.የኢሳት አማርኛ ዜና

ህወሃት ኢህአዴግ በመዳከሙ የቀድሞ አባሎቹን ለማሰባሰብ ሙከራ እያደረገ ነው ተባለ

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የህወሃት መስራችና በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አባል የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ ህወሃት ኢህአዴግ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሞ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ፣ ከድርጅቱ የለቀቁ የቀድሞ አባሎቹን በማነጋገር ወደ ድርጅታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ገልጸዋል። ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ የውስጥ ችግር መዳከሙን የሚገልጹት ዶ/ር አረጋዊ ፣ ...

Read More »

በካዛንችስ በርካታ የንግድ ቤቶች እየፈረሱ ነው

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ውስጥ በንግድ እንቅስቃሴያቸው ከሚታወቁት አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው ካዛንችስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤቶች በብዛት የፈረሱ ሲሆን፣ መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ነዋሪዎች ስጋት ገብቷቸዋል። የመንግስት ቤቶችን ተከራይተው ይሰሩ የነበሩ የንግድ ድርጅቶች በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች እንዲሰማሩ ቢደረግም፣ የግል የንግድ ቤት የነበራቸው ግን በካሳ መልክ የተከፈላቸው ገንዘብ ...

Read More »

የውጭ ምንዛሬ ገቢው እቅድ የማይጨበጥ ህልም ነው ተባለ

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከያዝነው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የወጭ ንግዱን ከ3 ወደ 12 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ መታቀዱ አሁን ሀገሪቱ ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ እጅግ የተጋነነና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ያተኮረ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ባለሙያው እንደሚሉት በመጀመሪያው የመንግስት ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ተቋማት የትምህርት አገልግሎት አሰጣጥና የክፍያ ስርዓት መመሪያ አወጣ፡፡

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዋጋ ቁጥጥር ውሳኔው አንዳንድ ት/ቤቶች አደናግጦአቸዋል፡፡ መመሪያው ፍትሐዊነት ጎድሎታል ያለውን የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ሁኔታ ሰርኣት የሚያሲዝ ነው ቢባልም ፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። አዲሱ መመሪያ ከስርኣተ ትምህርት ውጪ ልዩ ልዩ የትምህርት ኣይነቶችን ማስተማርና ለዚህም ክፍያ መጠየቅ ይከለክላል፡፡ ክፍያ ሲጠየቅ ለ10 ወራት ብቻ መሆኑን፣ የክረምትና የቅዳሜና እሁድ የማጠናከሪያ ትምህርቶች ...

Read More »

በኩዌት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔው ጸናባት

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በኩዌት ሱላቢካት ከተማ ውስጥ የአሰሪዋን ልጅ የ19 ዓመቷን ወጣት ሲሃም ማህሙድ በስለት በመግደል ወንጀል ተከሳ የነበረችው የ22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ወጣት ራቢያ ማህሙድ ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ ውሳኔ መፅናቱን የአገሪቱ ፍርድ ቤት አስታውቋል። ግድያውን ለመፈጸም ያበቃት ሟቿ መኝታ ክፍልዋ በተደጋጋሚ ጊዜ በመምጣት በር በመዝጋት ጥቃት የምትፈጽምባት መሆኑንና ይህ ተደጋጋሚ ጥቃት ...

Read More »

በኮንጎ ብራዛቪል ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮንጎ ብራዛቪል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በመላው የአፍሪካዊያን ጫወታ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው። በ5 ሺ ሜትር የወንዶች የሩጫ ውድድር ጌትነት ሞላ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፣ ርቀቱን በ 13 ደቂቃ 21 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ልዑልሲ ገብረስላሴ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። በ1 ሺ500 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድርም ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ...

Read More »

በወናጎ ከተማ በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገዶ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 16፣ 2008 ዓም በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ወናጎ ከተማ ከንግድ ቤት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ውዝግብ አድጎ ወደ ብሄረሰቦች ግጭት በማምራቱ በርካታ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ የተለያዩ የንግድ ቤቶችም ተዘርፈዋል። የከተማው ባለስልጣኖች ሆን ብለው ቀስቅሰውታል በተባለው በዚህ ግጭት፣ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ነን የሚሉ ሰዎች፣ የሌላ አካባቢ ብሄረሰቦች አካባቢያችንን ለቃችሁ ውጡ በማለት ግጭት ...

Read More »

የሲፒጄው ተወካይ የኢትዮጵያን ጋዜጠኞች አደነቁ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት፣ ሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ቶም ሮድስ፣ የዞን 9 ጸሃፊዎች የዚህን አመት የአለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሽልማት የሚገባቸው በርካታ ጋዜጠኞች አሉ ሲሉ ጋዜጠኞች ለፕሬስ ነጻነት እየከፈሉ ያለውን መስዋትነት አወድሰዋል። የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችን ለመሸለም የፈለግነው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፕሬስ አፈና ለአደባባይ ...

Read More »

ኢህአዴግ ከሚያደርገው የካቢኔ ሹምሽር አዲስ ነገር ላይጠበቅ ይችላል ተባለ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፊታችን መስከረም 24 ቀን በኢህአዴግ መቶ በመቶ የተያዘው ፓርላማ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የጠ/ሚኒስትርነት ሹመት ካጸደቀ በሃላ በጠ/ሚኒስትሩ አቅራቢነት የሚካሄደው የካቢኔ ሹም ር አዲስ ነገር ይዞ አይመጣም ተብሎአል። ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን እንደተናገሩት ግንባሩ በሙስናና በመልካም አስተዳደር ችግሮች በተጨማለቁ የካቢኔ አባላት ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ካልቻለ ...

Read More »

የህንዱ ፓወር ግሪድ ከ 400 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተከፍሎት ስራውን ለቀቀ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ድርጅትን እንዲያስተዳደር ለሁለት አመታት 21 ሚሊዮን 700 ሺ ዶላር ወይም ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለው ፓወር ግሪድ ይህ ነው የሚባል ስራ ሳያከናውን ተሰናብቷል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የመብራት መጥፋት ሊሻሻል ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ፣ ቀድሞውንም ይህን ያክል ገንዘብ ማውጣት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ስራ አስኪያጅ የሚሾሙትና የሚያወርዱት ዶ/ር ደብረጺዮን ...

Read More »