.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡት የፖለቲካ ክሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቂኝ እየሆነ ነው።

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም በ1997 ምርጫ ወቅት በቅንጅት መሪዎች፣ በጋዜጠኞችና በሲቪክ ተቋማት መሪዎች ላይ የቀረበው ክስ ፣ 24 ሰአታት አስቂኝ ፊልም የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር። በፍርድ ቤቱ የነበረውን ሁኔታ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የቃሊቲው መንግስት በሚል ርእስ ዘርዝሮ ማቅረቡ ይታወቃል። በቅርቡ አይ ኤስ ኤስ የተባለው አሸባሪ ድርጅት በ30 ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ...

Read More »

ሚኒስትር ዲኤታዎች ድምጽ አልባና ደካሞች ናቸው ተባሉ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“በኢትዮጵያ ያሉ ሚንስትር ድኤታዎች ድምፅ አልባ እና ተሳትፎ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው” ሲል የኢህአዴግ ጽ/ቤት የአመራር ግንባታ የመለስ ዜናዊ የአመራር ግንባታ ክፍል ያወጣው ደብዳቤ አመለከተ። ደብዳቤው ዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ያላቸውን ሚኒስትር ድኤታዎች ዘርዝሮ አስቀምጧል። በአቶ አዲሱ ለገሰ የሚመራው እና ከፍተኛ የኢህአዴግ አባላትን ብቻ የሚያሰለጥነው የኢህአዴግ አመራር ማሰልጠኛ ክፍል የአመራሮችን ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት በረመዳን ጾም ተቃውሞ ሊያይልብኛል ይችላል በሚል ፍርሃት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት የሮመዳንን ጾም ተከትሎ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት፣ 53 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ የመስጊድ ኢማሞችን በአክራሪነት ዙሪያ የማሰልጠን እና የማግባባት ስራውን እያከናወነ ነው፡፡ አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ሲል የሚታየው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሁንም መንግስትን እንቅልፍ እንደነሳው ነው፡፡ በሁሉም ክልልች ለሚገኙ የእስልምና የሃይማኖት አባቶች ህገመንግስቱ እና ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግዳጅ ለመለስ ፋውንዴሽን ማሰሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ታዘዙ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብር ወጪ ይሰራል የተባለውን የመለስ ፋውንዴሽን ለማስገንባት ህዝቡ በፈቃደኝነት ገንዘብ ያዋጣል ተብሎ ሲጠበቅ፣ የህዝቡ መልስ አስደንጋጭ መሆኑን የተረዳው በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራው ፋውንዴሽን፣ የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም የመንግስት ደሞዝ ተከፋይ ሁሉ ገንዘብ እንዲያዋጣ ለማስገደድ ሞክረዋል። ግምገማ በመፍራትና በግዳጅ ገንዘብ እንዲያዋጡ ከተደረጉት መካከል የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይገኙበታል። የሰራዊቱ አባላት እንደሚናገሩት ...

Read More »

በወጣት ተመስገን ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል የኢህአዴግ የግፍ አስተዳደር መገለጫ ነው ሲል መድረክ አስታወቀ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ተመስገን ታፈሰ ተሰማ ዕድሜው 22 ዓመት ሲሆን በትምህርት ደረጃውም በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ ያገኘ ወጣት ነው፡፡ ትውልዱና ዕድገቱ በደቡብ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ወረዳ ውስጥ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢማዴ-ደህአፓ/መድረክ አባል ሆኖ ለመታገል የወሰነና በመድረክ አባልነታቸው ምክንያት በሀገራቸው ሠርተው የመኖር የዜግነት መብታቸውን እየተነፈጉ አስተዳደራዊ ግፍ እየተፈጸመባቸው ካሉ ወጣቶች አንዱና ተጫባጭ ምሳሌ ሆኖ ...

Read More »

የአየር ሀይል ሃላፊዎች በዘረኝነትና በሙስና ተዘፍቀዋል ተባለ

ኢሳት ዜና (ሰኔ 18፥ 2007) በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ባለው ዘረኝነትና አስተዳደራዊ በደል በመንገፍገፍ ከሰራቱ የሚለዩት የበረራ ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መገኘቱን እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን የአየር ሀይል ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።  በህገ-ወጥ የሰው ዘውውር የአየር ሀይል አባላት የታሰሩ መሆናቸውንም  ለመረዳት ተችሏል። በ2007 አ/ም ብቻ አስር የበረራ ባለሙያዎች ስርአቱን በመክዳትና ወደ እስር ቤት በመጋዝ ከአየር ሀይሉ የተለዩ ሲሆን ፤ በአየር ሀይሉ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ፖሊሶች ላይ የሚደረገው ግምገማ ከባድ መሆኑን ምንጮች ገለጹ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንም አይነት መረጃ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት ከሰኔ አንድ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት የተጀመረው ግምገማ ፈታኝ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማውን ተከትሎ አንዳንድ ፖሊሶች በደህንነቶች ተደብድበዋል። በጉለሌ ክፍለከተማ መምሪያ ስር የሚገኙ አንድ የሳጅን ማእረግ ያለውና አንድ ተራ ፖሊስ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ሞባይላቸው ላይ ተገኝቶባቸዋል ...

Read More »

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ የምክር እና ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት መብትም አላገኙም ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በተደጋጋሚ ለቀረበው ጥያቄ ኢትዮጵያ ...

Read More »

ሚድሮክ ወርቅ በሁለት አመታት ብቻ ከ429 ሚሊዮን ብር በላይ አልከፈለም ተባለ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን በመጥቀስ ሪፖርተር እንደዘገበው በማዕድን ሚኒስቴር ላይ በ2006 ዓ.ም. አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ላይ ባደረገው የክዋኔ ኦዲት አገሪቱ ከፍተኛ ገንዘብ ማጣቷን አረጋግጧል፡፡ የማዕድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 678/2002 የከበሩ ማዕድናት ላይ ስምንት በመቶ ፣ያልከበሩ ማዕድናት ላይ ደግሞ ስድስት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ መጣሉን ሪፖርቱ ያትታል፡፡ “ማዕድን ሚኒስቴር ከሚድሮክ ወርቅ ...

Read More »

በፍርድ ቤት ውሳኔ የተፈቱት ሰላማዊ ዜጎች በድጋሚ በመንግስት ታፈኑ

ኢሳት ዜና (ሰኔ 17, 2007) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው አራት የፓርቲ አባላት ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር ውለዋል። አራቱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ከተከሳሾች ፍርድ ቤት ካስተላለፋቸው ከሁለት ወር በላይ በእስር ቤት በመቆየታቸው ምክኒያት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። አራቱ ተከሳሾች ማክሰኞ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወጡ ቢደረግም በእስር ቤቱ በር ላይ ...

Read More »