.የኢሳት አማርኛ ዜና

ባለሃብቶች መስራት አልቻንልም አሉ

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ” የኢንዱስትሪውን  ልማት በተሳለጠ መንገድ ይዘን በመጓዝ የአምስት አመቱን ዕቅድ ለማጠናቀቅ  በስኬት ጎዳና ላይ ነኝ ” በሚል  የገዢው መንግስት ቢናገርም፤ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች በርካታ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡ ሰሞኑን በተካሄደው የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት  ከከፍተኛ ባለሃብቶች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ፣ ባለሃብቶች  እንደገለጹት በባለስልጣናት ላይ የሚታየው የፍርሃት መንፈስ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን በአንድነት እንዲነሱ ጥሪ ቀረበ

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ ሜይ 2፣ 2015 ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶና ታዋቂው ጸሃፊ እና ፖለቲካ ተንታኝ አቶ የሱፍ ያሲን፣ አገራችን ከገባችበት ችግር መላቀቅ የምትችለው  በአንድነት በመነሳት መሆኑን ተናግረዋል። አቶ የሱፍ ገዢው ፓርቲ ባመጣው የፌደራል ስርአት ሳንጣላ ተራርቀናል ያሉ ሲሆን፣ ልዩነታችን ለጥንካሬያችን መሰረት ...

Read More »

የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች በድርጅታቸው ግራ ተጋብተዋል

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን ለመዘከር የወጣው ህዝብ ተቃውሞውን ወደ ኢህአዴግ መንግስት ካዞረ በሁዋላ፣ ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ያስነሳው በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገለው ሰማያዊ ፓርቲ ነው በማለት የከፈተው ሰፊና አሰልቺ ፕሮፖጋንዳ የህዝቡን አመለካከት ሊቀይር አለመቻሉ ከፍተኛ ካድሬዎችን ስጋት ላይ ጥሎአቸዋል፡፡ በመስቀል አደባባይ የታየውን ህዝባዊ ቁጣ  ሰማያዊ ፓርቲ የቀሰቀሰው የመንደር ሁከት ለማስመሰል ...

Read More »

ፌደራል ፖሊስ በማእከላዊ እስር ቤት ታስረው የሚገኙት እስረኞች እርስ በርስ እንዲወነጃጀሉ እያደረገ ነው

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ታህሳስ ወር አርበኞች ግንቦት7ትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ መንገድ ላይ ተይዘዋል ባላቸው እሰረኞች ላይ ለደረጃ ምስክርነት አብረው ከታሰሩት መካከል እያሰለጠ ነው። አንዳንዶች ፖሊስ ራሱ ያዘጋጀውን ቃል በፍርድ ቤት ተገኝተው የሚሉ ከሆነ ከእስር እንደሚፈቱ ፣  ለመመስከር ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ እድሜ ልካቸውን በእስር ላይ እንደሚቆዩ እንደተነገራቸው ምንጮች ገልጸዋል። ሰለሞን አሞኘ የተባለው ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ ህዝቡ በቡድን ድምጽ እንዲሰጥ እያዘጋጀ ነው

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግንቦት አጋማሽ ሊደረግ በታሰበው  ምርጫ ላይ  ገዢው ፓርቲ በቡድን ድምጽ የሚሰጡ ዜጎችን በማደራጀት ላይ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች አመልክተዋል። ዜጎች ድምጽ እንዲሰጡ የሚደረገው ገዢው ፓርቲ አንድ ለአምስት እያለ በሚጠራው የአፈና ስርአት ውስጥ ሆነው ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በድምጽ መስጫው ቀን በአንድ ለአምስት የተደራጁትን ሰዎች በአንድ ላይ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየመሩ በመውሰድ ...

Read More »

ጠ/ሚኒስትር ናታኒያሁ ደማስ ፈቃደን አነጋገሩ

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ዘረኝነትን በመቃወም ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እሁድ ተጠናክሮ ከቀጠለ በሁዋላ፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ ፣ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደን አነጋግረውታል። ወታደር ደማስ በእስራኤል ፖሊሶች መደብደቡ በአገሪቱ የሚኖሩትን በተእስረኤላውያንን በእጅጉ አበሳጭቶ ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቶአቸዋል። ቤተእስረኤላውያኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እጥብቀው የተቃወሙ ሲሆን፣ ቁጣቸውንም የተለያዩ ጠርሙሶችና ...

Read More »

በጤናተቋማትአገልግሎትአለመሟላትየእናቶችሞትበእጥፍጨምሯል፡፡

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀገሪቱካሉት 879 በላይ  የጤናተቋማትውስጥመሰረተልማቶችየተሟሉላቸው 105 ብቻሲሆኑ፣ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 68 ሴቶች በየሰዓቱ ደግሞ 3 እናቶች ህይወታቸው እንደሚያልፍ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የአብዛኛው እናቶች ሞት የሚከሰተው በደም መፍሰስ፣ በተራዘመ ምጥና በከፍተኛ የደም ግፊት ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ መቶ ሺ እናቶች መካከል 420ዎቹ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጣሉ። በጤና ጥበቃ ሚኒስትር የእናቶችና ...

Read More »

በሱዳን በኩል ወደ ውጭ የሚወጡ ዜጎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በዚህ ሳምንት ብቻ 9 ሺ 405 ወጣቶች ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን ሲጓዙ በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ተይዘዋል። ፋሲል የኔአለም ዝርዝሩን ያቀርበዋልበሰሜን ጎንደር ዞን ቆላማ ወረዳዎች በተደረጉ 2 የዳሰሳ ጥናቶች በቀን  ከ150-250  በዓመት ደግሞ ከ 54,000 እስከ 90,00 ኢትዮጵያውያን   ወደ  ሱዳን ይሻገራሉ፡፡ ጥናቱ በመላው አማራ ወይም በመላው ...

Read More »

ገዢው  ፓርቲ  የቅድመ ምርጫ ግምገማውን ይፋ አደረገ፡፡

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪፖርቱ ኢህአዴግ ምርጫውን ለማሸነፍ መልካም እድል መኖሩን ጠቅሷል። ኢህአዴግ መንግስት መሆኑና የመንግስትን ንበረቶችና ጽህፈት ቤቶች መጠቀሙ እንዲሁም   በቅስቀሳ ወቅት አንድ  ለአምስት  በሚል  አሠራር  በተጠቀመበት  የቅስቀሳና  የማሳመን አሠራር    በርካታ  ድምፆችን ለመውሰድ የሚያስችል እድል መፍጠሩን በ2002 ቱ ምርጫ ወቅት መታየቱን አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሚኒስትሮች ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል። በቅድመ ውጤት ትንበያው   ኢህአዴግ በከፍተኛ ድምጽ ...

Read More »

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ፕሬሱን ማዳከሙን ቀጥሏል

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ነጻ ፕሬሱን በማዋከብ፣ በማሳደድ፣ በማሰር ከሚያደርገው ቀጥተኛ ጥቃት በተጨማሪ ስልታዊ ጥቃትን በተጠናከረ መልኩ ስራ ላይ እያዋለ ነው። በነገው ዕለት የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ቀን በኢትዮጵያ ታስቦ የሚውለው የፕሬሱ ስልታዊ አፈና በተጠናከረበት ወቅት መሆኑም ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ምንም ዓይነት ትችትና የተለየ አስተያየት ለመስማት  ዝግጁ ያልሆነው የኢህአዴግ ...

Read More »