መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስካሁን 13 ሰዎች እንደሞቱ ቢገልጽም፣ የመጨረሻው መረጃ ይፋ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊልቅ ይችላል። ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ሼህ አህመድ ከሳውድ አረቢያ እንደገለጹት፣ 13 ቱ ሟቾች የተለዩት ዘመዶቻቸው ባረጋገጡት መሰረት ነው። የሳውዲ መንግስት የሟቾችን ቁጥር ሙሉ በሙሉ ለማሳወቅ እንዳልቻለ የገለጹት ሼህ ሙሃመድ፣ ከዚህ ቀደም ከክሬን መውደቅ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በዛምቢያ በእስር ቤት ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተላኩ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዛንቢያ የስደተኞች ቢሮ በአገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ በመግባታቸው ክስ ከቀረበባቸውና የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ሃያ ስድስት የውጭ አገር ዜጎችን ወደየትውልድ አገራቸው መመለሱን አስታውቆ፣ ከእነዚህ መካከል 16ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ከኬንያ ጀምሮ ባሉት የመሸጋገሪያ አገራት ውስጥ አያሌ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስርቤትና በታጋቾች በደልና ስቃይ እየደረሰባቸው ሲሆን ፣ ኤንባሲዎች ዜጎቻቸውን ለመታደግ የሚያደርጉት ...
Read More »በገጠር መንገዶች ላይ ሚታየው የጥራት ችግር አሁንም አለመፈታቱ ተነገረ፡፡
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ገጠር መንገድ ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ባደረገው አመታዊ የሰራተኞች ስብሰባ ላይ ችግሩ አለመቀረፉን የገለጹት ባለሙያዎችና የድርጅቱ ሰራተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ የሚያሳማው የጥራቱ ጉዳይ መሆኑን ተናገረዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁልጊዜ ሊያሻሽለው አልቻለም በማለት ባለሙያዎች ያቀረቡት የጥራት ጉዳይ መንገዶች ጥገና ተደርጎላቸው ከተሰሩ በኋላም ተገቢውን ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ በመበላሸታቸው በወረዳና ዞን አካባቢ ...
Read More »የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች ስጋት ላይ ናቸው
መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ ገዥው ፓርቲ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን የመልካም አስተዳደር፣ የሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን አጋልጡ በሚል ከፍተኛ ግፊት ማድረጉን ተከትሎ ትርምስ መፈጠሩ ተሰማ፡፡ የመገናኛ ብዙሃኑን መሪዎች ጨምሮ አንዳንድ ጋዜጠኞች በሙስናና ብልሹ አሠራር የሚጠረጠሩ መሆናቸው ይበልጥ ነገሩን አወሳስቦታል፡፡ ኢህአዴግ በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔ በመልካም አስተዳደር ችግሮች መተብተቡንና ሕዝቡ ...
Read More »በአፋር የስልጣን ውዝግብ የህወሃት ደጋፊዎች ማሸነፋቸው ተሰማ
መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት ነባር ታጋይና በሁዋላም የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አብዴፓን) መስርተው ክልሉን ላለፉት 24 ዓመታት ሲመሩት የቆዩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ፣ ከስልጣን ተነስተው ወደ ፌደራል ሲዛወሩ እርሳቸውን ለመተካት በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ፣ ህወሃት የደገፋቸው ቡድኖች አሸናፊዎች ሆነው መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ቀድም ብለው ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡት ወጣቱ አቶ ጣሃ አህመድ ፣ የድርጅቱ ...
Read More »በረሃብ የተጠቁ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ
መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኤልኒኖ የአየር መዛባት ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሳቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕፃናትን ጨምሮ ከ4.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከፍተኛ በሆነ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑንና አፋጣኝ የሆነ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአውስትራሊያው ቻይልድ ፈንድ በሪፖርቱ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ያለው የርሃብ ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና በተለይ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብና በሶማሌ ክልሎች ለአስከፊ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ህጻናት ...
Read More »በጣሊያን ፍሽስት ወረራ ወቅት ለተፈጸመው ግፍ ጣሊያን ካሳ እንድትከፍል ተጠየቀ
መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ፍሽስት ወረራ ወቅት ለተፈጸሙት ዘግናኝ ግፎች የጣሊያን መንግስትና ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁና የተዘረፉት ቅርሶችና ንብረቶች ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ዓለምአቀፍ ሕብረት ለፍትሕ ጥያቄውን አቀረበ። በጣሊያን ወረራ ወቅት የጣሊያን ወራሪዎች በዓለም ላይ የተከለከለውን ካለስተር ቦንብ ተጠቅመው ንፁሃን ኢትዮጵያዊያንን ጨፍጭፈዋል፣የታሪክ ድርሳናትን ዘርፈዋል፣ውሃን በመርዝ ...
Read More »ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ታሰረ
መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ችግር በማጋለጥ እንዲሁም የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ፣ በየመን የጸጥታ ሃይሎች መታሰሩ ታውቋል። ጋዜጠኛ ግሩም በምን ምክንያት እንደታሰረ የታወቀ ነገር የለም። ኢሳት ባለቤቱን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም። በየመን በመካሄድ ላይ ያለውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘረኝነት እየተወነጀለ ነው
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን ስራውን የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትርፋማነቱ በተለያዩ አለማቀፍ የንግድ ተቋማት እየተመሰገነ ቢመጣም፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ” ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ክሶችን እያቀረቡ ነው። አየር መንገዱ ጀምሮት ከነበረው የቁልቁለት ጉዞ የታደጉት አቶ ግርማ ዋቄ ስራቸውን ከለቀቁ በሁዋላ፣ በምትካቸው የተሾሙት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሄር ሰዎች ለማስያዝ እንቅስቃሴ ...
Read More »ቤት ሰሪ የመንግሰት ሰራተኞች አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ የ1997ቱን ምርጫ ውጤት ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቶ የነበረው ኢህአዴግ የህዝቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በሚል የቤት ፈላጊዎችን በማህበር ካደራጀ በሗላ ፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ እንዲቆጥቡ በማድረግ ከ9 ዓመታት በሗላ የቤት መስሪያ ቦታቸውን ለቤት ሰሪዎች ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጅ ቤቱን መስራት የሚችሉት መንግስት ባወጣላቸው የቤት እቅድ መሰረት ባለፎቅ ቤት ...
Read More »