የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው በክልሉ በሚካሄደው ትጥቅ የማስፈታት ሂደት በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ጎጃም ዞኖች ብቻ 2 ሚሊዮን 13 ሺ 497 ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች ለክልሉ ሚሊሺያ ጽ/ቤት ገቢ ተደርጓል። የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊው አቶ ደጀኔ ሽባባው በጽ/ቤቱ የ2ዐዐ7 በጀት ዓመት ግማሺ አመት ሪፖርት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሰማዕእታት ቀን 78ኛ አመት ታስቦ ዋለ።
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወራሪው የጣሊያን ሰራዊት በጦር አዛዡ ፊልድ ማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ አማካኝነት 30 ሺህ ኢትዮጰያውያንን በግፍ የጨፈጨፈበት 78ኛ ዓመት ዛሬ በመላው ኢትዮጰያውያን ዘንድ በመተሳብ ላይ ነው። በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ ዜጎች ፣ የጣሊያን ወራሪ ሃይል በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አስከፊ ጭፍጨፋ የሚያስታውሱ ጽሁፎችን በመልቀቅ እለቱን ዘክረውታል።
Read More »አቶ አባይ ወልዱ የህወሃት ክንፍ እንዲፈጠር ከሳሞራ ጋር አሲረዋል በሚል ተገመገሙ
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤተመንግስት ትንሹ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደውን የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግምገማ የሚቃኘው መረጃ እንደሚያሳየው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ የህወሃት ክንፍ እንዲፈጠር ከመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ጋር ማሴራቸው በሌሎች የኢህአዴግ አባላት ሂስ ቀርቦባቸዋል። አቶ አባይ ወልዱ የቀረበባቸውን ሂስ በደፈናው ተቀብያለሁ፣ አርማለሁ በማለት መመለሳቸውን ሰነዱ ያስረዳል። አቶ አባይ ግለሂሳቸውን እንዲያወርዱ ሲጠየቁ የስራ ሰአት ...
Read More »ከ200 በላይ ዕጩዎች የተሰረዙበት ሰማያዊ ፓርቲ የነጻነት ትግሉን እንደሚገፋት አስታወቀ
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ የተሰረዙበት መሆኑን የገለጸው ፓርቲው፣ የካቲት 22 ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች የሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ የነጻነት ትግል አካል ነው ብሎአል። የድርጅቱ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጹት ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ ...
Read More »በቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ላይ ዛቻና ማዋከቡ ተባብሶ ቀጥሏል።
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በህገወጥ መንገድ በታገደው የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ አመራሮች ላይ ደህንነቶች ዛቻ፣ማስፈራሪያና ማዋከብ እየፈጸሙ ነው። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት አቶ አስራት አብርሀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ባለፈው እሁድ ማታ መናኛ አለባበስ የለበሱ ሁለት ወጣቶች የተከራዩበት ቤት ድረስ በመሄድ “እንፈልገሃለን” እንዳሏቸው በመጥቀስ፤ “በዚህ ሰዓት የምትፈልጉኝ እናንተ ደግሞ እነማናችሁ?” ብለው ሲጠይቋቸው “ከደህንነት መስሪያቤት ...
Read More »የቤተክርስቲያን ነዋየ -ቅድሳት ለዓባይ ግድብ ተብሎ መሰጠቱ ተዘገበ
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ በምእመናን ዘንድ ተቃውሞ አስነስቷል። ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውሰጥ መጥፋታቸውን የደብሩ ካህናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ...
Read More »ሚኒስትሮችንና አፈ-ጉባኤዎችን ጨምሮ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቤተ መንግስት የተገመገሙበት ሰነድ ኢሳት እጅ ገብቷል።
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ በማድረግ ነው። በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ ከ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተገመገሙት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣”የሀሰት የስራ አፈጻጽመ ታቀርቢያለሽ” የተባሉት የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር ዘነቡ ታደሰ፣”ሳሞራን ትፈራዋለህ”ተብለው የተገመገሙት የመከላከያ ...
Read More »አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ- ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር እንደማይግባቡ ተናገሩ
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባ ዱላ-ገመዳ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት- ከአቶ ሙክታር ከድር ጋር እንደማይግባቡ የተናገሩት፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር አባላት በቃኘው ጥልቅ ግምገማ ላይ ነው አፈ-ጉባኤው በግምገማው”የኦሮምያ አባላትን በተለየ ትህትና ታሰተናግዳለህ፣የአፈ ጉባኤነቱን ቦታ በደስታ አልተቀበልከውም፣ በአዲስ አበባ አዲስ ማሰተር ፕላን ጋር ተያይዞ ተል እኮ የማስፈጸም ችግር አለብህ፣ ከማስተር ፕላኑ ጋር ተያይዞ ለተነሳው አመጽ መባባስ ...
Read More »በሙስሊሞች ላይ በከፍተኛ የደህንነት ሃይሎች የሚመራ የእስር ዘመቻ መከፈቱ ተነገረ
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍትሕ ራዲዮ እንደዘገበው፤በአዲስ አበባ ብቻ ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን ለማሰር ታቅዷል፡፡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ አካላት በምክንያት ለማሰር በከፍተኛ የኢትዬጲያ መንግስት የደህንነት ሃይሎች የሚመራ ዘመቻ መከፈቱን ፍትህ ራዲዬ ዘግቧል። ራዲዮው ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ዘመቻው ያነጣጠረው፤ ከመጪው ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በህዝበ-ሙስሊሙ መካከል ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥሩ ይሆናል የሚል ስጋት ባሳደሩ ሙስሊሞች ላይ ነው። መንግስት ምርጫው ...
Read More »ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፤ ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች <<ጥፋተኞች አይደለንም>> ብለዋል። የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ያደመጠው ፍርድ ቤትም፤ ለፊታችን መጋቢት 21 ቀጠሮ በመስጠት የእለቱን ችሎት አጠናቋል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ ወር 2006 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ ...
Read More »