ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፣ 2007) ሰሞኑን በአፋር ክልል የተከሰተው ድርቅ ተባብሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁምና የቤት እንስሳት መሞታቸውን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ በክልሉ በክረምት ወቅት የሚጠበቀው ዝናብ በሚፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለፅ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ አፋር ክልል መዲና በሚወስደው ዋናው አስፋል መንገድ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁምና የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ምዕራባውያን ፖለቲከኞች አንዳርጋቸው ጽጌ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፥ 2007) የአሜሪካ ፤ የብሪታኒያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ አመራሮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ። የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄያቸው ያቀረቡት ...
Read More »የሁለቱ ክልሎች ገዢዎች እርስበርሳቸው እየተወነጃጀሉ ነው
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትግራይ እና በአማራ ክልል ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፍ ዝቅ ሲል ቆይቶ ፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ በአካሄደው ግምገማ ላይ እንደገና አገርሽቶበታል። የትግራይ ክልል ገዢ አቶ አባይ ወልዱ የተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎችን በመያዝ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው አወዛጋቢ መሬት ፣ ከአማራ ክልል ገዢ ጋር በድንበር አካበባ ያደረጉት ውይይት፣ በዘለፋና በጸብ ከተቋጨ ከወራት በሁዋላ፣ ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከህወሃት የደህንነት አባላት ጋር መስማማት አልቻሉም።
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ ባደረገው ግምገማ ፣ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እርሳቸውንና ቤተመንግስቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ሃይሎች ጋር ተስማማተው መስራት አልቻሉም የሚል ትችት ከቀረበባቸው በሁዋላ፣ ግንኙነቱ ወደ ባሰ ደረጃ መውረዱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም “በቤተሰቦቼና እና በእኔ ላይ በሚደረገው አላግባብ ክትትል ተሰላችቻለሁ” የሚል ንግግር በሁለተኛው ዙር የኢህአዴግ ሂስ እና ግለ ሂስ የአቋም ግምገማ ላይ ተናግረዋል። ...
Read More »የደቡብ ሱዳን መንግስት ድርድሩ ከአዲስ አበባ እንዲወጣ፣ ስዩም መስፍንም እንዲቀየሩ ጠየቀ
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደብዩብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተደራዳሪን ከአገሯ አስወጥታለች። እርመጃው የተወሰደው የደቡብ ሱዳን መንግስት አንድ የተቃዋሚ አባል ወደ አዲስ አበባ እንዳይሄድ ማገቱን ተከትሎ ነው። ደቡብ ሱዳን የድርድሩ ቦታና አደራዳሪው ስዩም መስፍን እንዲቀየር የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ የሰጡት ምክንያትም፣ አዳራዳሪዎቹ ራሳቸው በአገራቸው የተቃዋሚ ሃይሎችን ያስተናግዳሉ፣ እነሱ ሰላማዊና ...
Read More »በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች አብዛኛዎቹ ከደረጃ በታች ናቸው ተባለ
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ ዓለም አቀፍ መስፈርት የሚያሟሉ ሆቴሎችን ደረጃ ለመመደብ በተካሄደው ጥናት 98 ያህል ሆቴሎች ከደረጃ በታች ሆነው መገኘታቸው ይፋ ሆኗል። በዓለም አቀፉ ቱሪዝም ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ተጠንቶ ባለፈው ቅዳሜ ይፋ በተደረገው ውጤት መሠረት ለውድድር ከቀረቡት 136 ያህል ሆቴሎች ደረጃ ማግኘት የቻሉት 38 ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ባለ5 ኮከብ ያገኙት 3 ሆቴሎች፣ ባለ4 ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 በሜልቦርን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ማድረጉን አስታወቀ
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውስትራሊያ የሜልቦርን የአርበኞች ግንቦት7 ጽ/ቤት ” ሀገራችን ስላለችበት ሁኔታ እንምከርበት” በሚል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል ብሎአል። የድርጅቱ የሜልቦርን ከተማ ተጠሪ አቶ ነብዩ መላኩ ፣ “የድርጅት አጥር ሳይከልለን ትግሉን እንርዳ” የሚል መልእክት ሲያስተላልፉ፣ ዶ/ር ታደሰ ብሩ በስካይፕ ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ ” ትግሉ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን ገለጸው፣ “ትግላችን ...
Read More »ብቃት የተላበሰ አመራር የለንም ሲሉ አቶ አለምነው መኮንን ተናገሩ
ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ብአዴን የየተመሠረተበትን 35ዓመት ህዳር 11 ቀን 2008 ዓ.ም ለማክበር በማሰብ፣ ከሚዲያ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ብአዴን የህዝቡን ፍላጎት የሚያሟላ ብቃት የተላበሰ አመራር የለውም ብለዋል። በግዮን ሆቴል ብአዴን በጠራው የሚዲያና ኮምኒኬሽን ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስብሰባ ላይ ማብራሪያ የሰጡት አቶ አለምነው መኮንን፤ ብአዴን ያለበትን ተግዳሮቶች በዘረዘሩበት መግለጫቸው፣ ...
Read More »ድርቁ የኢሊኖ ውጤት ነው ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች የታየው ዝናብ እጥረትና የተከሰተው ድርቅ ኢሊኖ እየተባለ የሚጠራው የአየር መዛባት የፈጠረው ነው ብሎአል። በተለያዩ አካባቢዎች የእንስሳት መኖና እና የምግብ እጥረት ተፈጥሯል ብሎአል። ሚኒስቴሩ በውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የችግሩን አሳሳቢነት ይፋ ማውጣታቸውን ተከትሎ የሰጠው የመጀመሪያ መግለጫ ነው። ገዢው ፓርቲ አገሪቱ በምግብ ራሱዋን መቻሉዋን በተደጋጋሚ ሲናገር ቢሰማም ፣ የዝናብ እጥረት ሲያጋጥም ...
Read More »የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆሉ ተዘገበ
ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ3.25 ቢሊዮን ዶላር ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉን የንግድ ሚኒስቴርን በመጥቀስ ኒው ፎልቶን ዘግቧል። አሁንም አገሪቷ ወደ ውጭ አገራት ከምትልካቸው ምርቶች ውስጥ ቡና ቀዳሚነቱን እንደያዘ ሲሆን፣ ከቡና ሽያጭ ገቢ 780 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱንና ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 8.5 % ጭማሪ አሳይቷል። የኢትዮጵያ የውጭ ...
Read More »