ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በሃመር ብሄረሰብና በዞኑ ፖሊስ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የአንድ ሻለቃ ጦር አባላት በርካቶቹ ኮብልለው በመጥፋታቸው ፣ ለወታደሮቹ መጥፋት ምክንያት ናቸው የተባሉ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት መካካል የሚታየው አለመተማማንና ልዩነት በመስፋቱ እርስ በርስ እስከመጋጨት ደርሰዋል። ከወር በፊት በሃመር ወረዳ በተፈጠረው ግጭት በርካታ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ የፈረሰበት ወጣት ራሱን አጠፋ
ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን ያጠፋ ሲሆን፣ ባለቤቱም ራሱዋን ስታ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸሎት እየተደረገላት ነው። ወጣት ታምራት ትናንት ነሃሴ 26 የቀብሩ ስነስርአት ተፈጽሟል። ሚሚ ባቴ የተባለች የአንድ ሳምንት መጫትም በላዩዋ ላይ ቤቷ በመፍረሱ፣ ጎዳና ላይ ወድቃለች። ...
Read More »በግለሰቦች እጅ የሚገኘውን የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መልሶ ለመቀማት እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡
ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ከምርጫ 2007 በፊት ህብረተሰቡ መሳሪያ እንዲታጠቅ በመፍቀድ ህጋዊ ያደረገውን የመሳሪያ ፈቃድ በመንጠቅ መሳሪያዎችን ለመሰብሰብ ስልቶችን እየቀየሰ መሆኑ ምንጮች ለኢሳት አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ህጋዊ ለማድረግ ምዝገባ ካካሄደ በኋላ የመሳሪያ ፍቃድ በመስጠት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲከላከልበት መፍቀዱን ተከትሎ፣ ከአጎራባች ክልሎች በተለይም ከትግራይ ክልል በተሰማው ተቃውሞ በየግለሰቡ እጅ ...
Read More »አዲስ አበባ መስተዳድር ከ 4 ሺ በላይ ሰራተኞችን ተጠያቂ ሊያደርግ ነው
ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ 221 አመራሮችንና 4 ሺ 100 ሰራተኞችን ገምግሞ ጥፋተኛ ብሎአቸዋል። ሰራተኞቹ በህግ ይጠየቃሉ ተብሎአል። ኢሳት የሰራተኞችን ግምገማ በተመለከተ ከወር በፊት ባቀረበው ዘገባ፣ አብዛኞቹ ሰራተኞች እና አመራሮች ዝቅተኛ ነጥብ እንደተሰጣቸውና ሊባረሩ እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዚሁ ግምገማ ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታውም ዝቅተኛ የግምገማ ነጥብ የተሰጣቸው በመሆኑ፣ ከሚቀነሱት መካካል ሊሆኑ ይችላሉ።
Read More »በከባድ መኪና ውስጥ ተደብቀው ሲጓዙ የነበሩ መቶ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዛምቢያ ፖሊስ ተያዙ
ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስደተኞቹን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ከባድ መኪና በናካንዳ የድንበር የፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ ፓሊስ የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ተይዘዋል። ሕገወጥ ስደተኞችን በማዘዋወር ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የዛንቢያ ዜጎችም አብረው ተይዘዋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአስር እስከ ሃምሳ ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። ስደተኞቹ በአሁኑ ወቅት በኳቤ የደኅንነት እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙና የከባድ መኪናውን የመጨረሻ መዳረሻ ለማወቅ ...
Read More »የታሰሩ ሴቶች እንዲፈቱ ዘመቻ ሊጀመር ነው
ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ወኪል የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት የታሰሩ 20 ሴቶች እንዲፈቱ ዘመቻ ይጀምራሉ። ከ20 ዎቹ ሴት እስረኞች መካከል ብሌን መስፍን፣ ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንድይፍራው ከኢትዮጵያ፣ ዋንግ ያኑ፣ ጋዎ ያኑና ሊዩ ዚያ ከቻይና፣ ካጂያ ኢስማዮላ ከአዘርባጃን፣ አስቴር ዮሃንስ ከኤርትራ፣ ማትሉዩባ ካሚሎቫ ከኡዝቤክስቲያን፣ ፒዮ ፒዮ አውንግ ከበርማ፣ ...
Read More »የሚመገቡት በማጣታቸው ወጣቶች እየተሰደዱ ነው
ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርቁ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት የሚመገቡት ባለመኖሩ አብዛኛው ወጣቶች ወደ ጠረፍ ከተማ በመሰደድ ላይ ናቸው። በሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ ዞን ያሉ ነዋሪዎች በድርቁ ምክንያት እንስሳት አልቀዋል፤ መሬት የሌላቸው ወጣቶች የቀን ስራ በመስራት ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ምግብ ፍለጋ ወደ ጠረፍ ከተማ እየተሰደዱ ነው። መሬት የሌላችው ወጣቶች በየአካባቢያቸው መሬት ተከራይተው በማምረት ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድሩ እንደነበር የሚገልጹት ...
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከጠቅላላ ጉባኤው ሲመለሱ ተደበደቡ
ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፈቃድ በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ ላይ ተደብድበው መዘረፋቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ ጌትነት የሰማያዊን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አረካ ላይ ተደብድበው ስልካቸውንና የአንገት ሀብላቸውን ተቀምተዋል። የቀማቸው ሰው እጅ ከፍንጅ ቢያዝም ፖሊስ እርሳቸውን አስሮ ወንጀሉን የፈፀመውን ሰው ለቆታል። አቶ ጌትነት ድርጊቱ በመንግስት ...
Read More »በቁጫ ሰዎች ታሰሩ
ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነትና ከአስተዳደር መብት ጋር በተያያዘ ለአመታት የዘለቀው የቁጫ ህዝብ ጥያቄ፣ ምላሽ ባላገኘበት ሁኔታ፣ አሁንም የሚታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከ140 በላይ የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ካለፉት ሁለት አመታ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ ሰሞኑን ሌሎች የመንግስት ሰራተኞችም መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል። በአካባቢው የሚታየው አፈና ከአቅም ...
Read More »አራት ንፁሃን ሶማሊያዊያን በኢትዮጵያ ሰራዊት ተገደሉ
ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር የዘመተው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት በመሃከላዊ ሶማሊያ በገልጋዱ ግዛት ውስጥ አራት ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎችን በግፍ መግደሉንና ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ መምህራን መሆናቸው ተገልጿል። ”በአካባቢያችን በኢትዮጵያ ታጣቂዎች እንደዚህ ዓይነት አስቀያሚ እርምጃዎች እየተወሰዱብን እኛ ከዚህ በላይ ልንታገስ አይገባንም።ይቅርታ ልናደርግላቸውም አይገባንም።ካለርህራሄ አራት ንፁሃን ሰላማዊ ዜጎቻችንን ገለውብናል።” በማለት ...
Read More »