልግሎትን <<በመጥቀስዋጋኩሱብ>> የተሰኘውየግንባሩልሳንእንዳስታወቀው፤የመከላከያሚኒስትሩሲራጅፈርጌሳእና የደህንነትሹሙአቶጌታቸውአሰፋ – ከኦጋዴነጻነትግንባር የውጪግንኙነትሀላፊከአቶአብዲራሁምማህዲእና ከግንባሩዋናጸሀፊ ከአቶአብዲያሲንጋርበናይሮቢተገናኝተው ድርድሩንጀምረዋል። ሁለቱምወገኖችበአብዛኞቹየድርድሩመርሆዎችላይ መስማማታቸውምተገልጿል። በሁለቱወገኖችመካከልለአስርትኣመታትየዘለቀውግጭት በመነጋገርእንዲፈታዓለማቀፉማህበረሰብግፊትእያደረገእንደሚገኝየግንባሩዜናአገልግሎትአውስቷል። ሁለቱወገኖችባለፈውጥቅምትወርበኬንያጀምረውትየነበረውድርድር፤የኢትዮጵያመንግስት ያቀረበውንቅድመ-ሁኔታኦብነግለመቀበልፈቃደኛባለመሆኑምክንያትመቋረጡይታወሳል። እንዲሁም የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በተመሳሳይ መንገድ ለድርድር ናይሮቢ የሄዱትን 2 የኦብነግ ከፍተኛ አመራሮች አፍነው መውሰዳቸው አይዘነጋም። እንደኦጋዴንዜናአገልግሎትዘገባየኦጋዴንግጭትበአፍሪካየግጭትታሪኮችረዥሙሲሆን፤እስካሁን 500 000 ሰዎችሞተዋልከሚሊዮንየሚልቁክልሉንለቀውተሰደዋል። አንዳንድ ወገኖች ክልሉን በማስተዳደር ላይ ያሉት አቶ አብዲ ሞሃመድ ከህወሃት የጦር አዛዦች ጋር በመሆን የሚፈጽሙት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፣ የኢህአዴግን ባለስልጣናት ...
Read More »የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) ካድሬዎች ፣የደህንነት ሰዎች እና የመከላከያ አባላት፤አዲስአበባ የተለያዩ አካባቢዎች እየዞሩ፦‹‹ለህወሓት በዓል ማክበሪያ ገንዘብአዋጡ›› በማለት እየቀሰቀሱመሆናቸውንነዋሪዎችተናገሩ።
የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የህወሀት 40ኛዓመትየፊታችንየካቲት 11 የሚከበርሲሆን፤ለበዓሉማክበሪያበግዳጅናበጫናከባለሀብቶችብቻ 45 ሚሊዮንብርእንደተገኘመዘገባችንይታወሳል። ህወሀትከመንግስትካዝናየሚጨምረውንሳያካትትለአንድጊዜበዓልማክበሪያብቻይህንያህልብርየሰበሰበቢሆንም፤ከነዋሪዎችተጨማሪገንዘብለማሰባሰብበካድሬዎችአማካይነትቅስቀሳመጀመሩንየአዲስአበባውዘጋቢያችንያጠናቀረውሪፖርትያመለክታል። ከዚህባሻገርበአዲስአበባ፣መቀሌእናበየክልሎቹየሚደረገውየበዓልዝግጅትላይካድሬዎችደምቀውእንዲገኙ የልብስመግዣገንዘብእየተሰጣቸው እንደሆነተመልክቷል። በዚህምመሰረትለሴቶችየሀበሻቀሚስ መግዣ 4 ሺህብር፣ ለወንዶችደግሞ ለቁምጣናለሌሎችባህላዊአልባሳት ተብሎ 2 ሺህብርእየተሰጠመሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
Read More »በባህር ዳር ከተማ ከወራት በፊት ሲታይ የነበረው የነዳጅ እጥረት አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡
የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የነዳጅ ዋጋ በዓለም ገበያ ቅናሽ ማሳየቱን ተከትሎ የገዢው መንግስት ባደረገው አነስተኛ የዋጋ ማሻሻያያ ኮረፉትን የነዳጅ ማደያ ባለ ንብረቶች መቆጣጠር ባለመቻሉ ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎችና ባጃጆች መቸገራቸውን ለዘጋቢያችንገልጸዋል፡፡ ድምጻችንከተሰማለሌላችግርእንዳረጋለንየሚሉትቅሬታአቅራቢዎችሰሞኑንበነዳጅማደያዎችቤንዚንባለመኖሩበጥቁርገበያእስከአርባብርድረስበመግዛትእየሰሩመሆናቸውንገልጸው፤ይህ ሰርተንእንዳንበላናቤተሰብለማስተዳደርእንዳንችልሆንተብሎከአመራሮችጋርበመመሳጠርየሚሰራብንደባነውበማለትያማርራሉ፡፡ በከተማዋወስጥቤንዚንምሆነናፍጣበብዛትቢኖርምከተተመነውበላይበእጥፍዋጋስንገዛ ጥቆማብናደርግም፡መንግስትተገቢውንፍተሻናምርመራበማድረግለህግየማይገዙትንመቅጣትሲገባውህብረተሰቡንለብዝበዛማጋለጡአግባብአይደለምበማለትእስተያየታቸውንሰጥተዋል፡፡ ከአሁንበፊትባለሃብቶችነዳጅደብቀውቢገኙምየከተማውአስተዳደርለተወሰኑቀናትማደያውንበመዝጋትከቆየበኋላምንምዓይነትርምጃሳይወስድመልሶመክፈቱ ሌሎችባለማደያዎችምነዳጅበመደበቅበጥቁርገበያለመሸጥእንዳደፋፈራቸውቅሬታአቅራቢዎችለዘጋቢያችንተናግረዋል፡፡ ነዳጅበሚገኝበትማደያከግማሽቀንበላይተሰልፈውስራእንደሚፈቱየሚናገሩትአሽከርካሪዎችግማሽቀንድረስምተሰልፈንምአለቀተብሎየምንሰናበትነትጊዜበርካታነውበማለትሰርቶየመኖርህልውናቸውአደጋላይመሆኑንተናግረዋል፡፡
Read More »በሲ ኤም ሲ ደማቅ የሰደቃና የዱአ ፕሮግራም ተካሄደ
የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ችሎት መጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ የካቲት 4 2007 ዓመተምህረት ደማቅየሰደቃስነ-ስርዓትተካሄደ እንደ ሪፖርተሮቻችን ዘገባ፤ የሙስሊምመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ኮሚቴዎቻችን ችሎት መጠናቀቁን ተከትሎ የሰደቃውና የዱአው ፕሮግራም የተካሄደው፤ችሎቱሲካሄድበትበቆየውበሲኤምሲአካባቢነው። በደማቁየሰደቃናየዱአ ፕሮግራምላይ የኮሚቴዎቹንቤተሰቦችእናሚስቶችጨምሮየችሎቱታዳሚያንበሙሉተገኝተዋል። የሰደቃፕሮግራሙየተዘጋጀው፤የኮሚቴዎቹየፍርድቤትሂደትሊጠናቀቅቀናትሲቀሩትበችሎቱሲገኙከነበሩሙስሊሞችጋርበጋራበመሆንዱአለማድረግበማሰብእንደሆነተገለጿል፡፡ የሙስሊምመፍትሄአፈላላጊኮሚቴዎች፤የመብታችንይከበር! ጥያቄበማንሳታቸውየሽብርተኝነትክስተመስርቶባቸውላለፉትሶስትዓመታትበእስርላይእንደሚገኙይታወቃል።
Read More »12 ኢትዮጰያውያን ሴቶች ኩዌት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ
የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኢትዮጰያውያን የሚመራ ፣ የቤት ሰራተኞችን በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውር ቡድንኩዌት ውስጥ በቁጥጥርስርመዋሉንአረብታይምስዘገበ። እንደ ጋዜጣውዘገባ፤አንዲት ሾፌርንጨምሮ 12 ኢትዮጰያውያን ሴቶችን ያቀፈውና ሴትሰራተኞችን በድለላና በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውር ነበር የተባለው ይህ ቡድን በኩዌት ማህበራዊ ጉዳይ ምርመራተቋም- ጂሌብአልሹዮክ” ተብሎበሚጠራቦታነውበቁጥጥርስርየዋለው። የኩዌትየሀገርውስጥጉዳይሚኒስቴርጉዳዩንአስመልክቶበሰጠውመግለጫ ፤የማህበራዊጉዳይምርመራተቋሙ -ከታማኝምንጮቹ ኢትዮጵያውያኑ ለምርመራበተቋቋመውየሰራተኛአገናኝቢሮላይጫናበመፍጠርከበርካታየኩዌትነዋሪዎችገንዘብእየበዘበዙእንደሆነየደረሰውንመረጃተከትሎባደረገውክትትል 12ቱምየቡድኑአባላትመያዛቸውንአስታውቋል በአሁኑወቅትበእስርየሚገኙትእነኚህኢትዮጰያውያን፤.በሀገሪቱህግመሰረትአጥፍተዋልለተባለው ጥፋት ተገቢውን ቅጣትወደሚቀበሉበትአካልእንደሚተላለፉተገልጿል። በጉዳዩዙሪያየኢትዮጰያመንግስትምሆነበኩዌትየኢትዮጰያኤምባሲየሰጡትመግለጫምሆነአስተያየትየለም።
Read More »በፕሮፓጋንዳው ስራ በኩል በሚታየው ድከመት ዙሪያ የመንግስት ሹመኞች እርስ በርሳቸው ተካሰሱ
የካቲት ፫(ሦስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በቅርቡ በኪሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን በተመራው የቀድመው ኢቲቪ የአሁኑ ኢቢሲ አመራሮች፣ የፕሬስ መምሪያ ሃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮ አመራሮች፣ የህዝብ ግንኙነቶች፣ ኮሚኒኬተሮችና ሌሎች ባለስልጣናት በተገኙበት በተካሄደው ውይይት ላይ የመንግስት የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች የአትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችን ሲከሱ፣ የኢቢሲ አመራሮች ደግሞ ረጃጅም እጆች ያሉዋቸው ባለስልጣናት ቴሌቪዥኑን ስለተቆጣጠሩት ፍትሃዊ የሆነ ሽፋን ለመስጠት አልተቻለም ሲሉ ወቅሰዋል። “ረጅም እጅ ያለው ባለስልጣን ካለ፣ ሄክታር መሬትም ...
Read More »ተረስተናል ያሉ የከምባታ ጠንባሮ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
የካቲት ፫(ሦስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የከንባታ ጠንባሮ ህዝብ ባለፉት 23 አመታት የመሰረተ ልማት አገልግሎት አላገኘም በሚል ከሺ ያላነሱ ነዋሪዎች በተገኙበት በዱራሜ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል። የአካባቢው ተወላጆች በራሳቸው ተነሳሽነት ትምህርት ቤቶችን እየሰሩ ፣ የመብራት፣ የመንገዶችና የቴሌኮሚኒኬሽን ዝርጋታ ማካሄዳቸውን ገልጸው፣ መንግስት ምንም ድጋፍ ባለማድረጉ፣ ችግሩ የባሰባቸው ነዋሪዎች እየተሰደዱ መሆኑን ሰልፈኞቹ ገልጸዋል። ሰልፈኞቹ የደቡብ ክልል ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርገዋል። በሰልፉ ላይ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ሳይቀሩ ...
Read More »