.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአፋር በተከሰተው ረሃብ ዜጎች እየተሰደዱ ነው

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ካለፈው ወር ጀምሮ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ባለመዝነቡ በርካታ የቀንድ ከብቶች ሲያልቁ፣ ነዋሪዎችም ቀያቸውን በመልቀቅ ምግብ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው።ኢሳት ያነጋገራቸው ዜጎች እንደገለጹት፣ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንዲደርስላቸው ለመንግስት ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ከመንግስትም ሆነ ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች የቀረበላቸው ነገር የለም። በርካታ አርብቶአደሮች ውሃና ምግብ እናገኛለን በሚል ወደ ተንዳሆ የእርሻ ልማት እየተጓዙ ...

Read More »

የምግብ እና የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማእከላዊ እስታትስቲክስ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በተለይ በአዲስ አበባ እና በኦሮምያ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምግብ ኢንዴክስ 13 ነጥብ 9 በመቶ ሲጨምር፣ በአዲስ አበባ 26 በመቶ፣ አፋር 16 በመቶ፣ አማራ 6.7 በመቶ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 13.9 በመቶ፣ ኦሮምያ 21.2 በመተ እንዲሁም በትግራይ 5.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከፍተኛ ጭማሪ የታየባቸው የምግብ ክፍሎች እህል፣ ስጋ፣ ...

Read More »

የእርሻ ወቅትን ተከትሎ በኢትዮጵያና በሱዳን አርሶአደሮች መካከል ግጭት እየተከሰተ ነው

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የእርሻ ወቅቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች በመሬታቸው ላይ ለማረስ ሙከራ ሲያደርጉ፣ የሱዳን ባለሃብቶችና ታጣቂዎች ጥቃት እየፈጸሙባቸው ነው። አርሶ አደሮቹ “በገዛ አገራችን እርሻ እንዳናርስ በሱዳኖች እየተከለከልን ነው” ያሉ ሲሆን፣ በሱዳኖች በኩል የሚፈጸመውን በደል ለመሸከም እየከበዳቸው መምጣቱን ይገልጻሉ።ሱዳኖች መሬቱ የእነሱ መሆኑንና የኢትዮጵያ መንግስትም ማረጋጋጫ እንደሰጣቸው ይናገራሉ። የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ግን ይህንን አይቀበሉትም።

Read More »

አቶ ፍቃዱ በቀለና ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ በዋስ ተፈቱ

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ም/ሰብሳቢ የነበረውና ከሶስት ሳምንት በፊት በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ፣ ‹‹ሰዎችን ለግንቦት ሰባት በመመልመል ወደ ኤርትራ ትልክ ነበር›› የተባለው አቶ ፍቃዱ በቀለ ከታሰረበት ካሳንችስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በዋስ ተፈቷል፡፡ በተመሳሳይ ክስ ተጠርጥሮ ከ25 ቀናቶች በላይ ካሳንችስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው የቀድሞ አንድነትና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ...

Read More »

ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጣ መሬት ማስመለሱን ገለጸ

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኮሚሽኑ ባለፉት 5 አመታት ፣ 5 ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የተዘረፈ መሬት ማስመለሱን ገልጿል። 27 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችንና 22 መኪኖችን ማስመለሱንም ገልጿል። ኮሚሽኑ ሙስናን ለመዋጋት ጥረት ቢደረገም ሙስና አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታውቋል። 90 ሺ የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን ማስመዝገባቸውን ኮሚሽኑ ቢገልጽም፣ መቼ ይፋ እንደሚያደርግ ወይም እስካሁን ይፋ ለማድረግ ለምን እንዳልቻለ የገለጸው ...

Read More »

የጋሞ ጎፋ ዞን ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 20 ቀናት ሲጓተት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በአርባምንጭ የተካሄደ ሲሆን፣ ህዝቡ መንግስት አይካፈፍለን በማለት ቁጣውን ሲገልጽ ተሰምቷል። ጎታና ቱፋ ታድላ የተባለ ጸሃፊ የጋሞን ህዝብ የሚያንቋሽሽ መጽሃፍ ማዘጋጀቱን ተከትሎ፣ የአካባቢው ህዝብ መንግስት ጋሞን ከጎፋ ህዝብ ጋር ለማጋጨት ሆን ብሎ የተሸረበው ሴራ ነው በማለት ሲቃወመው ቆይቷል። “የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ይመጣሉ፣ አርበኞች ...

Read More »

የስራ አጡ ቁጥር የህልውና ስጋት ደቅኗል ሲል ብአዴን ገለጸ

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ብአዴን በባህርዳር ባካሄደው 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ክልሉን የገጠሙትን ፈተናዎች አቅርቧል። ጉባኤው በዝግ የተካሄደ ሲሆን፣ አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች ድርጅቱ የገጠመውን ፈተና በዝርዝር አቅርበዋል። ዝምታን የመረጠው ህዝብ በስርዓቱ ደስተኛ እንዳልሆነ በርካታ አመላካች ነገሮች መኖራቸው የተብራራ ሲሆን፣ “ህዝብ አኩርፏል፣ ምን እናድርግለት ?” የሚል ጥያቄም ተነስቷል። በእየአመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ስራአጥ ወጣቶች መምጣታቸው ...

Read More »

የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞች ቃል የተገባላቸው የዲያስፖራ አባላት አዲስአበባ እየገቡ ነው

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን አባላትን በቀላሉ ለመያዝ እንዲመች በሚል ስሌት የዲያስፖራ ቀን በኣል የተዘጋጀ ሲሆን፣ በበአሉ ላይ ለሚገኙ የዲያስፖራ አባላት የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞች እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል። ከሰሜን አሜሪካ የመጡ የኦሮሞ ተወላጆች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት “በበዓሉ ላይ ከተገኙ በመረጡት አካባቢ ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ወዲያውኑ ከሊዝ ነጻ እንደሚሰጣቸው፣ ወደኢንቨስትመንት የሚገቡ ከሆነ ...

Read More »

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለ3ኛ ጊዜ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ቀረ

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተከሰሱት 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ ፣3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ ፣4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን እና 5ኛ ተከሳሽ አቶ አንሙት የኔዋስ የመከላከያ ምስክር ሆነው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለዛሬ ሀምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የደረሰው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ...

Read More »

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ወገኖች ጋር ተባብሮ ትግሉን እንዲያካሂድ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን የፍርድ ውሳኔ አውግዟል። “ስርዓቱ ለመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው እውቅና ሰጥቶ ሲደራደር” ከቆየ በሁዋላ ፣ አሸባሪ ብሎ መክሰሱ፣ ‹‹ሽብር›› የሚባለው ክስ ስርዓቱ ያልፈለገውን የሚያስርበት ፍርድ ቤቱና ህጉም የአገዛዙ ዋነኛ መሳሪያ ሆነው መቀጠላቸውን ያመላክታል ብሎአል። በኮሚቴው ላይ የተወሰደው እርምጃ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ይበልጡን ትግሉን አጠናክሮ፣ ከሌሎች ...

Read More »