ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንድ ዓመት በላይ በተንዛዛ የፍርድ ቤት ቀጠሮ በእስር ሲማቅቁ የነበሩት አራቱ የፖለቲካ እስረኞችን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች፣ የልደታው ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት፣ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከሳሾችን አሰናብቷል። በዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች አቶ ሀብታሙ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብቻ በያመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ይዘረፋል ተባለ
ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ መመሪያ የተቋቋመው አጥኚ ቡድን የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመንን አስመልክቶ በ51 የአዲስ አበባ አድባራት ባካሔደው ጥናታዊ ሪፖርት፣ በየወሩ 100 ሚሊዮን ብር፣ በዓመት ደግሞ 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር በሙስና እንደሚዘረፍ ገልጿል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እና ሰፊ የመሬት ይዞታ ቢኖሯትም የሚገባውን ያኽል ተጠቃሚ ...
Read More »በሰቆጣ ከተማና አካባቢዋ ከወር በሁዋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ዝናብ በመዝነቡ ህዝቡ ደስታውን ገለጸ
ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ሰኔ 15 እና 16 የክረምቱ ዝናብ ከዘነበ በሁዋላ፣ ዝናብ ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት አልዘነበም። ሃምሌ 29 ቀን ደግሞ ለአንድ ጊዜ ዘንቦ በመጥፋቱ ፣ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጅ ትናንት ከምሽቱ 11 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ መዝነብ የጀመረው ዝናብ እስከ 12 ሰአት ከ10 ደቂቃ ድረስ በመዝነቡ፣ የከተማው ...
Read More »የአዲስአበባ ከንቲባ የስር አመራሮቻቸውን ወቀሱ
ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል አቶ ድሪባ ኩማ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በከተማዋ መቀነስ ያልቻለው መመሪያዎችን በቁርጠኝነት መፈጸም የማይችል አመራር በመኖሩ ነው ሲሉ በስራቸው የሚገኙ አመራሮችን ወቅሰዋል፡፡ ከንቲባው ይህን የተናገሩት በሰኔ ወር 2007 የተጠናቀቀውን የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ ዓመት የሚጀምረው ሁለተኛውን ዕቅድ አስመልክቶ ከከፍተኛ ...
Read More »አቶ በረከት ስምኦን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው ሊሰናበቱ ነው
ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመሠረተበትን 35ኛ ዓመት በታላቅ ፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኘው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ንቅናቄው ሰሞኑን በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ እንደማይመረጡ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ህወሃትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ያሰናብታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የብአዴን ምንጮች እንደሚሉት ኢህአዴግ ...
Read More »ከምርጫው ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውን ከ80 በላይ የፓርቲ አመራሮች መታሰራቸውን ሰመጉ አስታወቀ
ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉ ባወጣው 137ኛ ልዩ መግለጫ፣ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውንና 83 የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች መታሰራቸውን በስም ዘርዝሮ አቅርቧል። በደብረማርቆስ ከተማ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም የተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ፣ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የተገደለ መሆኑን የቅርብ ቤተሰቦቹ ለሰመጉ መግለጻቸውን ጠቅሷል። በሚዳቀኝ ወረዳ ...
Read More »በኢትዮጵያ የታየውን ድርቅ ለመቋቋም ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ
ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የመኸርና የክረምት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉና በመዘግየቱ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሰለባ ለሆኑ ከ4 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ግምቱ ከ386 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ7 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አፋጣኝ የሆነ የሕይወት አድን የምግብና ሌሎች እርዳታዎች እንደሚያስፈልጉ ጠቅሷል። በመላ አገሪቱ ...
Read More »በወላይታ ዞን በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውና መደብደባቸው ተገለጸ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የዞኑ አስተዳደር ህገ ወጥ ግንባታ ናቸው ያላቸውን መኖሪያ ቤቶች ለማፍረስ መሞከሩን ተከተሎ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውና መደብደባቸው ተገለጠ። በሳምንቱ መገባደጃ በዞኑ በምትገኘው የቦሎሶሶሬ ወረዳ በተቀሰቀሰ በዚሁ ግጭት ከ20 በላይ ነዋሪዎች በላይ ነዋሪዎችና ህገ-ወጥ ናቸው የተባሉትን ግንባታዎች ለማፍረስ የተሰማሩ ከ10 በላይ አፍራሽ ግብረ ሀይሎች ጉዳይ እንደደረሰባቸው ከሀገር ...
Read More »በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተገደሉት ሰዎች ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪዎች ተናገሩ
ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአለፈው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ የአካባቢው ህዝብ የስርዓቱ ደጋፊ አይደለም፣ በምርጫውም ለመሳተፍም ሆነ ከመንግስት ጎን ለመቆም ፍላጎት አላሳየም በሚል የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአካባቢው ተወላጆች፣ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ እስካሁን በመንጌ ወረዳ 11 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ግጭቱ ወደ ዳቡስ አካባቢም የተዛመተ በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። በመንጌ ከተማ ...
Read More »በደቡብ ወሎ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ
ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። ከታሰሩት መካከል 6 ያክሉ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ እቅድ ተይዞ በነበረበት በቱሉ አወሊያ አንድ ፖሊስ ተደብድቦ አቀስታ ሆስፒታል ገብቷል። በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ ወጣቶችን ከቤታቸው እያወጣ መደብደቡን የአይን እማኞች ...
Read More »