.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኤርትራ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች

ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤኤፍፒ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ የሚያሰማው የጦርነት ዛቻና አገሪቱን እወራለሁ እያለ የሚያሰማው መግለጫ ጨምሯል። የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ህወሃት በተለየ ሁኔታ በኤርትራ ላይ ዛቻ እያሰማ ነው። በክረምቱ ወር ይሰማ የነበረው ፉከራ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ተጠናክሮ መቀጠሉን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ገልጿል። የህወሃት አገዛዝ ኤርትራን እንዲወር ከአሜሪካ ፈቃድ ...

Read More »

በጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ የክለሳ ምዝገባ መታሰቡ ሕዝብን አስቆጣ

ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ መኩሪያ ኃይሌ የሚመራው የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የራራ መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት በድጋሚ የተካሄደውም ምዝገባ ዳግም እከልሳለሁ ማለቱ አብዛኛዎችን ነዋሪዎች አስቆጣ፡፡ ሚኒስቴሩ በመጋቢት 2007 ዓ.ም የወጣው 10ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ ነዋሪው ከአቅሙ በላይ መሆኑን መግለጹን መነሻ በማድረግ ተመዝጋቢዎች አቅማቸውን የፈቀደውን እንደሚዘገቡ ዳግም ዕድል ለመስጠት ...

Read More »

የምግብ እና የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ

ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማእከላዊ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት ባወጣው ሪፖርት በነሃሴ ወር ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዋጋቸው ጨምሯል። የጭማሪዎች መጠን ከክልል ክልል ሲለያይ አዲስ አበባ ፣ አፋርና ኦሮምያ ከፍተኛ ጭመሪ ታይቶባቸዋል። የምግብ ዋጋ ከአምናው ጋር ሲተያይ 11 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ደግሞ በ8 ነጥብ 9 ጭማሪ አሳይተዋል። በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላና አትክልት ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 የተሳኩ ስብሰባዎች ማድረጉን አስታወቀ

ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መረጃ እንደገለጸው በተለያዩ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በተካሄዱ የአገርን አድን ጥሪዎች ህዝቡ ለንቅናቄው ያለውን ድጋፍ ገልጿል። ብጹ አቡነ መቃርዮስና አቶ ብዙነህ ጽጌ በእንግድነት በተገኙበት በስዊዘርላንድ በተካሄደው ስብሰባ፣ ሴቶች በውድ ገንዘብ የተገዙ የእጅ አምባራቸውን ሰይቀር ለግሰዋል። በዝግጅቱም ከፍተኛ ገንዘብ ተሰብስቧል። የቶሮንቶ፣ ካልጋሪና ኦክላንድ ስብሰባዎችም እንዲሁ በጥሩ ውጤት መጠናቀቃቸው ተገልጿል።በኖርዌይ ስታቫንገር ...

Read More »

አስራ አንድ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ካለሕጋዊ ቪዛ በመግባታቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ፓንጋኒ ውስጥ አስራስምንት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ካለፍቃድና ሕጋዊ ቪዛ ኬንያ ውስጥ በመግባት የተከሰሱ ሲሆን ሰባቱ ፓሊስ በእጃችን ላይ የነበረውን ሕጋዊ ዶክመንቶች ወስዶብናል በማለት ክሱን ያስተባበሉ ሲሆን ሌሎች አስራ አንዱ ግን በአስተርጓሚ በኩል በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል የቀረበባቸውን ክስ ማመናቸውንና ለፍርድ ውሳኔው ለሴፕቴንበር 8 ቀን መቀጠራቸውን ዘስታር ዘግቧል።

Read More »

አልሸባብ ሁለተኛዋን ስትራቴጂክ ከተማ ተቆጣጠረ

ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ የአፍሪክ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም በኡጋንዳና በኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የነበረው በመሃከላዊ ሂራን ግዛት ቡቅአበል ሁለተኛው ስትራቴጂካዊ ከተማ በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ውሏል። እስላማዊ ታጣቂዎቹ በስተደቡብ ሶማሊያ የምትገኘውን ኩርቱዋሬንና ከሞቃዲሾ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘውን የጃናሌን ከተሞች ባለፈው ሶስት ቀናት በቁጥጥራቸው ስር ማድረጋቸው ይታወሳል። በሶማሊያ ከ6,200 በላይ የሚሆኑ የኡጋንዳ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን ...

Read More »

በአርባምንጭ የአንድ ቤተሰብ አባላት በስቃይ ላይ ናቸው

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ የአንድ ቤተሰብ አባላት ልጆቻችሁ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ናቸው በሚል ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ለኢሳት ገለጹ። ፈቃዱ አበበ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወንድምህ አርበኞች ግንቦትን እንዲቀላቀል አድርገኸዋል በሚል ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ታስሮ እየተሰቃየ ሲሆን፣ የእርሱ ታናሽ ወንድም ደግሞ በፖሊሶች ከፉኛ ተደብድቧል። ይህም አልበቃ ብሎ፣ ...

Read More »

የኢህአዴግ ካድሬዎች መረጋጋት ተስኖአቸዋል

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የመስተዳድሩን ካድሬዎች ገምግሞ ለአብዛኞቹ ዝቅተኛ ነጥብ መስጠቱን ተከትሎ እና ከ4 ሺ በላይ ሰራተኞች በወንጀል እንደሚጠየቁ መነገሩን ተከትሎ፣ የመስተዳደሩ የኢህአዴግ አባላት ከፍተኛ መረበሽ ውስጥ ገብተዋል። በዚህም የተነሳ መስተዳድሩ አገልግሎቶችን መስጠት አቁሟል በሚባልበት ደረጃ መድረሱን ምንቾች ገልጸዋል። “ምንም ስራ እየተሰራ አይደለም፣ ካደሬው በሙሉ ድንጋጤ ላይ ነው፣ ሹመትና ሽረቱን እየጠበቀነ ...

Read More »

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የሆድ ጥያቄ የሚያነሱ ዲያስፖራዎች ሲል በባህርዳር የተገኙትን ዲያስፖራዎችን ተቸ

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዲያስፖራ ቀንን ለማክበር በባህርዳር የተገኙት 50 የዲያስፖራ አባላት፣ በመንግስት ወጪ ባረፉበት ኢትዮ-ስታር ሆቴል በቢንቢ ትንኝ መበላታቸውን እንዲሁም የተመቻቸ ምግብ አልቀረበልንም የሚል ምክንያት በመጥቀስ፣ ቁርስና ምሳ አንበላም ብለው አድማ ያደረጉ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ክልሉ በመደወል እንግዶቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወደ ሚያርፉበት ጣና ሆቴል እንዲዛወሩ ተደርጓል። የመስተዳደሩ ባለስልጣናት የሆድ ጥያቄ የሚያነሱ ዲያስፖራዎች ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በታችኛው ኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎች ላይ መጠነ-ሰፊ የሰብዓዊ መብት ረገጣ መፈጸሙን የሚያጋልጥ ሪፖርት ይፋ ሆነ።

ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለጋሽ አገራት በተለይም የእንግሊዝ መንግስት ሪፖርቱን ቢደብቀውም፣ የአውሮፓ ህብረት ፍርድ ቤት ሪፖርቱ ይፋ እንዲሆን ባዘዘው መሰረት ይፋ ሆኗል። ሰርቫይቫል ኢን ተርናሽናል ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ጥናቱን ያከናወኑት -የኢትዮጵያ ዋነኛ እርዳታ ሰጪ የሆኑት ዩናይትድ ኪንግደም፣ዲ.ዔፍ አይ ዲ የተሰኘው የም እራባውያን ለጋሾች ቡድን ፣ የአሜሪካ የረድ ኤት ድርጅት የሆነው -ዩ ኤስ ኤይድ እና የአውሮፓ ...

Read More »