መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እድለኞቹ በአስተዳደሩ አታላይ ፕሮፖጋንዳ ማዘናቸውን ገልጰዋል። አስተዳደሩ ምርጫ 2007 ተከትሎ ከ32ሺ በላይ ቤቶች ላይ እጣ በመጋቢት ወር 2007 ያወጣ ሲሆን ቤቶቹንም በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከማስረከብ አልፎ ቀጣዩን እጣ በሰኔ ወር 2007 እንደሚያወጣ ቃል ቢገባም አንዱንም መፈጰም ሳይችል ቀርቶአል። አስተዳደሩ የካርታ ስራ እንዳዘገየው ቢናገርም እውነቱ ግን ቤቶቹ ባለመጠናቀቃቸው መሆኑን የአስተዳደሩ ምንጮች አጋልጠዋል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ” በሰባ ደረጃ” የተሰኘው ነጠላ ዜማ “የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ” በመባል በሸገር 102 ነጥቨብ 1 የለዛ ራዲዮ ፕሮግራማ አደማጮች ተመረጠ።
መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንጋፋው ድምጸዊ አለማየሁ እሸቴ ደግሞ የህይወት ዘመን ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። ከለ380 በላይ ሙዚቃዎችን የሰራው ድምፃዊ ኣለማየሁ አሸቴ ከ ዘመናዊ ሙዚቃ ፋናወጊው ከግርማ በየነ እጅ ሽልማቱን ከተረከበ በሁዋላ ባደረገው ንግግር ፦“ምናለ ጊዜን መመለስ ብችል እና ካለፉት ጓደኞቼ ጋር ይህን ቀን ባከብረው” በማለት ብዙዎችን ስሜት ውስጥ አስገብቷል። አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በበኩሉ ፦”ሰባ ደረጃ ...
Read More »የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት በሚል ቅጥያ የሚጠሩትና የተቸገሩ ስፖርተኞችን በመርዳት የሚታወቁት አቶ አቤሴሎም ይሕደጎ አረፉ
መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገራችን አትሌቲክስ ስፖርት ሲነሳ ስማቸው አብሮ የሚነሳውና ለብዙ ሯጮች የችግራቸው ተጋሪ በመሆን አገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት የቀስተደመና ስፖንጅ ፋብሪካ መስራች እና ባለቤት አቶ አቤሴሎም ይሕደጎ በተወለዱ በ79 ዓመታቸው ሀሙስ መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ አቤሴሎም የቀብር ስነስርዓት ቤተሰቦቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ቅዳሜ ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ...
Read More »የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ተጨማሪ የስርጭት መስመር ከፈተ
መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ገዢው ፓርቲ የሚያደርስበትን ተደጋጋሚ አፈና ተቋቁሙ ተጨማሪ የስርጭት መስመር የከፈተ ሲሆን ስርጭቱን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በሚከታተለው ናይል ሳት ላይ በቀላሉ ማግኘት እንደሚቻል አስተዳደሩ አስታውቋል። የአዲሱ ስርጭት ሙከራ እንደተሳካ ዝርዝር መረጃውን የምናቀርብ መሆኑን ለመግልጽ እንወዳለን።
Read More »በህወሃት የሚደገፉት አቶ ስዩም አወል የአፋር ክልልና የአብዴፓ መሪ ሆነው ተሾሙ
መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሁለት ጎራ ተከፍለው ሲወዛገቡ የቆዩት የአፋር ክልል ባለስልጣናት ፣ የህወሃት ድጋፍ ያለው አቶ ስዩም አወልና የአቶ አሊ ሴሮ ቡድን በአሸናፊነት ከወጣ በሁዋላ፣ ላለፉት 20 አመታት የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ሃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ስዩም አወል አሁን ከያዘው ስልጣን በተጨማሪ የክልሉ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል። በተቃራኒ ጎራ የተሰለፈውና የተማረውን ሃይል አካቷል የተባለው የአቶ ጠሃ ...
Read More »አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የኦህዴድን ፖለቲከኞች አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል
መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል የሚገኙ የአዲስ አበባ አጎራባች ቀበሌዎችን ወደ ዋናዋ ከተማ የሚጠቀልለው አዲሱ ማስተር ፕላን ወይም ፍኖተ ካርታ፣ አርሶደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ለጥቂት የዘመኑ ባለሃብቶች ለመስጠት ተብሎ የተዘጋጀ ነው በማለት ተቃውሞ ያሰሙ የኦሮሞ ወጣቶች መገደላቸውንና መታሰራቸውን ተከትሎ፣ ለአንድ አመት ያክል ከመጽደቅ እንዲዘገይ የተደረው እቅድ እንደገና ለማጸደቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ የኢህዴድ አባላትን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። የህወሃት/ኢህአዴግ ...
Read More »በአፍሪካ ውስጥ በግድቦች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለወባ በሽታ የተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች አረጋገጡ
መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ውስጥ በግድቦች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለወባ በሽታ የተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች አረጋገጡ በዓመት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች በግድቦች አካባቢ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በወባ በሽታ የሚጠቁ ሲሆን በአዲሱ ዓመት ብቻ ከሰባ ስምንት በላይ አዳዲስ ግድቦች በመሰራታቸው ተጨማሪ ሃምሳ ስድስት ሽህ የወባ ተጠቂዎች እንደሚኖሩ ጥናቱ ጠቁሟል። የውሃ ግድቦችን ለኃይል ማመንጫነት መጠቀም ከሰሃራ ...
Read More »ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ህግና ስርኦቶች መከበር 42 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ተባለ
ኢሳት ዜና (መስከረም 19 ፣ 2008) በአለማችን የደህንነት ስጋት ይታይባቸዋል ተብለው ከተፈረጁት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ በ 42ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናት ያካሄደ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጠ። የዘንድሮውን አመታዊ ረፖርት ይፋ ያደረገው ጋሉፕ አናሊቲክስ የተሰኘውና በአለም አቀፍ ህግና ስርኦቶች መከበር ዙሪያ የሚሰራው ተቋም በ 141 የአለማችን ሃገራት ላይ በተካሄደው ጥናት ኢትዮጵያ 42ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን አስታውቋል። በየሃገራቱ ያሉ ...
Read More »ለሰብዓዊ መብት ስብሰባ ወደስዊዘርላንድ የተጓዙ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ስብሰባ ረግጠው ወጡ
ኢሳት ዜና (መስከረም 19 ፣ 2008) የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጄኔቭ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ካለው 30ኛ ጉባኤ ጋር ተያይዞ በተጠራ መድረክ ላይ የተጋበዙት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ስብሰባ ረግጠው ወጡ። ስኞ እለት የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት በተመለከተ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተገኙትና በኋላ በቀረበው ሪፖርት ሳይደሰቱ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ወደ ስብሰባው አልተመለሱም። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተወካዮች ጨምሮ የተለያዩ አለም ...
Read More »በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ከፍተኛ የውሃና የምግብ እጥረት መከሰቱን ሰነዶች አመለከቱ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶችና መንግስት በጋራ በፈረንጆች አቆጣጠር ሴፕቴምበር 24 ፣ 2015 ያደረጉት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ እንደሚያስረዳው ፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች እጅግ አሳሳቢ የሆነ የውሃና የምግብ እጥረት ተከስቷል። ችግሩም በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንደሚጨምር ለኢሳት የደረሰው ቃለ ጉባኤ ያስረዳል። በተለይ በሶማሊ ክልል ባለው የጸጥታ ሁኔታ አስቸኳይ ምግብና ውሃ ...
Read More »