ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተያዘው ክረምት በአብዛኛው ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍሎች የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ የሰቆጣ ከተማና የአካባቢው ወንዞች በመድረቃቸው የውኃ እጥረቱ መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ነዋሪዎች ፣ በዝናቡ እጥረት የተነሳ የጉድጓድ ውሃ መጠን በማነሱ የሚጠጣ ውኃ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ “በከተማዋ በአጠቃላይ የውኃ ችግር ተከስቷል፡፡በከተማዋ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ ልማት ጽህፈት ቤት ምን እየሰራ እንደሆን አናውቅም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ለመለስ አካዳሚ ግንባታ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ለኢህአዴግ ፓርቲዎች ተከፋፈለ
ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርሶአደሩ ፣ የመንግስት ሰራተኛውና ነጋዴው ለቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አካዳሚ ግንባታ በሚል በግዴታ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍል ቢደርግም፣ ምክንያቱ በውል ባልተገለጸ ሁኔታ ገንዘቡ ለኢህአዴግ አራት ድርጅቶች ማለትም ለህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ተከፋፍሏል። ሁሉም ድርጅቶች 80 ሚሊዮን 566 ሺ 221 ብር ደርሶአቸዋል። ገንዘቡን ለመንግስት ወይም ለከፈሉት ዜጎች መመለስ ሲገባ ድርጀቶች እንዲከፋፈሉት መደረጉ ...
Read More »ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በመዲናዋ አዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ ለቀጣዩ ሦስት ዓመታት ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን፣ አምስት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላትም በጉባኤው ተመርጠዋል፡፡ ጉባኤው የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም መርጧል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲን ለቀጣይ ...
Read More »አርበኞች ግንቦት ሰባት በላስ ቬጋስና በለንደን የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ!!
ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርበኞች ግንቦት ሰባት የጀመረውን የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማጠናከር በላስቬጋስ ከተማ የተጠራው የሀገር አድን ጥሪ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎና በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በእለቱ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ከፍተኛ ገንዘብ መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል፡ በዚህ ለሰማእታት በተደረገ የህሊና ጸሎት የተጀመረ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ሙሉነህ እዩኤልና አቶ ጋሻው ገብሬ የንቅናቄው አመራር አባላት በአዳራሽ ተገኝተው አስፈላጊውን ...
Read More »በወረ ጃርሶ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለት ወጣቶች ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ ተጨማሪ አርሶአደሮች እየተያዙ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ከ380 በላይ ሰዎች ተይዘው ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ገሚሶቹ ሴቶች ናቸው። አብዛኞቹ ሴቶቹ የተያዙት በርካታ አርሶአደሮች አፈሳውን ለማምለጥ ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ በባሎቻቸው ቦታ ሲሆን፣ የተወሰኑት ደግሞ ለሽፍቶች ምግብና ውሃ አቀብላችሁዋል ተብለው ነው። በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ...
Read More »ጎጃም ውስጥ በድርቁ ምክንያት በሰውና እንሰሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው
ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ አድማሱን በማስፋት ጎጃም ውስጥም ተከስትዋል።በድርቁ ጉዳት በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል፡፡ ድርቁ አስከፊ ደረጃ እንደደረሰ መንግስት ማመኑን የገለፁት ነዋሪዎች ነሃሴ ...
Read More »በኦሮምያ ደቡብና ሶማሊያ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የማንበብና የመጻፍ ክህሎት ከዜሮ በታች ነው
ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል በሚተገበረው የክላስተር ፖሊሲ በተለይ በኦሮምያ ፤ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የማንበብ እና የመፃፍ ክህሎታቸው ከዜሮ ነጥብ በታች መሆኑን ከትምህርት ሚኒስትር የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡ የተማሪዎቹ የሂሳብ ማስላት ችሎታ መዳከሙን፣ በሳይንስ ትምህርት ላይ ለውጥ እንዲመጣ የተጣለው ግብም አለመሳካቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል። መምህራን በትርፍ ጊዜያቸው ...
Read More »አምቡላንሶች ለተለያዩ ፖለቲካዊ አገልግሎት መዋላቸው እንዲቆም ተጠየቀ፡፡
ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለእናቶችና ህጻናት ጤንነት ታስቦ ከተለያዩ ለጋሽ ሃገራት በእርዳታ የተገኙትን አምቡላንሶች ከታሰበላቸው አገልግሎት ውጭ ለተለያዩ ፖለቲካዊ ስራ በመመደብ ሲጠቀሙባቸው እንደነበር በምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የሚገኙ አንድ የስራ ኃላፊ ገለጹ፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት ኃላፊ እንደተናገሩት የወረዳ አስተዳዳሪዎች በቂ በጀት እንዲመድቡ መመሪያ ቢሰጣቸውም ችላ በማለት አገልግሎት መስጠት የነበረባቸው አምቡላንሶች ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ችግር ...
Read More »በአውሮፕላን ስዊድን የገባው ስደተኛ አየር መንገድ ውስጥ ባለው በዘረኝነት መማረሩን ገለጸ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 15 ፣ 2007) ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞ አውሮፕላን ውስጥ በእቃ መጫኛ ውስጥ ተደብቆ በስዊድን ጥገኝነትን የጠየቀው ኢትዮጵያ በአየር መንገድ ውስጥ በአንድ ብሄር የበላይነት የሚደርሰው በደልና ግፍ ለህዝብ ለማጋለጥ ሲል ድርጊቱን መፈጸሙን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አስታወቀ። የ 24 አመቱ ወጣት ይርጋሸዋ ማሽላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር የበላይነት ሰፍኖ እንደሚገኝ እና በአየር ...
Read More »ከ300 በላይ አርሶአደሮች ታስረው እየተደበደቡ ነው
ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ በሚገኙ በፋጂ ኢጀርሳ፣ ላንቱ ወላርጊ እና ምእራብ ኮርጎጎ ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ300 በላይ አርሶአደሮች ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ኢጀርሳ መንደር ውስጥ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረው እየተደበደቡ መሆኑን ቤተሰቦቻቸውና እስራቱን ለማምለጥ የተደበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አርሶ አደሮቹ የታሰሩት ሻሾ አንበሳ ...
Read More »