መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢ ተቆርቋሪና የማህበረሰብ ቱሪዝም ኤክስፐርት የሆነው ወጣት ቢኒያም አድማሱ ሰሞኑን በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ እንደተቀሰቀሰ መስማቱን ተከትሎ ወደዚያው በማቅናት እሳቱን ለማጥፋት ሲረባረብ ነው በቃጠሎ ህይወቱ ያለፈው። ወጣት ቢኒያም ወደባሌ ብሄራዊ ፓርክ ያቀናው እንደሱ እሳቱን ለማጥፋት ከዘመቱ ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመሰባሰብ ነበር። በስፍራው ደርሰው በጋራ ርብርብ በሚያደርጉበት ወቅት እሳቱ ቢኒያምን ጨምሮ ሌሎቹን ወጣቶች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በአየር ሃይል አባላት ላይ እየዛቱ መሆናቸው ተሰማ
መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብራሪዎች ባለፉት 6 ወራት ከድሬዳዋ አየር ሃይል ግቢ ጠፍተው ተቃዋሚዎችን መቀላቀላቸውንና መሰደዳቸውን ተከትሎ ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑስ በቀሪዎቹ ላይ የዛቻና የማስፈራሪያ ንግግሮችን በማድረግ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል ። የአየር ሃይል ምንጮች እንደተናገሩት፦ጀነራሉ <<ከጠፉት የአየር ሃይል አባላት ጋር ግንኙነት ነበራቸው>>ያሏቸውንና <<ሊጠፉ ሲሉ ተያዙ የተባሉ ሌሎች የአየር ሃይል አባላትን>> ለቀሪዎቹ አባላት ሲያሳዩ ሰንብተዋል። ኢታማዦር ሹሙ ሰሞኑንም ...
Read More »ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ድብደባ ተፈጸመባቸው
መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ ማንነቱን በማያውቁት ሰው ድብደባ ተፈጸመባቸው። ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ወደ ፍርድ ቤት እየሄዱ ሳሉ ሜክሲኮ አካባቢ ብሔራዊ አረቄ ፋብሪካ መታጠፊያ ላይ አንድ እብድ የሚመስል ሰው ተንደርድሮ ዐይናቸውን በቡጢ ክፉኛ መቷቸዋል። ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጠበቃ ሆነው ለረዥም ጊዜ በመከራከራቸው በስርዓቱ ሰዎች ዛቻና ማስፈራሪያ ...
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር -የአውሮፓ ህብረት ተወካዮችን ወቀሱ
መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ሲሉ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለአውሮፓ ህብረት መልእከት አስተላለፉ። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይህን ያሉት የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ ላይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ በተጋባዥ እንግድነት የተገኙት ...
Read More »<<ችሎት ደፍራችሁዋል ተብለው ፍርድ የተላለፈባቸው እነ አብርሀ ደስታ፦<<የደፈርነው አሻንጉሊት እና ወትሮም የተደፈረ ችሎት ነው>>ሲሉ ተቃውሟቸውን ገለጹ።
መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ ፓርቲ አመራሮች ‹ችሎት በመድፈር ወንጀል› ጥፋተኛ በመባላቸው የሰባት ወር እስራት ተፈረደባቸው። የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት በመድፈር በሰባት ወር እስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አብርሀ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና ...
Read More »በጋምቤላ የድንበር ከተሞች ዜጎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እየተገደሉ ነው
የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆኑ የጋምቤላ አካባቢዎች ኢትዮጵያውያን በየጊዜው እንደሚገደሉና የጸጥታው ሁኔታ እየተበላሸ መሆኑን በተለያዩ የመንግስትና የግል ስራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎች ገልጸዋል። መታሃር፣ ላሬ፣ ኢታንግ እንዲሁም ፑጊዶ በሚባሉ አካባቢዎች ማንነታቸው በውል የማይታወቁ ታጣቂዎች አብዛኛውን ጊዜ በግል ኩባንያዎች ተቀጥረው በሚሰሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው። እነዚህ ታጣቂ ሃይሎች የሚወስዱትን እርምጃ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል ...
Read More »በሃረር የቀን ሰራተኞች ታፈሱ፣ እድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱትም ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች ተወሰዱ
የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃረር ከተማ ካለፈው ሁለት ሳምንት ጀምሮ እንዳዲስ በተጀመረው አፈሳ በርካታ በቀን ስራ የሚተዳዳሩ ነዋሪዎች ታፍሰው ወደ አልታወቀ ስፍራ የተወሰዱ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ግን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ተወስደዋል ብሎዋል። እሁድ እለት ደግሞ በርካታ አዲስ ምልምል ታዳጊዎች ደግሞ ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ብር ሸለቆ ተወስደዋል። እድሜያቸው ከ12 እስከ 13 አመት የሚደርሱ ወጣቶችም ወደ ማሰልጠኛ የተወሰዱ ሲሆን፣ ...
Read More »ጀማሪ የሥራ ተቋራጮች ፈቃድ ለማግኘት የተጭበረበረ ማስረጃ እንደሚጠቀሙና ይህም ለሕዝብ ሀብት ብክነት ዋና መንስኤ እየሆነ እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡
የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ደረጃ አንድ፣ ደረጃ ሁለት እየተባለ እስከ አስር ደረጃ ድረስ የስራ ተቋራጭነት ፈቃድ የሚሰጥ ሲሆን ይህንን ፈቃድ ለማግኘት እንደዶዘር፣ ግሬደር፣ እስካቭተርና ፒክ አፕ ያሉ መኪኖችን መያዝ በቅድመ ሁኔታነት የሚጠየቁ ቢሆንም፣ ሥራ ተቋራጮች እነዚህ ተሸከርካሪዎች እንዳሉዋቸው በማስመሰል ከትራንስፖርት ባለስልጣን አንዳንድ ሃላፊዎች ጋር እየተሻረኩና የጥቅም ትስስር እየፈጠሩ ሐሰተኛ ሊብሬ በማቅረብ ፈቃዱን የሚወስዱ ...
Read More »የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ስደተኞች አርብ እለት ወደ ሰሜን ሱዳን ሲጓዙ በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሱዳን ትሪቢዩን የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ ከህገ ወጥ አሻጋሪዎቹ መክከል ሁለቱ ህይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል። እንደ ሱዳን ፖሊስ ገለጻ አደጋው የደረሰው ከካርቱም 79 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውና አል-ባካ ተብላ በምትጠራው አካባቢ ባለው “የሺሪያን አል-ሺማጅ” የቀለበት መንገድ ላይ ነው። እስካሁን ከተጎጆዎቹ መካከል 15ቱ መሞታቸው ታውቋል። አሽከርካሪዎች ብዙውን ጊዜ ...
Read More »በደልጊ ከተማ ከቤተክርስቲያን ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ
የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማ ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ የተከለለውን ቦታ 40 የሚሆኑ የምክር ቤት አባላትና ደጋፊዎቻቸው መከፋፈላቸው የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ፣ የካቲት 27 ጧት ላይ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ የከተማው ፖሊስ ጣቢያ ፣ መዘጋጃ ቤት፣ መስተዳድሩና የብአዴን ጽህፈት ቤት መስኮቶችና በሮች ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የመዘጋጃ ቤት ዘበኛም ተደብድበዋል። በብዙ ሺ የሚቆጠር ...
Read More »