.የኢሳት አማርኛ ዜና

የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ የሴቶች ሃላፊ ታሰረች

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት የኢህአዴግ አባል የሆነችው ወ/ሮ አስቴር ስዩም የወረዳው የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ፣ በቅርቡ ደግሞ በጎንደር ከተማ የጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅት ሃላፊ በመሆን ስትሰራ ቆይታለች። አስቴር የኢህአዴግ አባል ብትሆንም ከበላይ አካል የሚመጣውን ትእዛዝ ሁሉ እንደወረደ የማትቀበል እንደሆነችና በዚህም የተነሳ የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቷት እንደነበር፣ ከስራም ታግዳ መቆየቷን እርሷን በቅርብ የሚያዉቋት ይናገራሉ። የአንድ አመት ...

Read More »

ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ከሶስት ሽህ በላይ የኢህአዴግ ወታደሮች አልሸባብን ለመውጋት በሚል ወደ ጌዶ ዘመቱ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ ደይሊ ኔሽን የኢትዮጵያ ሰራዊት በታንክና በከባድ መሳሪያ ታግዞ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ሰራዊቱ የተንቀሳቀሰው ከኢትዮጵያ መሆኑንም የገለጸው ጋዜጣው፣አልሸባብ የሚቆጣጠረውን የባርደሬ ግዛት ለማስለቀቅ ሳያቅድ እንዳልቀረ ገልጿል። የአፍሪካ ህብረት ከኢትዮጵያ ያገኘውን ጨምሮ ከ20 ሺ በላይ ሰራዊት በሶማሊያ ቢያሰማራም አልሸባብን ለመደምሰስ አልቻለም። ታጣቂ ሃይሉ በቅርቡ በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ...

Read More »

በኢነሳና በሃኪንግ ቲም መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር መረጃዎች አጋለጡ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃኪንግ ቲም ለተባለ ኩባንያ 1 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የስለላ መሳሪያዎችን የገዛው በአብዛኛው በህወሃት አባላት የሚመራው የደህንነት መስሪያ ቤት፣ ከኩባንያው ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ እንደነበርና ውዝግቡ ሳይፈታ መረጃው ይፋ መሆኑን ለህዝብ ይፋ ከሆነው መረጃ ለመረዳት ተችሎአል። ቢኒያም ተወልደ በተባለ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ምሩቅ በኩል ግንኙነቱን የሚያደርገው የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ፣ የስለላ ሶፍት ...

Read More »

ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የጦር መሳሪያ ሊገዛ ነው

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ፣ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ የጦር አዛዦች በተገኙበት የወታደራዊ ጥቅል አቋማቸውን አቅርበዋል። በከፍተኛ ሚስጢር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ፣ ጄ/ል ሳሞራ ” ጦራችን ከጊዜው ጋር እየዘመነ አይደለም፣ የታንኮቻችን አቅም ያረጀ ነው፣ ተዋጊ አውሮፕላኖቻችን ከገበያ የወጡ ናቸው፣ መቀየሪያ እቃዎቻቸው ( ስፔር ፓርትስ) ከገበያ እየወጡና እየጠፉ ነው። ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ እየተካሄደ ነው

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞችም እየታፈሱ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዲስ አበባ የተቃዋሚ ሃይሎች ሰርገው ሳይገቡ ገብተዋል የሚል መረጃ ለደህንነት ክፍሉ እንደደረሰ የኢሳት ምንጮች ገልጸው፣ አሁኑ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር ሊያያዝ ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስፍረዋል። ለደህንነት ሲባል ኢሳት መረጃዎችን ...

Read More »

የሚኒስትር ሬድዋን አማካሪ መኮብለላቸው ተሰማ

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አዱኛ አሞኘ ከሀገር መኮብለላቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል። አቶ አንዱዓለም በ2007 ምርጫ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለቅስቀሳ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዲያዘጋጁ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ተመድበው እንደነበር ጋዜጣው ዘግቧል። አቶ አንዱዓለም ከሀገር ከመኮብለላቸው በፊት ቀደም ብለው ባለቤታቸውንና ልጃቸውን ወደ አሜሪካ ማሻገራቸውን ጋዜጣው ዘግቦ፣ ግለሰቡ ከሚኒስትሩ ...

Read More »

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ በተከሰሱት ላይ ብይን ሳይሰጥ ቀረ

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮች የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሽን ጨምሮ 10 ተከሳሾች ሐምሌ 1/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ብይኑን ሳይሰጥ ቀርቷል። ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል በጽሑፍ ተገልብጦ ከመዝገቡ ...

Read More »

የዋጋ ግሽበቱ በከፍተኛ ደረጃ ጨመረ

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ወርሃዊ የዋጋ መረጃው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም የሸቀጦች ዋጋ ካለፈው ጋር ሲነጻጸር መጨመሩን ይፋ አደረገ፡፡ በኤጀንሲው መረጃ መሰረት በግንቦት ወር 9 ነጥብ 4 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 10 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የዋጋ ግሽበትን ወደአንድ አሃዝ አውርጃለሁ በማለት ባለፉት ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ ለፓርላማ አባሎች እንደተናገሩት የኤርትራ መንግስት አካባቢውን የማተራማስ አጀንዳውን ካላቆመ ፣ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። አቶ ሃይለማርያም ሻእቢያ ኢትዮጵያና ጅቡቲን ለማተራመስ እየሰራ ነው ሲሉ ከሰዋል። የኢትዮጵያን ህዝብ አስታውቀን እርምጃ እንወስዳለን ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ እስካሁንም ለደረሰብን ጥቃት ተመጣጣኝ እርምጃ ስንወስድ ቆይተናል ሲሉ አክለዋል። የአቶ ሃይለማርያም መግለጫ በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት7 ...

Read More »

በሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ውስጥ 82 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ ዋና ከተማ ጋሮው በከባድ መኪና ድንበር አቋርጠው ሲጓዙ የነበሩትን ሰማንያ ሁለት ሕገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና የተሽከርካሪውን ሹፌር አብሮ መያዙን የፑትላንድ ፀጥታ ሹም ኃላፊ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከአስር ሽህ በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው አስተማማኝ ባልሆኑ ጀልባዎች በመሳፈር ባሕር አቋርጠው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ሰላምዋ እርቋት በጦርነት ምስቅልቅል ውስጥ ...

Read More »