መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒቨርሳል ቲቪ ጋዜጠኞች የታሰሩት፣ ሁለት የፓርላማ አባላትን ጋብዘው የኢትዮጵያ ጦር በአገሪቱ ውስጥ መቆየት አለበት የለበትም የሚል ክርክር በማድረጋቸው መሆኑን የጣቢያው የዜና ክፍል ሃላፊ የሆነው ጋዜጠኛ አብዱላዚዝ ኢብራሂም ሙሃመድ ተናግሯል። በርካታ የሶማሊያ ዜጎች የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መቆየቱን መቃወም ጀምረዋል። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አልሸባብን በ2 ሳምንታት ውስጥ ደምስሰን እንወጣለን ቢሉም ፣ ጦሩ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህራንና ሰራተኞች በግዳጅ ስልጠና እየወሰድን ነው አሉ
መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች ላይ ከኢሕአዴግ መንግስት የሚሰነዘረው የፖለቲካ ጠልቃ ገብነትና አፈና ከመቼውም ጊዜ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በምሬት ተናግረዋል። የኢሕአዴግ መንግስት “ስልጠና’ በሚል ስም በአገር-አቀፍ ደረጃ ካዘጋጃቸው ስብሰባዎች አንዱ በሆነው ሰብሰባ ጠቅላላውን የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ከሰኞ መስከረም 10 እስከ 16 2008 ዓ/ም አዳራሽ ውስጥ ...
Read More »ከ8 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ ተጋልጧል
መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት እና አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ 4 ሚሊዮን 500 ሺ ህዝብ በረሃብ መጠቃታቸውን ይፋ ቢያደርጉም፣ በከተሞች የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ዜጎች ቁጥር ሲጨመር አጠቃላይ የተረጅዎችን ቁጥር ከ8 ሚሊዮን በላይ ሊያደርሰው እንደሚችል መረጃዎች አመልክተዋል። በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሪፖርት ሲደረግ የቆየው በገጠሩ የሚታየው ችግር ብቻ ነው። ይሁን እንጅ የከተማና የኮንስትራክሽን ልማት ሚኒስትር መኩሪያ ሃይሌ ...
Read More »በቴፒ የሚታየው ውጥረት አለመርገቡን ነዋሪዎች ገለጹ
መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብና የጋምቤላ አዋሳኝ በሆነቸው ቴፒ ከተማ በየጊዜው የሚታየው የጸጥታ ችግር ሰሞኑን እንደገና አገርሽቶበታል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ካለፈው አመት ጀምሮ ከፍ ዝቅ እያለ ሲካሄድ የነበረው ግጭት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ በህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ልዩነትም ሰፍቷል። መስከረም 20 ብርሃኑ የተባለ የዩኒቨርስቲ ጥበቃ የተገደለ ሲሆን፣ ለግድያው እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም። ባለፈው አመት የአካባቢው ...
Read More »በጉንዶ መስቀል ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ ውጥረት ነግሷል
መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በጉንዶ መስቀል ከተማ በሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ1 200 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ መወሰኑን ተከትሎ በከተማው ውጥረት ነግሷል። የከተማው ባለስልጣናት ህዝቡን ሰብስበው ቤቶቻችሁን አፍርሱ ብለው ትእዛዝ ሲሰጡ፣ ነዋሪዎቹ ግን አጥብቀው ተቃውመዋል። መስከረም 13 ቀን በከተማው የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በፌደራል ፖሊሶች ቢጨናገፍም፣ ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለና የከተማው መስተዳድር ተጨማሪ ...
Read More »በሻሸመኔ ካህናት እርስ በርስ ተደባደቡ
መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጠዋት በሳሸመኔ ተክለሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን መቅደስ ውስጥ ካህናትና ዲያቆናት እርስ በርስ በመደባደባቸው ሰዎች ተገድተዋል። የግጭቱ መንስኤ የቆየ መሆኑን የሚናገሩት ምእመናኑ ዛሬ የተፈጠረው ድርጊት ግን ያልተጠበቀ ነው። ካህናቱ ጎራ ለይተው መደባደባቸውን ተከትሎ አካባቢው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎአል። ኢሳት ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት ባይችልም፣ በሰአቱ የተኩስ ድምጽም ተሰምቷል። ጥይቱን ማን ተኮሰው የሚለው ጥያቄ የከተማው ...
Read More »አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ለአዲሱ የፕሬስ ትውልድ ፈር ቀዳጅ ነበር ተባለ
መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች “መልካም ስም ከመቃብር በላይ ዘላለማዊ ሆኖ ይኖራል” በሚል ርዕስ ባወጡት መግለጫ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲረጋገጥ፤ ብሎም ለአዲሱ የፕሬስ ትውልድ ፈር ቀዳጅ የነበረው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ለብዙዎች የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ቤተሰቦች መሪር ሃዘን ነው ብለዋል። ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በአንደበቱ እውነትን የመሰከረ፤ ...
Read More »ከወራት በፊት በነጻ እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው አምስቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለጥቅምት 3 ተቀጠሩ።
መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ ነገረ ኢትዮጰያ ሪፖርተር ዘገባ ከአምስቱ እስረኞች መካከል አንዱ የሆነው የአንድነት ፓርቲው አቶ ዳንኤል ሽበሽ ጨለማ ቤት ታስሮ ይገኛል። የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲለቀቁ ወስኖላቸው የነበሩት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሽበሽና አቶ አብርሃም ሰለሞን ለመጪው ...
Read More »ሱዳን ከኤርትራ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋገጠች።
መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢዪን እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ይህን ያረጋገጡት፤ ዛሬ ሀሙስ ከኤርትራው የፋይናንስ ሚኒስቴር ከአቶ ብርሀኔ ሀብተማርያም ጋር ካርቱም ውስጥ ባደረጉት ውይይት ነው። ሰሞኑን ካርቱም በኤርትራ የነበሩ የኢትዮጰያ አማጽያንን ወደ ኢትዮጵያ አሸጋግራለች የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ በኤርትራና በሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ሊሻክር እንደሚችል እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ፤ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ...
Read More »በአማራ ክልል ካሉት ትምህርት ቤቶች መስፈርቶችን የሚያሟሉት ከ 30 በመቶ አይበልጡም ተባለ።
መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ይህን ያሉት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ ስዩም አድማሱ ናቸው። ሀላፊው በ2002 ዓ.ም በታቀደው የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ በትምህርት ዘርፍ በርካታ ያልተሳኩ የአፈጻጸም ችግሮች መኖራቸውን ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባለፉት አምስት ዓመታት በትምህርት ዘርፉ የታቀዱ ስራዎች የአፈጻጸም ችግሮች እንደታዩባቸው ...
Read More »