መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስከረም 13 ቀን 2008 ዓም የሃጅ ጸሎት ለማድረስ ወደ አገሪቱ ከተጓዙት ኢትዮጵያውያን መካከል 47 ሙስሊሞች መሞታቸውን የእስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት አስታውቋል። 24 ጸሎት አድራሽዎች ቆስለው ከሆስፒታል ሲወጡ ፣ 2ቱ አሁንም ተኝተው በመታከም ላይ ናቸው። በእለቱ በደረሰው አደጋ የሳውዲ መንግስት 700 ሰዎች እንደሞቱ ቢናገረም፣ በእየለቱ የሚወጣው አሃዝ የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ መሆኑን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በእስር ላይ የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በነፃ እንዲሰናበቱ ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ጠየቀ
መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቡድኑ ነገ ሃሙስ ክሳቸው ለ37ተኛ ጊዜ በፍርድ ቤት የሚታየውና በመፃፋቸው ብቻ በአሸባሪነት ክስ ተወንጅለው በእስር ላይ የሚገኙት አራቱ የዞን 9 ጦማሪያን ቡድን አባላት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ክሳቸው ተቋርጦ በነፃ እንዲለቀቁ ሲል አሳስቧል። ካለፈው ዓመት ጀምሮ በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች አጥናፍ ብርሃነ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣አቤል ዋበላ እና ናትናኤል ፈለቀ እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር ...
Read More »ጸረ ሙስና ወደ አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከዝርፊያ ማዳኑን አስታወቀ
መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ በማካሄድ ላይ ባለው 11ኛ ጉባኤ በተለያዩ ክልሎች ከ937 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳኑን ገልጿል። ከክልሎች ሁሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከስርቆት የዳነው በአማራ ክልል ነው ሲል አክሎ ጠቅሷል። በዚህ ጊዜ እንደተገለጸው ግልጽነት በጎደለው የግዢ ሂደት ሊባክን የነበረ ከ937 ሚሊየን ብር በላይ የህዝብ ገንዘብ ለማዳን ተችሏል። ከሙስና ጋር በተያያዘ ከ3 ሺ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ...
Read More »አስራ አራት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ተያዙ
መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ኬንያ ሲገቡ መንገድ ላይ ያዝኳቸው ያለውን አስራ አራት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የኬንያ ፖሊስ ይዞ ማቻኮስ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል።ስደተኞቹ የቀረበባቸውን ክስ ያልተቀበሉት ሲሆን የሃያ ሽህ ሽልንግ የገንዘብ ቅጣት ወይም የመቶሰላሳ ቀናቶች የእስር ቅጣት እንደሚበየንባቸውና ቅጣቱን ከከፈሉ በኋላ ወደ አገራቸው እንደሚላኩም ተገልጿል። ስደተኞቹ በናይሮቢ ሞንባሳ አውራ ጎዳና በማቻኮስ በቹሙቪ የገበያ ...
Read More »በጎንደር የፌደራል ፖሊስ አንድ የመዋለ ህጻናት ወስዶ አልመልስም አለ
መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደገለጹት በከተማው ቀበሌ 9 የድሃ ልጆች የሚማሩበትን መዋለ ህጻናት ትምህርት ቤት፣ ምርጫውን ሰበብ ተደርጎ ለፌደራል ፖሊስ በጊዜያዊነት ከተሰጠ በሁዋላ፣ ፖሊስ አለቅም በማለቱ ከነዋሪዎች ጋር ውዝግብ ተፈጥሯል። ፖሊስ በ15 ቀናት ቦታውን እንደሚለቅ ገልጾ፣ ትምህርት ቤቱን ቢረከብም፣ እስካሁን ድረስ ባለመልቀቁ ወላጆች ልጆቻቸውን ማስተማር አልቻሉም። ወላጆች አቤቱታ ለማቅርብ ብንሄድም በፖሊሶች ተደብድበናል በማለት ገልጸው፣ ...
Read More »አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ አዲስ ካዋቀሩት ከቢኔ 5 የቀድሞ ሚኒስትሮችን ቀነሱ
መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ ካላካተቱዋቸው የቀድሞ ሚኒስትሮች መካከል የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ሶፍያን አህመድ፣ የንግድ ሚኒስትሩ ከበደ ጫኔ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አለማየሁ ተገኑ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አሚን አብዱልቃድር፣ የፕላን ኮምሽን ሚኒስትሩ አቶ መኮንን ማንያዘዋል ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም አቶ ሬድዋን ሁሴንን ከኮምኒኬሽን ሚኒስትርነት አንስተው የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ያደረጉዋቸው ሲሆን፣ የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ በማወሳሰብ ሲወነጀሉ የነበሩት ዶ/ር ...
Read More »በቴፒ ተጨማሪ ሰዎች ተገደሉ
መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአመት በላይ ለሆነ ጊዜ በውጥረት ውስጥ የምትገኘዋ የጋምቤላና የደቡብ አዋሳኝ ከተማ ቴፒ፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ሶስት ዜጎች ተገድለውባታል። ከሳምንት በፊት የፌደራል ፖሊስ አባላት አንድ ሰው ከገደሉ በሁዋላ፣ ማንነታቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ ደግሞ ከቴፒ 7 ኪሜትር እርቀት ላይ በምትገኝ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት የኢህአዴግ ካድሬዎችን ዛሬ ጠዋት ...
Read More »በስልጠና ላይ ያልተገኙ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ደሞዝ ታገደ
መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2008 ዓ.ም በ መንግስት ያዘጋጀውን የፖለቲካ ስልጠና ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆኑ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ደሞዛቸው እንዳይከፈል በመታገዱ የምንበላውና የቤት ኪራይ የምንከፍለው አጥተናል ሲሉ ገልጸዋል።በስብሰባው ላይ የተገኙ መምህራን ደሞዝ ሲከፈላቸው በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሰበሰቡት መምህራን ደግሞ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው ተነግሯቸዋል። በአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህራን ወደ ውጭ እንዳይወጡ ታግደው ስልጠናውን በግድ እንዲወስዱ ተደርገዋል። በሌላ ዜና ደግሞ ...
Read More »በአዲስ አበባ መስተዳድር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ተቀነሱ
መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመስተዳድሩ 10 ክፍለ ከተሞችና 116 ወረዳዎች የሚገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች የሹም ሽር እና የሹመት ቦታ ለውጥ መረጃዎች የታወቁ ሲሆን፣ የማዕከል መ/ቤት ቢሮዎችና ሹም ሽር ድልደላ በዚህ ሳምንት የሚጠናቀቅ ሆኖ፣ በወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች አጠቃላይ ቁጥራቸው ከ800 የማያንሱ አመራሮች በሙስና፣ከድርጅቱ ጋር ባላቸው ተቃርኖ፣ በአመራር ብቃት ማነስ እንዲሁም በትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆን በሚል ዝርዝር የግምገማ ...
Read More »በመንገድ ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ‹‹ አለመስራት አያስጠይቅም !! ›› የሚል ያልተጻፈ መመሪያ አለ ሲሉ ኦዲተሯ ተናገሩ
መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል መንገድ ስራ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚታዩ በርካታ የአሰራር ችግሮች ለከፍተኛ ሙስና ሊያጋልጡ እንደሚችሉ በመናገር በየጊዜው እንዲስተካከሉ ሰራተኛው ቢጠየቅም፣ ከዓመት ዓመት አለመቀረፋቸው በስርዓቱና አመራሮች እምነት እንዲያጡ እንዳደደረጋቸው የኦዲት ባለሙያዎች በዓመታዊው የሰራተኞች ስብሰባ ላይ ገልጸዋል፡፡ በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ስር በሚገኙ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በተደረገ አጠቃላይ ምርመራ በፋይናንስ አስተዳደርና በግዢ አፈጻጸም ቀደም ...
Read More »