.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአዲስ አበባ በርካታ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች እየፈሩሰ ነው

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአሜሪካ ጊቢ ፣ በአዲስ ከተማና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለአመታት ከኖሩበት ቤት ያለበቂ ካሳ እና ተለዋጭ ቤት ቤቶቻቸው እየፈረሰባቸው ነው። መንግስት ቤታቸው ለሚፈርስባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ተላዋጭ አድርጎ ቢሰጥም፣ ተከራዮች ግን ኪራዩን የመክፈል አቅም የላቸውም መንግስት ከህዝቡ ጋር ሳይማከር የሚወስደው እርምጃ፣ ከፍተኛ የኑሮ ቀውስ እየፈጠረ መሆኑን ...

Read More »

የዞን 9 ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ የዋስ መብቱ ሲፈቀድለት የሎሚ መጽሔት አዘጋጅ በሌሉበት 18 ዓመት ተፈረደባቸው

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ዓመት ከአምስት ወር በሽብር ክስ ተከሰው በእስር ሲንገላቱ የነበሩት የዞን 9 አምደ መረብ ጸሐፍት ውስጥ ብቻውን እንዲቀር ተደርጎ የነበረው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ክሱን ውጪ ሆኖ እንዲከታተል የሃያ ሽህ ብር የዋስትና መብት የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት19ኛ ወንጀል ችሎት በመፍቀዱ ከእስር ተለቋል። በተጨማሪም የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስምንተኛ የወንጀል ችሎት የሎሚ መጽሄት ...

Read More »

እንግሊዝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ቅደሚያ እንድትሰጥ በድጋሜ ተጠየቀች

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙትን የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ህገወጥ እስር አስመልክቶ የእንግሊዝ ባለስልጣናት ነገ በሚጀመረው የኢትዮጵያና የእንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ላይ ሊያነሱት እንደሚገባ አቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ጠይቋል። የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስብሰባው ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው እንደመሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግራንት ሻፕስ ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-18 የእስር አመታት በግፍ ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 አሸናፊ ሆነ መመረጡን ድርጅቱ አስታውቋል። ለብዙዎች የዲሞክራሲ ሃይሎች የጽናት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፉትን ሶስት አመታት በእስር ቤት አሳልፏል። የእስክንድር ስራዎቹ ድንበር እና ባህል ተሻጋሪ ናቸው በማለት ያወደሰው ድርጅቱ፣ 5 ሺ ዶላር የሚያሸልመው ...

Read More »

የወልቃይት ነዋሪዎች ወደ ትግራይ መካለላቸውን እንደማይቀበሉት አስታወቁ

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች “መሰረታችን ሕገ መንግስቱ ነው ተብሎ የወልቃይት ነዋሪዎች ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገና የሕዝቡን ስነ ልቦናዊ፣ ባሕላዊ ወግን ያላማከለና ያላጠቃለለ ክልላዊ አከላለል በማድረግ የወልቃይት ሕዝብ የማይፈልገውንና የማያምንበትን በመጫን በግድ ወደ ትግራይ እንድንካለል መደረጋችን በውስጣችን ያለውን ማንነታችንን በመጨፍለቅ እንድንቀበል እየተደረግን ነው ፣ዛሬ ስነ ልቦናችን የማይቀበለውን ሕወሃት በዘዴ ማንነታችንን ለማሸማቀቅ እየሞከሩ ነው” ብለዋል ። በማህበራዊ ...

Read More »

አቶ አበበ ካሴ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመበት እንደሆነ ገለፀ።

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው አቶ አበበ ካሴ እስር ቤት ውስጥ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየደረሰብኝ ነው ሲል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አሰምቷል፡፡ በእነ አበበ ካሴ የክስ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው አቶ ታጠቅ አስማረ የተከላካይ ጠበቃ ለማቅረብ ዛሬ ጥቅምት 9/2008 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት አቤቱታውን ...

Read More »

በአዲስ አበባ የንግድ ተቋማት እየታሸጉ ናቸው

ኢሳት ዜና (ጥቅምት በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካን ግቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ሶስት ሺ የሚጠጉ የንግድ ተቋማት ቦታው ለልማት ይፈለጋል ተብሎ ንብረታቸው መታሸጉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ። የንግድ ተቋማት መታሸግን ተከትሎም የአካባቢው ነዋሪዎች መሰረታዊ የፍጆታ እቅርቦቶችን ለማግኘት ተቸግረው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ወፍጮ ቤቶች ሱቆችና ምግብ ቤቶች ከታሸጉበት የንግድ ተቋመት መካከል እንደሚገኙበት የተናገሩት ነዋሪዎች የመንግስት አካላት የወሰዱት ...

Read More »

የብአዴን የቀድሞ ታጋዮች መንገድ ላይ ወጥተው በመለመን ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ በማድረግ የተለያዩ ጋዜጠኞችንና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ ጉዞ ላይ ፣ የትግል ተሞክሮ እንዲያካፍሉ የተጋበዙት የቀድሞ ታጋዮች በርካታ ጓዶቻቸው መጠለያ በማጣት በየከተማው በላስቲክ ቤት መንገድ ላይ እንደሚኖሩ ለጎብኝዎች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ህዝብ እንደኖረው ለመኖር ዕድሉን አልተሰጠንም፡፡ ›› የሚሉት ነባር ታጋዮች ...

Read More »

በአዋሽ መልካሳ አንድ የፌደራል ፖሊስ ተገደለ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሱ የተገደለው በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ተጣልቶ ነው። ፖሊሶች አንድ የግሮሰሪ ሰራተኛን ሲደበድቡ ፣ ወጣቶች በብስጭት በፌደራል ፖሊሱ ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በከተማዋ ከፍተኛ ግርግር መኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገዳዮችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ነው። የከተማው ወጣቶች የፌደራል ፖሊስ አባላት ከፍተኛ የሆነ ጫና እንደሚፈጥሩባቸው ለኢሳት ገልጸው፣ አሁኑ እርምጃም ...

Read More »

የአለም የመገናኛ ብዙሃን ስለኢትዮጵያ ድርቅ ሰፊ ሽፋን በመስጠት ላይ ናቸው

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታላላቆቹ የአለም የመገናኛ ብዙሃን መካከል ዘ ኒውዮርክ ታይምስና ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ የዜና ሽፋን በመስጠት ላይ ሲሆን፣ ዘ ኒዮርክ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ድርቁ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል። “ያሲን ሙሃመድ ከአነስተኛ የእርሻ ማሳው ላይ እየወሰደ ጫት ይቅማል፣ ለምን ተብሎ ሲጠየቅ ፣ ጫት ረሃብን ያስታግሳል “የሚል መልስ መስጠቱን የዘገበው ዘ ኒዮርክ ...

Read More »