ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢሮው በጣና ሐይቅ ላይ በቱሪስት ማስጎበኘት ስራ በተሰማሩ ማህበራት አሰራር ጣልቃ በመግባቱ በተከሰሰበት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡ ባለስልጣን ቢሮው የቱሪስት ጀልባዎችን በተራ ለማሰራት ያደረገው የተራ ማስከበር ስራ ህግና ደንቡን ያልተከተለ ነው በማለት የተቃወመውን የጥዋት ብርሃን አነስተኛና መለስተኛ የግል ጀልባ ባለንብረቶች ማህበር ፣ ያልኩትን አልፈጸማችሁም በማለት አስራ አምስት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከዓመት በዓሉ ጋር ተያይዞ የሸቀጦች ዋጋ እየናረ ነው
ጷግሜን ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለለስልጣን ሰሞኑን የአዲስ ኣመት በዓልን አስመልክቶ በሸቀጦች ላይ ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ቢናገርም፣ የሸቀጦች ዋጋ ከንረት ሊታደገው አለመቻሉን ያነጋገርናቸው የአዲስአበባ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በአዲስአበባ በሳሪስና በሾላ ገበያዎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ሰሞኑን የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ በገበያዎቹ የአበሻ በመባል የሚታወቀው ሽንኩርት በኪሎ ከ17- ...
Read More »በአርበኞች ግንቦት7 ስም የተከሰሱት በእስር ቤት የደረሰባቸውን በደል ተናገሩ
ጷግሜን ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ የነበረው አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በእስር ቤት እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ እንዲሁም መስክሮች በሃሰት መስክሩ ተብለው እግራቸው እንደተሰበረ ሲገልጽ፣ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የታች አርማጭሆ ተወካይ አቶ አንጋው ተገኝ ደግሞ በእስር ቤት ውስጥ በጨለማ ቤት በመቀመጡ አይኑን መታተመሙንና ህክምና መከልከሉን ገልጿል። ...
Read More »የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግላቸውን ቀጥለዋል
ጷግሜን ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምስራቅ ሸዋ ዞን ናዝሬትና ሻሸመኔ ዙሪያ አሳሳ፣ ዶዶላ፣ አርሲ ነገሌ፣ አጄ፣ ኮፈሌ፣ ሄረሮ እና አዳባ በሚገኙ ሰባት ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊሞች በግድግዳዎች ላይ የተቃውሞ ጽሁፎችን በመጻፍና በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ከድምጻችን ይሰማ ጋር አብረው እንደሚታገሉ አሳውቀዋል። የሕዝበ ሙስሉሙ ተቃውሞ በአካባቢው ባለስልጣናት ላይ መደናገጥ የፈጥረባቸው መሆኑን አንዳንድ ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ድምጻችን ይሰማ ትግሉን ወደ አንድ ...
Read More »አራት የተቃዋሚ ድርጅቶች ጥምረት መመስረታቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ቀረቡ
ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስልጣን ላይ ያለውን የኢህአዴግ አገዛዝ በሃይል ለማስወገድ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ” አገር አድን ሰራዊት” ማቋቋማቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው። የአፋር ድርጅት የጋራ ንቅናቄ፣ የትግራይ ህዝብ የጋራ ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲ ሃይሎች ንቅናቄ እና አርበኞች ገንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በጋራ የአገር አድን ንቅናቄ የሚባል ድርጅት መመስረታቸውን ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓም ያስታወቁ ሲሆን፣ ...
Read More »አቃቢ ህግ በአርበኞች ግንቦት7 ስም በተከሰሱት ላይ ምስክሮችን አሰማ
ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቃቢ ህግ ምስክሮችን ያሰማው በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ችሎት ላይ ሲሆን፣ በተከሳሾች ወርቅዬ ምስጋናው፣ አማረ መስፍን፣ ቢሆኝ አለናና አትርሳው አስቻለው ላይ 6 ምስክሮች ቀርበው መስክረዋል። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው አቃቢ ህግ ያቀረባቸው 13 ምስክሮች ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ግልጽ አድርጎ ባለማቅረቡ ጠበቆች ተቃውሞ አስምተዋል። አንደኛው ምስክር በ12ኛው ተከሳሽ አትርሳው አስቻለው ላይ በመሰከረበት ወቅት፣ “ለየትኛው ...
Read More »ለትምህርት ጥራቱ መጓደል የዘመቻ ስራዎችና የመምህራን ፍለሰት ዋነኛዎቹ ምክንያቶች ሆነዋል ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ
ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ለልዩ ልዩ ባለሙያዎች ባቀረበው የቀጣይ አምስት አመታት የትምህርት ዕቅድ ውይይት ላይ፣ ባለፉት አመታት የትምህርትን ስራ በትምህርት ባለሙያዎች ሳይሆን ለጉዳዩ ዕውቅና በሌላቸው የፖለቲካ ሰዎች እንዲመራ መደረጉና የዘመቻ ስራ ላይ ማተኮሩ የትምህርቱ ጥራት ለመውደቁ ዋና መንስዔ መሆኑን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ባለሙያዎች በአዲስ ዓመት የትምህርት ...
Read More »በሶማሊያ የእስርስበርስ ግጭት እንዲፈጠር የኢትዮጵያ ጦር ምክንያት እየሆነ ነው ተባለ
ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኞ ዕለት በሶማሊያ ጌዶ ግዛት የቀድሞ አስተዳዳሪ የነበሩት ሞሃመድ አብዲ ከሊል ከባድ መሳሪያ ከታጠቁ አጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን ጋርባሃሬ ከተማ ሲገቡ አካባቢው የጦርነት ድባብ ውስጥ መውደቁን የከተማዋ ነዋሪዎች እማኝነታቸውን ሰጡ። የገርባሃሬ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሰራዊት የሚደገፈው አዲሱ የጁባላንድ አስተዳዳሪ አህመድ ማዶቤ በከተማዋ በኃላፊነት መሾሙ እየታወቀ የሞሃመድ ከሊል ወደ ከተማዋ ተመልሶ መምጣት እንዳስገረማቸው ገልጸዋል። የቀድሞ ...
Read More »ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ምላሽ አልተገኘም
ኢሳት ዜና (ጳጉሜ 2, 2007) የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ወደ አምስት ሚሊዮን ሰዎች ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምላሽ አለማግኘቱን ገለጠ። ከእርዳታ ሰጪዎች የታየውን ዝምታም ተከትሎ መንግስት ከአገር ውስጥ ገበያ የእህል ግዥ ለማከናወን መገደዱን የግብርና ሚኒስትር ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። የእርዳታ ሰጪዎች በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ችግር ውስጥ ለገቡ እንዲሁም በመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ የኔፓል ህዝብ እርዳታ በማቅረብ ላይ ...
Read More »ህወሃት/ ኢህአዴግ በኤርትራ ላይ ወራራ ሊፈጽም ይችላል ተባለ
ኢሳት ዜና (ጳጉሜ 2, 2007) የኤርትራ መንግስት ከጎረቤት ኢትዮጵያ ወታደራዊ ወረራ ሊፈጸምብኝ ይችላል ሲል ዛሬ ሰኞ ገለጠ። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ (ህወሃት) ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገሪቱ ላይ እያቀረበ ያለው ፀብ-ጫሪ መግለጫና ንግግር እየጨመረ መምጣቱን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ማመልከቱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የተለያዩ ሃይሎችን ድርጊት ከኤርትራ ጋር ለማቆራኘት ጥረት ሲያደርግ የቆየው የህወሃት ገዢ ፓርቲ ከተያዘው ክረምት ...
Read More »