.የኢሳት አማርኛ ዜና

5ኛው የመድረክ አባል ተገደለ

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መድረክ ባወጣው መግለጫ ከ2007 ምርጫ በሁዋላ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ የመድረክ አባላት ቁጥር 5 ደርሷል። የኢህአዴግ አገዛዝ በደቡብና ኦሮምያ የሚፈጽማቸው ድብደባዎችና እስራቶች መጨመራቸውንም መድረክ ገልጿል። በከፋ ዞን በግንቦ ወረዳ በአድዮ ካካ ምርጫ ክልል በጎጀብ ምርጫ ጣቢያ የመድረክ ምርጫ ታዛቢ/ወኪል ሆነው የሠሩት አቶ አሥራት ኃይሌ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በመተማና አብርሃጅራ የሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹን ወደ ጎንደር ሊያዛውር ነው

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት7 እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ በዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የሚመራው የምርት ገበያ ድርጅቱ በመተማና አብርሃ ጅራ የሚገኙ ቅርንጫፎቹን በመዝጋት ወደ ጎንደር ከተማ ለማዛወር እቅድ እንዳለው ምንጮች ገልጸዋል። ድርጅቱ በሰሜን አካባቢ በሁመራ፣ ጎንደርና መተማ ለሰሊጥ ጥራት ምደባና ማከማቻ ቅርንጮፎችን የከፈተ ሲሆን፣ የአብርሃ ጅራ ...

Read More »

ፍርድ ቤቱ የእነ ደብሬ አሸናፊን ጉዳይ አላይም አለ

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመናገሻ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ሀምሌ 3/2007 ዓ.ም በደህንነትና ፖሊሶች ተይዞ የታሰረውን የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ደብሬ አሸናፊንና በወቅቱ ከእሱ ጋር ተይዘው የታሰሩትን ወጣቶች ጉዳይ እንደማያይ አስታውቋል፡፡ ዛሬ ሀምሌ 6/2007 ዓ.ም ደብሬ አሸናፊ፣ ቴዎድሮስ ሻንካና ኤፍሬም የተባሉት ታሳሪዎች አምስት ኪሎ በሚገኘው የመናገሻ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ዳኛው ‹‹ይህን ጉዳይ ...

Read More »

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አፍራሽ ግብረ ኃይል በከተማዋ ዳርቻ የሚገኙ የይዞታ ቦታዎች አፈረሰ

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በርካታ ፖሊሶችና የታጠቁ ኃይሎች በመኪና በመሆን ከተማዋን ሲዞሩ መዋላቸውን ዘጋቢያችን ገልጻለች። የፖሊስ አባላት በተጠንቀቅ (stand by) ሆነው እዲጠብቱ የታዘዙ ሲሆን፣ ከአሁን በፊት ለምርጫ ቅስቀሳ በሚል ለባለ ይዞታ ቦታ ባለቤቶች የተሰጠው ጊዜያዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ከተቀማ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ አንዳንድ ቤቶችን በግዳጅ እያፈረሱ ነው። ህብረተሰቡ አመጽ ሊያስነሳ ይችላል በሚል የታጠቁ ...

Read More »

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚታየውን ውጥረት ተከትሎ አየር ሃይል በጠንቀቅ እንዲቆም ታዘዘ

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት የአርበኞች ግንቦት7 በወሰደው ፈጣን ጥቃት በርካታ የኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸውን ፣ ይህንን ተከትሎ የወልቃይትና አካባቢው ህዝብ ያሳያው ድጋፍ እና ሽምቅ ተዋጊዎችን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ወጣት መበራከት ያሰጋው ገዢው ፓርቲ፣ የአየር ሃይል አባላት በጠጠንቀቅ እንዲቆሙ ማዘዙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአየር ሃይል አባላቱ ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በሌሊት ፈረቃ እንዲሰሩ ...

Read More »

ሙስሊሙ ማህብረሰብ ለመሪዎቹ ያለውን ድጋፍ ገለጸ

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰሞኑን በእስር ላይ የሚገኙ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትን ጥፋተኛ ማለቱን ተከትሎ ፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዛሬ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ድምጹን አሰምቷል። በቤኒን መስጊድ እጅግ በርካታ ህዝብ በተገኘበት በተደረገው ተቃውሞ ሙስሊሙ ህዝብ፣ የመሪዎቹን ነጻነት ከሚያረጋግጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ ሌላ ውሳኔ እንደማይቀበል ግልጽ አድርጓል። ፍርድ ቤት ...

Read More »

በሰሜን ሸዋ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታድነው እየታሰሩ ነው

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ሐምሌ 3/2007 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋ ሮቢት ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ቤታቸውን ድረስ በመሄድ ፖሊስ እያደነ እንዳሰራቸው የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ የነበሩትን አቶ ዘነበ ደሳለኝ፣ የፓርቲው ንብረት ያዥ የሆኑትን አቶ መንግስቱ ተበጀና የቀድሞው አንድነት የቀጠና ...

Read More »

በጋዛ በሃማስ እንደታገተ የሚነገርለት ኢትዮ – እስራኤላዊ አድራሻው መጥፋት ዘረኝነት ነው ተባለ

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ 26 ዓመቱ ወጣት መንግስቱ አቭራ ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለበት አድራሻ አይታወቅም ፤ የእስራኤል መንግስትም ወጣቱን ለማፈላለግ ያደረገው ጥረት አለመኖሩ ዘረኝነት ነው ተብሎአል። በጋዛ በሃማስ እጅ እንደታገተ የሚነገረው ወጣት መንግስቱ፣ ቤተሰቦች “ልጃችን ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ አልቻልንም ፣ መንግስትም ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ የወሰደው ምንም ዓይነት እርምጃ አለመኖሩ ቅሬታ” ፈጥሮብናል ይላሉ። የጠቅላይ ሚንስቴር ...

Read More »

በጽናቷ የምትወደሰው ርእዮት አለሙ ተፈታች

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ በሽብር ወንጀል ተከሳ የ14 አመታት ጽኑ እስራት ከተፈረዳበት በሁዋላ፣ ለጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለቷ የእስር ጊዜዋ ወደ 5 አመት ዝቅ እንዲል ተደርጎላታል። ያለፉትን ሶስት አመታት በአስቸጋሪ ሁኔታ በእስር ቤት ካሳለፈች በሁዋላ ፣ የኢህአዴግ መንግስት አመክሮ ጊዜዋ አልቋል በሚል ፈቷታል። ርዕዮት በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የጽናት ምልክት ተደርጋ ትወሰዳለች። ይህ ...

Read More »

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በፍትህ ሚኒስቴር የተጣለባቸው እገዳ ምንም አይነት ስነልቦናዊ ጫና እንደማይፈጥርባቸው ተናገሩ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፍትህ ሚኒስቴር በሽብረተኝነት ክስ ለሚከሰሱ ጋዜጠኞችና የሃይማኖት መሪዎችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና አባላት ጠበቃ በመሆን የሚታወቁትን አቶ ተማም አባ ቡልጉን የዲሲፒሊን ግደፈት ፈጽመዋል በሚል ለአንድ አመት ከ7 ወር አግዷቸዋል። መታገዳቸውን ከሚዲያ የሰሙ ጓደኞቻቸው እንደነገሩዋቸው የገለጹት አቶ ተማም፣ በህጉ ቢሆን ነሮ የእግድ ደብዳቤው ከሚዲያ በፊት ለእርሳቸው መድረስ ይገባው እንደነበር ተናግረዋል። ድርጊቱ እርሳቸውን በህዝብ ...

Read More »