.የኢሳት አማርኛ ዜና

በጋሞ ጎፋ ዞና ኢህአዴግ ባለስልጣናት በእርስ በርስ ሽኩቻ እየታመሱ ነው

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ችግሩ የተፈጠረው በጋሞና በጎፋ ተወላጅ ባለስልጣኖች መካካል ነው። የዞኑን፣ የክልሉንና የፌደራል ስልጣኑን የተቆጣጠሩት የጎፋ ተወላጅ ባለስልጣኖች፣ ጋሞዎችን ሰድበዋል ፣ የጋሞ ተወላጅ ባለስልጣናትን በንቀት ያያሉ በሚል እርስ በርስ በጀመሩት ቁርሾ፣ የመንግስት ስራ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ የእርስ በርስ ሽኩቻውን ወደ ህዝብ በመውሰድ የጋሞ ባለስልጣናት የጋሞ ተወላጆችን አሰባስበው ለነገ የተቃውሞ ሰልፍ ...

Read More »

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጦር ነጋሪት ጆሮ እንዳትሰጥ አንድ ምሁር መከሩ

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ኤንድ ኢንተርናሽናል ስተዲስ የተባለው ተቋም ” ከአሜሪካ ጉዞ በፊት የአሜሪካ ፖሊሲ በኬንያና በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ባዘጋጀው ፓናል ውይይት ላይ የተገኙት በጆርጅ ማሶን ዩኒቨርስቲ የግጭት አስወጋጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ቴሬንስ ሊዮንስ እንደተናገሩት ኢህአዴግ በቅርቡ በኤርትራ ላይ ጦርነት ለማወጅ የሰጠውን መግለጫ አሜሪካ እንደማትደግፈውና እንደማትተባበር በግልጽ ማስታወቅ እንደሚገባት መክረዋል። የአሜሪካ የውጭ ...

Read More »

ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን አቤቱታ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በበሳውዲ አረቢያ ለረዢም ጊዜ በስደት ቆይተው ወደ ትውልድ ቀያቸው የተመለሱ በአማራ ክልል የሚገኙ ከስደት ተመላሾች ፤በራሳቸው ካፒታል እና ጥረት ለመንቀሳስ ቢሞክሩም “ልዩ ልዩ መሰናክል በመፍጠር የገዢው መንግስት ሊያሰራን አልቻልንም “በማለት ተናግረዋል፡፡‹‹ ከስደት ከተመለስን በኋላ በማህበር ተደራጁ በማለት ቢያደራጁንም የምንሰራበት የእርሻ መሬት ለማግኘት ለአምስት ወራት አሰቃይተውናል፡፡ ›› የሚሉት ከስደት ተመላሾች፣ እንዲሰሩበት የተሰጣቸው ...

Read More »

ኢህአዴግ ያሰባሰበው የህዝብ ድምጽ ” አስፈሪ” ነው ተባለ

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ 2007ትን መቶ በመቶ በሆነ ድምጽ አሸንፊያለሁ ብሎ ያወጀው ኢህአዴግ፣ ከምርጫው በሁዋላ ያሰባሰበው የህዝብ አስተያየት ለፓርቲውም ሆነ ለአገሪቱ ህልውና አስፈሪ መልእክት የያዘ ነው ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ሪፖርቱ በመጪው ነሃሴ በሚካሄደው የግንባሩ ጉባኤ ላይ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ህዝቡ በአስተዳዳር፣ በፍትህ፣ በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች፣ በውሃና በመብራት እጦት እየተሰቃየ መሆኑን ተጠናክሮ በቀረበው ሪፖርት ...

Read More »

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ወደየመን እየጎረፉ ነው ተባለ

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 9 2007) ግጭት ወደአለበት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ አሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትናንት ረቡእ ገለጸ ። በየመን ያለው የጸጥታ ሁኔታ አደገኛ ቢሆንም በብዙ ሺ  የሚቆጠሩት ስደተኞች አሁንም ድረስ ወደ ሀገሪቱ እየገቡ መሆናቸውን ረቡእ ከጄኔቫ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ የሰጡ የደርጅቱ ሀላፊዎች አስታውቀዋል። ከኢትዮጵያኑ በተጨማሪ የሶማሊያ ተወላጆች ወደየመን እየተሰደዱ እንደሆነ የገለጸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ ሆኖ ...

Read More »

ኢሳት ሙሉ የ24 ሰአት ዝግጅቱን ጀመረ

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በገዢው መንግስት ከፍተኛ አፈና የሚደርስበት የኢሳት የቴሌቪዝን ስርጭት ከሳምንታት ሙከራ በሁዋላ ዛሬ ሙሉ ስርችቱን በ ኤም 44 ሳተላይት ጀምሯል። አዲሱ ሳተላይት ጠንካራ ሲግናል ያለው ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በሙከራው ወቅት ስርጭቱን ለማፈን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን የኩባንያው ኢንጂነሮች ገልጸዋል። ተመልካቾች አልፎ አልፎ የድምጽ ወይም የምስል መዛባት ቢያጋጥማቸው ስርጭቱን ለማፈን ከሚደረግ ሙከራ የመጣ ...

Read More »

የመሳሪያ ትግሉን የህዝብ ብሶት የወለደው ነው ሲሉ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናገሩ

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲያችሁ አባሎች የትጥቅ ትግልን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በመርህ ደረጃ ኢህአዴግን ብሶት ከወለደው ሰው ጠመንጃ የማያነሳው ለምን ድነው ሲሉ ጠይቀዋል። ሰው መኖር ካልቻለ ምን አማራጭ አለ ሲሉ የጠየቁት ኢ/ር ይልቃል ሰው መቀመጫ መሄጃ ሲያጣ ቢሀድ ምን ይገርማል፣ አትሂድስ ለምን ይባላል? ብለዋል። እንዴውም ወጣቱ ...

Read More »

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት ወሰነ

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ቀደም ብሎ እንደተዘገበው በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እስረኞች ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችሁዋል ከተባልን፣ አቶ አንዳርጋቸው ቀርበው ይጠየቁልን የሚል መከላከያ መልስ ሰጥተው ነበር። ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው በአገር ውስጥ መኖራቸው ስለማይታወቅ ...

Read More »

ሰራዊቱ የትጥቅ ትግሉን እየተቀላቀለ እንደሆነ ተገለጸ

ኢሳት ዜና (ሐምሌ 07 2007 በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተንሰራፍቶ ያለውን አፈናና የአንድ ብሄር የበላይነት በመሸሽ በርካታ ወታደሮች የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ መሆናቸውን በሽግግር መንግስት ወቅት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የነበሩት አቶ መሀመድ ሀሰን ለኢሳት አስታወቁ። ሰሞኑን ወደ ኤርትራ በመጓዝ በዚያ የሚገኘውን የትጥቅ ትግል መመልከት እንደቻሉ የተናገሩት የቀድሞው ዲፕሎማት፣ በቆይታቸው ከሰራዊቱ ጋር የተሰደዱ በርካታ ወታደሮችን እንዳነጋገሩ ገልጸዋል። እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1994 ...

Read More »

ጋዜጠኛ ሃብታሙ ምናለ የአልሸባብ የቡድን ሴል ነህ ተብሎ መታሰሩ ተዘገበ

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፣ የቀዳሚ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅና የሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ ሪፖርተር የነበረው ሃብታሙ ምናለ ” የአልሸባብ የሽብር ወንጀል ቡድን ሴል ነህ” በሚል ተጠርጥሮ መገናኛ አካባቢ በሚገኘው አምቼ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ገልጿል። ሃብታሙ፣ “የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሚገኙበት ስብሰባ ላይ የሽብር ወንጀል ልትፈጽም በማሰብ ስትንቀሳቀስ ...

Read More »